Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Friday
Aug 29th
Home arrow Sections arrow ናይትሮጅንም እንደ ካርቦን ዳይኦክሳይድ
ናይትሮጅንም እንደ ካርቦን ዳይኦክሳይድ Print E-mail
Wednesday, 28 May 2008
ከዚህ በፊት በዓለም የሙቀት መጨመር ምክንያት የሚሆነው የካርቦን ዳይኦክሳይድ ልቀት መጨመር እንደሆነ ሲነገር ቆይቷል፡፡ ይሁንና ናይትሮጅንም ለአየር ሁኔታ ለውጥ ያለው አሉታዊ አስተዋፅኦ ከካርቦን ዳይኦክሳይድ እንደማይተናነስ አንድን ጥናት ጠቅሶ አሶሽየትድ ፕሬስ ዘግቧል፡፡

 

ዘገባው እንደሚያስረዳው የዓለም ህብረተሰብ እስካሁን ድረስ ናይትሮጅን በአየር ሁኔታ ለውጥ ላይ ስላለው አስተዋፅኦ የሚያውቀው ነገር የለም፡፡ ነገር ግን የካርቦን ዳይኦክሳይድን ያህል ትኩረት የሚሻ ጉዳይ እንደሆነ በቨርጂንያ ዩኒቨርሲቲ የአካባቢ ሳይንስ ፕሮፌሰር ጀምስ ጋሎዌይ በጥናታቸው አስታውቀዋል፡፡

እንደ ጋሎዌይ ጥናት በከባቢ አየር ውስጥ የናይትሮጅን ጋዝ ጥርቅም በአስደንጋጭ ሁኔታ እየጨመረ ነው፡፡ ይህም የካርቦን ዳይኦክሳይድ ልቀት መጠን መጨመር የሚያሳስበንን ያህል ሊያሳስበን እንደሚገባ ነው ጋሎዌይ በጥናታቸው ያሳሰቡት፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ "የናይትሮጅንና ካርቦን ዳይኦክሳይድ ጋዝን ወደ አየር ሳንለቅ የዓለምን ሕዝብ የምግብና የሃይል አቅርቦት ፍላጎት እንዴት ማሳካት ይቻላል?" ሲሉ ይጠይቃሉ፡፡

በከባቢ አየር ውስጥ የናይትሮጅን መጠን 78 በመቶ ሲሆን ከዚህ በላይ ናይትሮጅን ወደ ከባቢ አየር መልቀቅ ምን ያህል አደገኛ እንደሆነ መገመት እንደሚያዳግት ጥናቱ ይጠይቃል፡፡ አክሎም የማዳበሪያ ፍጆታ መጨመር ለናይትሮጅን ጋዝ ልቀት መጨመር ምክንያት እንደሆነ ይገልፃል፡፡ በመሆኑም ከካርቦን ዳይኦክሳይድ ልቀት ጋር የተያያዙ ሥራዎች ከከባቢ አየር ለውጥ ጋር ተያይዞ እንደሚነሱት ሁሉ ከናይትሮጅን ጋዝ ልቀት መጨመር ጋር የተያያዙ ሥራዎችም እንደ ካርቦኑ ኃላፊነት እንዳለባቸው ያሳስባል፡፡

*            *            *

በእርግዝና ወቅት የሚጨነቁ ልጆቻቸው በአለርጅክ የመጠቃት እድል አላቸው

በእርግዝናቸው ወቅት የሚጨነቁ እናቶች ልጆቻቸው ከመተንፈሻ አካል ችግር /ሮቋ"ሻቂሮ/ን ጨምሮ በተለያዩ አለርጂኮች የመጠቃት እድል እንዳላቸው በጥናት ተረጋገጠ፡፡

ቢቢሲ ጥናቱን ጠቅሶ እንደዘገበው በእርግዝናቸው ወቅት ከሚጨነቁ እናቶች የሚወለዱ ህፃናት በደማቸው ውስጥ ለአለርጂክ ሊያጋልጣቸው የሚችል የኬሚካል መጠን በከፍተኛ ሁኔታ ይገኛል፡፡

ጥናቱ የተካሄደው በሃርቫርድ የህክምና ትምህርት ቤት በ387 ያህል ህፃናት ላይ ሲሆን የጥናቱን መሪ ዶ/ር ሮዛሊንድ ራይት የመተንፈሻ አካል ችግር እና የተለያዩ አለርጅኮች  ከእናቶች ጭንቀት በተጨማሪ የዘርና የተለያዩ አካባቢያዊ ተፅዕኖዎች አስተዋፅኦ ያደርጋሉ፡፡

በሃርቫርድ ጥናቱን ያካሄዱት አጥኝዎች ቡድን እንደሚሉት በእርግዝና ወቅት የሚጨነቁ እናቶች ሆዳቸው ውስጥ ያለው ፅንስ ለአለርጂክ የሚጋለጥበትን ሁኔታ እንደሚያባብሰው ገልፀው ጥናቱ በተካሄደባቸው 387 ህፃናት እትብት ለአለርጂክ ወሳኝ የሆኑ የኬሚካል ለውጦችን በመለካት ጥናት አካሂደዋል፡፡

ዶ/ር ሮዛሊንድ እንዳሉት "በእርግዝና ወቅት በሰውነት ውስጥ በሚካሄዱ ባዮሎጂካል ሆርሞን ለውጥ ሳይሆን የገንዘብ እጥረት፣ የፍቅር ግንኙነታቸውና ሌሎች ነገሮች የማያስጨንቋቸው ከሆነ በፅንሱ የሰውነት መከላከያ አቅም ላይ ለውጥ ይፈጥራል" በማለት ያብራራሉ፡፡

በእንግሊዝ የመተንፈሻ አካላት ችግር ህክምና ተቋም ዋና የህክምና አማካሪ የሆኑት ዶ/ር ማይስ ቶማስ እንደሚሉት "ጭንቀትና የመተንፈሻ አካላት ችግር ግንኙነት ከዚህ ቀደም የታወቀ ቢሆንም አሁንም ድረስ ግን ሙሉ በሙሉ ግልፅ አይደለም፡፡ ምናልባት በከፊል ጭንቀቱ በሰውነት የመከላከያ ሲስተም ላይ የሚያሳድረው ተፅዕኖ ሊሆን ይችላል" ብለዋል፡፡

*            *            *
ፀረተባይ ዲ.ኤን.ኤን ይጎዳል

በሕንድ ገበሬዎችላይ የተደረገው ጥናት እንደሚያሳየው በፀረ ተባይ የተጋለጡ ሰዎች ዲ.ኤን.ኤ.ያቸው ከጥቅም ውጭ ሊሆን ይችላል፡፡ ይህም ለካንሰር ከሚያጋልጡ ዋና ምክንያቶች አንዱ መሆኑን ጥናቱ ይጠቁማል፡፡

ሕንድ ውስጥ በፑንጃብ ግዛት የሚኖሩ ገበሬዎች ዲ ኤን ኤ መቀየር ለካንሰር ቅርብ እንዲሆኑ ማድረጉን በጥናቱ ተገል"ል፡፡

በፓቲየላ ዩኒቨርሲቲ ጥናቱን ካካሄዱት መካከል ፕሮፌሰር ሳትሊር ካውር እንዳሉት ጥናቱ እድሜን፣ አልኮል መውሰድን፣ አለመውሰድን፣ ማጨስና አለማጨስን ከግንዛቤ ውስጥ ያስገባ አይደለም፡፡ ዋናው ለዲ ኤን ኤ ከጥቅም ውጭ መሆን ምክንያት ብለው ድምዳሜ ላይ የደረሱት የፀረ ተባይ መድሃኒት መርጨትን ብቻ በማገናዘብ ነው፡፡ "በግኝቱ መሠረትም የዲ.ኤን.ኤ መቀየርን ተከትሎ በተለይ የሚቀየሩ ዲ.ኤን.ኤ.ዎች ቁጥር በጨመረ ቁጥር በካንሰር የመያዝ እድልም አብሮ ይጨምራል" ብለዋል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ በሕንድ ክሮፕ ኬር ፌዴሬሽን ባለሙያ የሆኑት ሳሊል ሲንግሃል "በአሁኑ ጊዜ ሥራ ላይ የሚውል ለካንሰር የሚያጋልጥ የፀረ ተባይ መድሃኒት የለም፡፡ ገበሬዎች በካንሰር የሚጠቁት ፀረ ተባይ መድሃኒት በመርጨታቸው ነው የሚለውም ተቀባይነት የለውም" ይላሉ፡፡

ሚስተር ሳይል እንደሚሉት ገበሬዎቹ ፀረ ተባይ የሚረጩት በየወቅቱ በተወሰኑ ጊዜያት ብቻ ነው፡፡ የርጭት ሥራውን የሚያከናውኑትም በጥንቃቄ እንደሆነ ይናገራሉ፡፡

*            *            *

 
< Prev   Next >