Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
Jul 06th
Home arrow Sections arrow የምስራቅ ሱዳን ግንባር ልዑካን...
የምስራቅ ሱዳን ግንባር ልዑካን... Print E-mail
Sunday, 13 January 2008

የምስራቅ ሱዳን ግንባር ልዑካን ከኘሬዚዳንት ኢሳያስ ጋር ተወያዩ

የኤርትራ ኘሬዚዳንት ከዚህ ቀደም ኤርትራ ስትሸመግልበት የነበረውን ስምምነት ለማፅደቅ ከቀድሞ የምሥራቅ ሱዳን አማፅያን መሪ ጋር ውይይት አደረጉ፡፡

ረቡዕ እለት የሱዳን ኘሬዚደንሻል አማካሪ በሆኑት ሙሳ ሞሀመድ አህመድ ከሚመራው የምስራቅ ሱዳን ግንባር ልዑካን ጋር የተደረገው ውይይት ሁለቱ ፓርቲዎች ጥቅምት አሥራ አራት 2ዐዐ7 ላይ የተደረገው የምስራቅ ሱዳን የሠላም ስምምነት ተግባራዊነት ላይ መነጋገራቸውንና ሁለቱም ፓርቲዎች ስምምነቱን ተፈፃሚ ለማድረግ ቁርጠኝነት ማሳየታቸውን ሻቢትን በመጥቀስ ሱን ትሪቢውን ዘግቧል፡፡

ከካርቱም መንግሥት ጋር በስምምነቱ ተግባራዊነት ላይ በቀጣይነት እንደምትነጋገር ኤርትራ ያስታወቀች ሲሆን የምስራቅ ሱዳን የቀድሞ አማፅያን ግንባር አንድነትን እንዲጠብቁ ጥሪ አስተላልፋለች፡፡

"ስምምነቱ የሚመለከታቸው እያንዳንዱ አካላትን ማጠናከር ለስምምነቱ ተግባራዊነት አስተዋፅኦ ይኖረዋል፡፡ የኤርትራና የሱዳን መንግሥታት እንዲሁም የሚመለከታቸው አካላት ለተፈፃሚነቱ የበኩላቸውን አስተዋፅኦ ማድረግ ይኖርባቸዋል" ብለዋል፡፡

የምስራቅ ሱዳን ግንባር ልዑካን አስመራ የደረሱት ከኤርትራ መንግሥትና ከገዢው የህግዴፍ በተደረገላቸው ጥሪ መሠረት ነው፡፡

 
< Prev   Next >