| በኬንያ ግጭት ሊቀሰቀስ ይቻላል |
|
|
| Sunday, 13 January 2008 | |
|
የኬንያ ዋነኛ የተቃዋሚ ፓርቲ የአገሪቱን የፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ውጤት አስመልክቶ በመጪው ረቡዕ የተቃውሞ ጥሪ እንደሚያስተላልፍ የፓርቲውን ቃለ አቀባይ ጠቅሶ ቢቢሲ ዘገበ፡፡ ኦሬንጅ ዲሞክራቲክ ሙቭመንት የተባለው የተቃዋሚ ፓርቲ የፊታችን ረቡዕ የሚያደርገውን አገር አቀፍ የተቃውሞ እንቅስቃሴ አስመልክቶ ጥሪ አስተላልፏል፡፡ የተቃውሞ ጥሪው ሰሞኑን የጋናው ፕሬዚዳንት ጆን ኩፎር የጀመሩት የዕርቀ ሰላም ጥረት መስተጓጎሉን ተከትሎ መሆኑ ተገልጿል፡፡ የወቅቱ የአፍሪካ ኅብረት ሊቀመንበር ጆን ኩፋር የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ሚስተር ራይላ ኦዲንጋ ከፕሬዚዳንት ምዋይ ኪባኪ ጋር እንዲነጋገሩ ያደረጉት ጥረት አልተሳካም፡፡ የተቃዋሚ ፓርቲ ቃል አቀባይ ሳሊም ሎን ..በአገሪቱ ውስጥ ያለውን ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት መንግስት ፍላጎት አላሳየም.. ሲሉ ገልፀዋል፡፡ የአሜሪካ የአፍሪካ ጉዳዮች ተጠሪ ጃንዲ ፍሬዘርና ሌሎች ታዋቂ ሰዎች የኬንያ ግጭት በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ ጥረት እያደረጉ መሆኑ ተገልጿል፡፡ የኬንያን የምርጫ ውጤት ተከትሎ በተቀሰቀሰ ግጭት ከስድስት መቶ በላይ ሰዎች ሲገደሉ ከ70ሺ በላይ የአገሪቱ ዜጎች መፈናቀላቸው ይታወሳል፡፡ የሱዳን መንግስት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ወታደሮችን ይቅርታ ጠየቀ የሱዳን መንግስት በዳርፉር በተሰማሩት የተባበሩት መንግስታት የሰላም አስከባሪ ወታደሮች ላይ ከሁለት ወራት በፊት በደረሰው ጥቃት ተሳታፊ እንደሆነ በማመን ይቅርታ መጠየቁን የቪኦኤ ዘገባ አመለከተ፡፡ የሱዳን መንግሰት በወታደሮች ላይ የደረሰው ጥቃት በስህተት መሆኑን ገልጿል፡፡ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሱዳን አምባሳደር አብዱል መሀመድ መሀመድ ጥቃቱን የሱዳን መንግስት አለማድረሱን መናገራቸው ይታወሳል፡፡ የሱዳን ወታደር ባለስልጣናት የተመድ ወታደሮች በአካባቢው የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ ባለማሳወቃቸው የተከሰተ ስህተት መሆኑን በመጥቀስ ስህተቱ የጋራ እንደሆነ አስታውቀዋል፡፡ በተያያዘ ዜና ሱዳን ከአፍሪካ ውጪ የሚመጡ ወታደሮችን እንደማትቀበል ማስታወቋን ተከትሎ ስዊዲንና ኖርዌ ወታደራቸውን ለመላክ የነበራቸውን እቅድ ሰርዘዋል፡፡ በሞዛምቢክ በተከሰተ የጎርፍ አደጋ 45ሺ ሰዎች ተፈናቀሉ በሞዛምቢክ በዛምቤዚ ሸለቆ በተከሰተ የጎርፍ አደጋ ከ45ሺ በላይ ሰዎች መፈናቀላቸውን የአገሪቱን ባለስልጣናት በመጥቀስ ቢቢሲ ዘገበ፡፡ የአገሪቱ ባለስልጣናት በጥቂት ሳምንታት ጊዜ ውስጥ ከአንድ መቶ እስከ ሁለት መቶ ሺ ሰዎች በጎርፍ አደጋ ሊጠቁ እንደሚችሉ አሳውቀዋል፡፡ ሞዛምቢክ በተደጋጋሚ የጎርፍ አደጋ መጠቃቷ ይታወሳል፡፡ የሞዛምቢክ ወንዝ ሞልቶ ከመስመር መውጣቱን የመገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል፡፡ የደቡብ አፍሪካ የፖሊስ ሀይል አዛዥ በሙስና ወንጀል ተከሰሱ የደቡብ አፍረካ ፖሊስ አዛዥ ጃኪ ሰለቢ በሙስና ወንጀልና ፍትህ በማዛባት ክስ እንደሚመሰረትባቸው የሀገሪቱ አቃቤ ሕግ አስታወቀ፡፡ የሀገሪቱ የአቃቤ ሕግ ባለሥልጣን፣ ሚስተር ጃኪ በሙስና ወንጀል እንዲሁም በወንጀል ድርጊቶች ዙሪያ እጃቸው እንዳለበት በመጥቀስ ክስ እንደሚመሰረትባቸው ገል..ል፡፡ የሚስተር ጃኪ የቅርብ ወዳጅ እንደሆኑ የሚነገርላቸው ፕሬዚዳንት ታቦ ሞቤኪ በአዛዡ ላይ የቀረበውን ውንጀላ ተቃውመዋል፡፡ የተቋዋሚ ፓርቲ አባላት አዛዡ ስልጣናቸውን እንዲለቁ መጠየቃቸውን የቢቢሲ ዘገባ አመልክቷል፡፡ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |