| የሶማልያ ፓርላማ አዲሱን ካቤኔ አፀደቀ |
|
|
| Sunday, 13 January 2008 | |
|
የሶማልያ ፌዴራላዊ የሽግግር ፓርላማ ህግ አውጪዎች በቅርቡ አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስቴር ኑር አዴ ሁሴን ሀሰን ያቋቋሙትን አዲስ ካቢኔ ማፅደቁ ጋረው ኦንላይን የተባለው ድረ ገፅ ዘገበ፡፡
በባይደዋ ካቢኔውን ለማፅደቅ የተገኙት የምክር ቤት አባላት ቁጥር 230 ነበር፡፡ ከነዚህ ውስጥ በአብላጫ ድምፅ ማለትም 223 የምክር ቤቱ አባላት አዲሱን ካቢኔ አፅድቀውታል፡፡ አምስት የምክር ቤቱ አባላት ካቢኔውን የተቃወሙት ሲሆን 2ቱ ደግሞ ድምፀ ተአቅቦ ማድረጋቸው ምንጮችን ጠቅሶ ድረ ገፁ ገልጿል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ኑር አዴ ከካቤኔው ማፅደቅ በኋላ የመንግሥታቸው ፖሊሲ በብሄራዊ ደህንነት፣ ዕርቅና ለዕርዳታ ሰጪ ድርጅቶች መተባበር በተመለከተ ንግግር ለምክር ቤቱ አቅርበዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ኑር አዴ የመሠረቱት አዲሱ የሶማልያ ካቤኔ 18 አባላት ያቀፈ ሲሆን፣ የሽግግር መንግሥቱ እ.ኤ.አ ከ2ዐዐ4 ጀምሮ እስከ አሁን 31 አባላት ያቀፈ ካቢኔ ነበረው፡፡ አዲሱ ካቢኔ ከሽግግር መንግሥቱ ወጪም አካትቷል፡፡ አዲሱ የኑር አዴ መንግሥት አንዳንድ ተግባራት እያከናወነ ይገኛል፡፡ ከነዚህ ውስጥ የአገራቱን ደህንነት በተመለከተ፣ በመላ አገሪቱ የፌዴራል ስርዓት መመስረትና አገሪቱን ለመጪው ዓመት ዲሞክራሲያዊ ምርጫ ማዘጋጀት የመሳሰሉ ተግባራት እየተከናወኑ ነው፡፡ በተመሳሳይ የሶማልያ ኘሬዚዳንት አብዱላሂ የሱፍ ጤንነታቸው በደህና ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |