| ለድሬ አስቸኳይ መፍትሄ |
|
| Sunday, 13 January 2008 | |
|
በሪፖርተር ጋዜጣ በልናገር ገጽ ረቡዕ ታህሳስ 30/2000 "ድሬዳዋስ?" በሚል ርዕስ የወጣውን ፅሑፍ አንብቤያለሁ፡፡ በፅሑፉ ላይ የተካተቱ ሐቆች ጥያቄን የሚጭሩ ናቸው፡፡ በሚወራና በሚሠራው መካከል ያለውን ክፍተት ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው፡፡ ፅሑፉ መንግሥትንም የሚያሳስብ ነው፡፡ ከወዲሁ ሳይቃጠል በቅጠል መፍትሄ የሚበጅለት ጉዳይ ነው፡፡ የድሬዳዋ ተደራራቢ ችግሮች አፋጣኝ ምላሽ የሚሹ ናቸው፡፡ በሁሉም የአገሪቱ ክልል ባሉ ከተሞች ያሉ ችግሮች ቀላል ናቸው ማለት ባይቻልም የድሬዳዋ ግን መሠረታዊ ናቸው፡፡ የኦሮሚያና የሶማሌ ክልሎች የይገባናል ጥያቄ ያስከተለው አለመግባባት እስከአሁን ባለመፈታቱ፣ ከተማይቱ ሌሎች ከተሞች ያገኙት ጥቅምና የመሠረተ ልማት አላገኘችም፡፡ በተጨማሪም እስከ አሁን ድንበሯ በውል አለመታወቁ ሌላ ችግር ነው፡፡ በችግር ላይ ችግር እየተደራረበ ለመፍታት እንቅፋት ከመሆኑ በፊት "የድሬ ነገር" አስቸኳይ መፍትሔ ሊሰጠው ይገባል፡፡ (ተስፋዬ በየነ፣ ከመሿለኪያ) |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |