| በፓኪስታን የዴንማርክ ኤምባሲ... |
|
|
| Wednesday, 04 June 2008 | |
|
በፓኪስታን የዴንማርክ ኤምባሲ ላይ የቦምብ ጥቃት ደረሰ
በፓኪስታን ዋና ከተማ በዴንማርክ ኤምባሲ አቅራቢያ በደረሰ ፍንዳታ ሰዎች መሞታቸውንና ሰላሳ ሰዎች ላይ ከፍተኛ አደጋ መድረሱን ቢቢሲ ዘገበ፡፡ በዴንማርክ ዜጐች ላይ ምንም ጉዳት ያልደረሰ ሲሆን ከሞቱት ውስጥ ሦስቱ የኤምባሲው ሠራተኞች መሆናቸው ታውቋል፡፡ ፍንዳታው የዴንማርክን ፖሊሲ የሚቀይር አይደለም ሲሉ የዴንማርክ ጠቅላይ ሚኒስቴር አንደርስ ፎግ ተናግረዋል፡፡ በአገሪቱ ሰሜን ምሥራቅ ክፍል ያለውን ጦርነት ለማብረድ የፓኪስታኑ ምርጥ የጦር መሪ ባይቱላህ ሜህሱድ ከባለሥልጣናቱ ጋር እየተወያየ ባለበት ወቅት የተከሰተውን ይህንን ፍንዳታ ማን እንዳደረሰው የታወቀ ነገር የለም፡፡ በሶሪያ የኒዩክለር ፍተሻ ሊደረግ ነው የዓለም አቀፍ የአውቶሚክ ሃይል ወኪል በሶሪያ ከሰኔ 18 እስከ 20 የኒዩክለር ተቋም ፍተሻ ያደርጋል ሲል ቢቢሲ ዘገበ፡፡ ለሰላም ጥቅም የሌለው ግንባታ ነው በማለት አሜሪካ ለሶሪያ የኒዩክለር ግንባታ ድጋፍ የምታደርገውን ሰሜን ኮሪያን ወንጅላለች፡፡ ሶሪያ በበኩሏ ምንም ዓይነት የኒዩክለር ግንባታ የለኝም በማለት በተደጋጋሚ ውንጀላውን አልቀበልም ብላለች፡፡ እስራኤል በ2007 ያፈነዳችው ክልል በጥቅም ላይ ያልዋሉ በርካታ የጦር መሣሪያዎችንና ግንባታዎችን የያዘ ነው ሲሉ ባለስልጣናቱ የተናገሩ ሲሆን ግንባታው ግን ፍንዳታው ከመድረሱ በፊት መቆሙን ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡ የዓለም አቀፍ አውቶሚክ ሃይል ወኪል ዋና ዳይሬክተር ሞሐመድ ኤልባራዲ በዚህ ጉዳይ ላይ ሁሉም ሶሪያዊ ሊተባበር ይገባዋል ብለዋል፡፡ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |