| ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ |
|
|
| Sunday, 13 January 2008 | |
|
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ሥራ አስፈፃሚዎች መበተናቸውን ያነበብኩት ከሪፖርተር ጋዜጣ ነው፡፡ በዶክተር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ የሚመራው ፌዴሬሽን ሥራ አስፈፃሚ እንዲበተን የተደረገው በጠቅላላ ጉባኤ ነው፡፡
በረቡዕ ታህሳስ 30 ቀን 2000 ዓ.ም ሪፖርተር ጋዜጣ አቶ ጌታቸው ገ/ማሪያም የተባሉት የፌዴሬሽኑ ሥራ አስፈፃሚ ራሳቸውን ከኃላፊነታቸው ማግለላቸውን ሳነብ ገረመኝ፡፡ ከየትኛው ፌዴሬሽን ነው ራሳቸውን ያገለሉት? ከፈረሰ፣ ታሪኩና ጉዞው ከተደመደመ ፌዴሬሽን እንዴት ራስን ከሥራ ስለማግለል ይወራል፡፡ አቶ ጌታቸው ራሳቸው ከየትኛው ፌዴሬሽን ራስዎትን አገለሉ? ተብለው ቢጠየቁ መልስ የሚሰጡ አይመስለኝም፡፡ ሌላው አቶ ጌታቸው ፃፉት በተባለው ደብዳቤ ከዚህ ቀን ጀምሮ የተወሰነው ውሳኔ አይመለከተኝም ካሉ በኋላ ከሥራ የለቀቁበትን ማመልከቻ ያስገቡበት ቀን በራሱ የተምታታ ነው፡፡ በዚሁ ጋዜጣ አቶ ወርዶፋ በቀለ፣ አቶ አርአያና አቶ አሸናፊ እጅጉ ያቀረቡት መልቀቂያ በጠቅላላ ጉባኤው ተቀባይነት ማግኘቱ አልገባኝም፡፡ ፌዴሬሽኑ ለሠራው በደልና ጥፋት ሁሉም ወገኖች መጠየቅ አለባቸው በሚባልበት በአሁኑ ወቅት የእነሱ መልቀቂያ ተቀባይነት ያገኘው ልክ አቶ ጌታቸው በጉባኤው አካሄድ ላይ ከዶክተር አሸብር ጋር እንዳልተስማሙ "ምንጮች" ገልፀዋል ተብሎ እንደተገለፀው ዓይነት ሆኖብኛል፡፡ ምናለ ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ ዓይነት ጨዋታ ባንጫወት፡፡ (ተክሌ ሲማ፣ ከቦሌ) |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |