Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
Jul 06th
Home arrow Sections arrow "ረቂቅ የፕሬስ ሕጉ ለሚዲያ ነፃነት...
"ረቂቅ የፕሬስ ሕጉ ለሚዲያ ነፃነት... Print E-mail
Sunday, 13 January 2008

"ረቂቅ የፕሬስ ሕጉ ለሚዲያ ነፃነት ዋስትና ለመስጠት ብቁ አይደለም"
ሚ/ር ሙክላኒ ዲምባ
የኦፕን ዲሞክራሲ አድቫይስ ሴንተር ምክትል ዋና ኤክስኪዩቲቭ ኦፊሰርና ዓለም አቀፍ የመረጃ ነፃነት ሕግ ባለሙያ

ሚ/ር ሙክላኒ ዲምባ በመረጃ ነፃነት ሕጎች ዓለም አቀፍ ኤክስፐርት ናቸው፡፡ ሚ/ር ዲምባ "ኦፕን ዲሞክራሲ አድቫይስ ሴንተር" የሚባለው የደቡብ አፍሪካ የሕግ ምርምር ተቋም ምክትል ዋና ኤክስኪዩቲቭ ኦፊሰርም ናቸው፡፡

ሚ/ር ዲምባ በደቡብ አፍሪካ ብቻ ሳይሆን በሞዛምቢክ፣ ማላዊ፣ ታንዛኒያ፣ ናይጄሪያ፣ ጋና እና ኬንያ በመረጃ ነፃነት ሕጎች ላይ የሰሩ ሲሆን በዚሁ ርዕስ ላይ በኢንዶኔዥያ፣ ፊሊፒንስና ታይላንድ በተጋባዥነት የጥናት ወረቀቶች አቅርበዋል፡፡

ሚ/ር ዲምባ ለተለያዩ ዓለም አቀፍ የልማት ድርጅቶች ጥናቶች ያካሄዱ ሲሆን ከእነዚህ መካከል በታንዛንያ የመረጃ ነፃነት ሕግና ኮሙኒኬሽን ላይ ያከናወኑት ጥናት ተጠቃሽ ነው፡፡

ሚ/ር ዲምባ በ14 አገሮች የመረጃ ነፃነት ሕጎችን ቁጥጥር አስመልክቶ "ኦፕን ሶሳይቲ ጀስቲስ ኢንሾቲቭ" ላካሄደው ጥናት አስተባባሪ በመሆንም ሰርተዋል፡፡

ሚ/ር ዲምባ በሳለፍነው ሳምንት ከኢትዮጵያው ረቂቅ የመገናኛ ብዙሃንና መረጃ ነፃነት ሕግ ጋር የተያያዘ ተግባር ለማከናወን አዲስ አበባ በተገኙበት ወቅት ስለረቂቅ ሕጉ በአጠቃላይም ስለአፍሪካ መገናኛ ብዙሃን ሁኔታ አነጋግረናቸዋል፡፡

በአፍሪካ መንግሥታትና በሚዲያ መካከል ያለው ግንኙነት ጥሩ የሚባል አይደለም፡፡ በአፍሪካ በጣም ፈጣንና ለውጥ ለማምጣት የሚችል ሚዲያ ያለባቸው ሀገሮች በጣም ጥቂት ናቸው፡፡በብዙ ሀገሮች ሁልጊዜም በመንግሥትና በሚዲያ መካከል ውጥረት አለ፡፡ በአንዳንድ አገሮች ውጥረቱ ከልክ ያላለፈና ለመስራት አስቸጋሪ ያልሆነ ነው፡፡ መንግሥት ሚዲያ መንግሥትን አስመልክቶ በሚያወጣቸው  ዘገባዎች ደስተኛ ላይሆን ይችላል፡፡ በደቡብ አፍሪካ ያለው ሁኔታ ለምሳሌ እንዲህ ነው፡፡ በመንግሥትና በሚዲያ መካከል አለመግባባት ሊኖር ይችላል፡፡ ነገር ግን አለመግባባቱ የግድ ሚዲያው ስራውን እንዳይሰራ የሚጨቁን መሆን የለበትም፡፡

በሌላ ፅንፍ ይኸው ውጥረት የከፋ ወንጀል የሚያስከትልና በሚዲያ ላይ አፈና ለመፈፀም የሚዳርግ ይሆናል፡፡ እንዳለመታደል ሆኖ አሁንም ብዙ የአፍሪካ ሀገራት ሕጎች መገናኛ ብዙኃንን ለማፈራረስ በመንግሥት መጠቀሚያ የሚሆኑበት ሁኔታ አለ፡፡ ስለመንግሥት ጥሩ ያልሆነ ዘገባ አውጥተዋል የሚባሉ ጋዜጠኞች የሚታሰሩበት ሁኔታም አለ፡፡

እንደ ..ሪፖርተርስ ዊዝአውት ቦርደርስ፣ በእኛ ሁኔታ ደግሞ የደቡባዊ አፍሪካ ሀገሮች ሚዲያ ተቋም እንዲሁም ዓለም አቀፍ የንግግር ነፃነት የመሳሰሉ አለም አቀፍ ተቋማት የሚያወጧቸውን ሪፖርቶች ስናይ በአፍሪካ በርካታ ጋዜጠኞች ስራቸውን ስለሰሩ ብቻ ይታሰራሉ፡፡ በአንዳንድ አጋጣሚዎች እስከ መገደልም ይደርሳሉ፡፡ አንዳንድ የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት በዚህ ተግባር ይታወቃሉ፡፡

ሚዲያ በዲሞክራሲ ግንባታ ሂደት ዋነኛ ሚና ለመጫወት የሚችል ቢሆንም እንዳለመታደል በብዙ ሀገሮች እንደ ጥሩ አጋር አይታይም፡፡ በብዙ መልኩ ከጀርባ ያላቸው ፍላጎት ምንድነው በሚለው ላይ በጥርጣሬ ይታያሉ፡፡ በዚህ ሂደት ሚዲያ እንደ ዋናና ጠቃሚ ባለድርሻ እንዲታይ ለማድረግ ብዙ ይቀረናል፡፡
 
የኢትዮጵያ የመረጃ ነፃነት ረቂቅ ሕግ አስገራሚ ሰነድ ነው፡፡ በሁለት ምክንያቶች አስገራሚ ሊባል ይችላል፡፡ የመጀመሪያው ጉዳይ የፕሬስ ሕግንና የመረጃ ነፃነት ሕግን አንድ ላይ መጨፍለቁ ነው፡፡ በደቡብ አፍሪካ ያለን የመረጃ ነፃነት ሕግ ብቻ ነው፡፡ ይህ ሕግ ለማናቸውም ሰው የመረጃ ማግኘት መብትን ማጎናፀፍን ዓላማው አድርጎ የወጣ ነው፡፡ በኢትዮጵያው ረቂቅ ሕግ ይህ ነገር ከፕሬስ ሕግ ጋር ተቀላቅሏል፡፡ ሁለቱን ማቀላቀሉ የሚመከር ነው ለማለት እቸገራለሁ፡፡ ምክንያቱም መረጃ የማግኘት መብት ለሚዲያው ብቻ የተሰጠ መብት አድርጎ የሚያይ ስለሚመስል ነው፡፡ እውነቱ ግን ይህ አይደለም፡፡ የመረጃ ማግኘት መብት ዘርፈ ብዙ ነው፡፡ ሰዎች መብቱን ለልዩ ልዩ ጥቅም ሊገለገሉበት ይችላሉ፡፡ ከእነኝህም መካከል ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፍትህን ለማስፋፋት፣ ድህነት፣ ሙስናና የልማት እጦት ባለባቸው ሁሉ እነኚህን ለመዋጋት ሊጠቀሙበት ይችላሉ፡፡ መገናኛ ብዙሃን አንድ ባለድርሻ ቢሆንም ሌሎችም አካላት በአጠቃላይ ዜጎች መረጃ የማግኘት መብት ይመለከታቸዋል፡፡

ሁለተኛው ልዩነት፣ በአጠቃላይ ረቂቅ ሕጉ ደህና የሚባል የመረጃ ነፃነት ሕግ መሆኑ ነው፡፡ በመረጃ ነፃነት ሕግ ሊዳሰሱ የሚገቡ ነገሮችን በመጠኑ ለመዳሰስ የሞከረ ነው፡፡ በዓለም አቀፍ መለኪያዎች መሰረት መረጃ ማግኘት መብት መሆኑን አስቀምጧል፡፡ ይህ መብት በተወሰነ መልኩ ሊገደብ እንደሚችልም አሳይቷል፡፡ የእንባ ጠባቂ ተቋም የመቆጣጠር፣ የማስፋፋትና የማስተማር ሚና እንዲኖረው በሕጉ መቀመጡም በጎ ጎኑ ነው፡፡ ነገር ግን ከዚህ በተሻለ መልኩ ሊረቀቅ ይችል ነበር፡፡ የመረጃ ነፃነት መብትን በተመለከተ አንድ ሕግ ሊኖረው የሚገባውን ዝቅተኛ መመዘኛ ያሟላ ቢሆንም የበለጠ በተሻለ መልኩ ሊወጣ ይችል ነበር፡፡

የተሻለ እንዲሆን ደግሞ አንዳንድ ጉዳዮች ሊሻሻሉ ይገባል፡፡ ለምሳሌ ለመረጃ ክልከላ ሰፊ ነበር የሚከፍቱ አንዳንድ ድንጋጌዎች አሉ፡፡ አንድ የመንግሥት የሥራ ሃላፊ የአንድን ሰነድ መኖር አለመኖር በተመለከተ መረጃ/ማረጋገጫ እንዲሰጥ ሲጠየቅ የመከልከል መብት እንዲኖረው ተደርጎ ተቀምጧል፡፡ በረቂቁ በአራት ሰፋፊ ምክንያቶች ይህ ሁኔታ ሊፈጠር እንደሚችል ተገል..ል፡፡ ይህ በጣም በዝቷል፡፡ እነኝህ ክልከላዎች ደግሞ በመንግሥት አለም አቀፍ ግንኙነት፣ ደህንነት፣ ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ወዘተ ባሉት ላይ መረጃ እንዳይሰጥ የሚያግዱ ናቸው፡፡ እነኝህ ሰፋፊ የመከልከያ ምክንያቶች ጠበብ ያሉ ሊሆኑ ይገባ ነበር፡፡

ሌላው አሳሳቢ ጉዳይ ረቂቅ ሕጉ በብዙ አጋጣሚዎች የባለሥልጣኖችን ውሳኔ ፍርድ ቤቶች በይግባኝ እንዳይመለከቱ መደንገጉ ነው፡፡ ኃላፊዎች መረጃ ሲከለክሉ የሚጠየቁበት አሰራር ተጠያቂነትንም ከማስፈን አንፃር አስፈላጊ ነው፡፡ አንድ ሰው በሕግ የተጎናፀፈውን መረጃ የማግኘት መብት ሲነፈግ አቤት የሚልበት ቦታ የግድ መኖር አለበት፡፡ በረቂቅ ሕጉ ግን በአንዳንድ ሁኔታዎች ይግባኝ ማለት የማይቻል መሆኑ አሳሳቢ ጉዳይ ነው፡፡

ረቂቅ ሕጉን በተመለከተ የማየው ችግር የህገመንግሥቱን አንቀፅ 29 እና ዓለም ዐቀፍን የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች አንቀፅ 19 አቀላቅሏል፡፡ ከላይ ለመግለፅ እንደሞከርኩት ሕጉ ከመረጃ ነፃነት አንፃር ዝቅተኛ የሚባሉ መለኪያዎችን አሟልቷል ሊባል ይችላል፡፡ ሃሳብን በነፃ ከመግለፅ መብት አንፃር ግን አስተያየት ለመስጠት እንኳን አያስችልም፡፡ ምክንያቱም የንግግር ነፃነት መብት በረቂቁ በግልፅ በተለየ ክፍል አልተቀመጠም፡፡ ይህ ሕግ በፕሬስ ነፃነት በኩል ለሚዲያ ነፃነት ዋስትና በመስጠት በኩል ብቁ አይደለም፡፡ 

ይህ ዓይነቱ ድንጋጌ ለምን እንዳስፈለገ ይገባኛል፡፡ አንድ ሕግ ሲወጣ ከወጣበት ቀን ማግስት አንስቶ ተግባር ላይ ሊውል አይችልም፡፡ ሕጉ የሚፈፀምበትን ሁኔታ የሚያመቻቹ ቅድመ ሁኔታዎች ሊሟሉ የግድ ነው፡፡ አፈፃፀሙን በተመለከተ በሚገባ ካልታቀደና ዝግጅት ካልተደረገ የሕጉ ተፈፃሚነት አጠያያቂ ይሆናል፡፡ የጊዜ ገደብ ማስቀመጡ ሕጉን የሚጠቀሙበት ሰዎች/ አጠቃላይ ሕዝቡ ስለሕጉ በቂ ዕውቀት እንዲኖራቸውም ያደርጋል፡፡ በሌሎች የዓለም ሀገራትም ጊዜ ገደብ የማስቀመጡ የተለመደ ነው፡፡ የእንግሊዝ የመረጃ ነፃነት ሕግ ተግባር ላይ የዋለው በ5 ዓመት የጊዜ ገደብ ውስጥ ነው፡፡ በደቡብ አፍሪካ ጊዜ ገደብ ሳይቀመጥለት እንደወጣ ተግባራዊ እንዲሆን የተደረገ ሲሆን ሰዎች ሕጉን ለማስፈፀም ዝግጁ ያልነበሩ በመሆኑ አፈፃፀም ላይ ብዙ ችግሮች ተከስተው ነበር፡፡ አንዳንዶቹ የሥራ ኃላፊዎች እንዲያውም መረጃ የማግኘት መብታችን በሕጉ ተጠብቋልና መረጃ ስጡን ሲባሉ "እርሱ ደግሞ ምንድነው?" ይሉ ነበር፡፡

የኢትዮጵያው ረቂቅ ሕግ መፈፀሚያ ገደብ ያስቀመጠው ከዚህ የተነሳ ይመስለኛል፡፡ ነገር ግን በነዚህ ሁለት ዓመታት ምን ምን ቅድመ ሁኔታዎች መሟላት አለባቸው? የሚለው በጊዜ ገደብ ተከፋፍሎ በሕጉ ሊቀመጥ በተገባ ነበር፡፡ በስድስት ወር እነኝህ ጉዳዮች መሟላት አለባቸው፤ በስምንት ወር ይህ መደረግ አለበት ተብሎ ሊቀመጥ ይገባል፡፡ ከዚህ ይልቅ አሳሳቢው ጉዳይ "የሀገሪቱ ፓርላማ ይህንን ጊዜ ሊያራዝም ይችላል" የሚል ሐረግ በሕጉ ውስጥ መካተቱ ነው፡፡ ይህ የሚመከር ነገር አይደለም፡፡ 

በደቡብ አፍሪካ ከሚዲያ ሥራ ጋር በተገናኘ የሚደነገጉ ማናቸውም ዓይነት ሕጎች የግልና የመንግሥት ብለው አይለዩም፡፡ የሚዲያ ባለቤትነትን የሚመለከቱ አንቀፆችን ሳይጨምር ማለት ነው፡፡ በዚህ ረገድ በግል ባለቤትነት የሚያዙ ሚዲያዎች ማሟላት የሚገባቸውን፣ ሊሰሩባቸው የሚገቡ ሁኔታዎችን በተመለከተ የተቀመጡ ድንጋጌዎች አሉ፡፡ በኢትዮጵያ ረቂቅ ሕግ ውስጥ ግን በምዝገባም ይሁን በሌላ መልኩ ቀጥታ የመንግሥት ቁጥጥርን በመገናኛ ብዙሃን ላይ የሚያሰፍን ሁኔታ መኖሩ አሳሳቢ ነው፡፡

ሚዲያ ከቀጥተኛ የመንግሥት ጣልቃ ገብነት ነፃ የሆነ ለሥራ አመቺ ሁኔታ ሊመቻችለት የግድ ነው፡፡ መገናኛ ብዙኃን ለሌሎች ዜጎች ጭምር በሚሰሩ የሀገሪቱ ሕጎች እስከተገዛ ድረስ መንግሥት ለነሱ ብሎ የሚያወጣቸው ሕጎች ማነቆ ሊሆኑባቸው አይገባም፡፡ የጋዜጠኝነት ሥነ ምግባርንና ሙያን ያከበረ አሰራርን ለማስፈን ጋዜጠኛው ራሱን በራሱ የሚቆጣጠርበት እድል ሊኖር ይገባል፡፡ ሚዲያው ራሱን በራሱ እያስተዳደረ እንደዚህ ዓይነት የጋዜጠኛውን ሥራ የሚያስተጓጉሉ ሕጎች አላስፈላጊ መሆናቸውን ሊያሳይ ይገባል፡፡ እዚህ ሀገር ሚዲያ ካውንስል እንደሌላችሁ ሰምቻለሁ፡፡ ቢኖር ኖሮ ይህንን ዓይነቱን ተግባር ይፈፅም ነበር፡፡

ስለ ዲሞክራሲ ሂደት ስናወራ መንግሥት፣ ተቃዋሚ እና ሲቪል ማኅበረሰቡ አሉ፡፡ እነኝህ አካላት በመገናኛ ብዙሀን ላይ ተፅዕኖ ሊያሳርፉ አይገባም፡፡ ሚዲያ ከነኝህ ተፅዕኖ ውጪ ሊሆን ይገባል፡፡ ይህ ተግባር ላይ ሊውል የማይችል ቅዱስ ሀሳብ ሊመስል ይችላል፡፡ ነገር ግን ሚዲያ ከእነኝህ ሶስት አካላት ሚና ውጪ ሊሆን ይገባል፡፡ መንግሥት ጋዜጠኞች በይፋ ተቃዋሚ ፓርቲዎችን ሲደግፉ ካየ ባለው ሥልጣን ሁሉ እነኛን ጋዜጠኞች ከተቃዋሚዎቹ እኩል ሊዋጋቸው ይነሳል፡፡ ሚዲያ ለራሱም ክብር ሲባል ከእነኝህ አካላት ውጪ ሆኖ መንቀሳቀሱን ሊያረጋግጥ ይገባል፡፡ ሚዲያ ማስተጋባት የሚገባው በማህበረሰቡ ውስጥ ያለውን ጉዳይ ብቻ ነው፡፡ ክርክሮች፣ ውይይቶች ማህበረሰቡ ጉዳዬ ብሎ የሚያነሳቸውን ጭብጦች ማስተጋባት ይገባል፡፡ ሚዲያ የክርክሩ/ የጭብጡ አካል ሊሆን ግን አይገባም፡፡

በደቡብ አፍሪካ ጥሩ ሚዲያና በጣም ጥሩ የጋዜጠኛነት ትምህርት ቤቶች ስላሉን ዕድለኞች ነን፡፡ ከእነኝህ ውስጥ እጅግ በጣም ጥሩ ደረጃና ብቃት ያላቸው ጋዜጠኞች ይወጣሉ፡፡ በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ሳይቀር ጋዜጠኞች የሚደርስባቸውን ጫና በመቋቋም የሚጠበቅባቸው አስተዋፅዖ ለማድረግ ችለዋል፡፡ በአፓርታይድ ወቅት የነበረውን የጋዜጠኞች ሥራ በምሳሌነት መጥቀስ ይቻላል፡፡ አሁን ደቡብ አፍሪካ ያሉ ጋዜጠኞች በሙሉ የልምድ ማነስ ያለባቸው ያሉ ሊኖሩ ይችላሉ፤ ነገር ግን ጥሩ ሥልጠናና ሙያ ያላቸው ናቸው፡፡ ከዚህ ሌላ ሚዲያ ክብሩንና ደረጃውን ጠብቆ እንዲሠራ የሚያግዙ አካላት አሉ፡፡ እነኝህ ተቋማት የደቡብ አፍሪካ ኤዲተሮች ፎረም፣ ፕሬስ ካውንስል፣ የደቡባዊ አፍሪካ ሚዲያ ተቋም (የደቡብ አፍሪካ ቅርንጫፍ)፣ የደቡብ አፍሪካ ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ ተቋም ወዘተ ናቸው፡፡ በዚህም ሀገር ሚዲያው ደረጃውን የጠበቀ ሥራ እንዲሠራ ለማስቻል ሊደራጅና የሚቆጣጠር አካል እንዲኖር ሊያደርግ ይገባል፡፡

በደቡብ አፍሪካ በመንግሥት የተያዘ ጋዜጣ የለም፡፡ የመንግሥት እንቅስቃሴዎች የሚወጡት ለዚሁ ተብሎ በተቋቋመ የኮሙኒኬሽንና የህትመት አገልግሎት በኩል ነው፡፡ ይህንን ያደረጉበት ምክንያትም መንግሥት ልዩ ልዩ በጎ ተግባራት ቢያከናውንም ሚዲያው የሚያተኩረው ጉድለቶች ላይ ብቻ ሆነ ከሚል ነው፡፡ ይህ ህትመት በነፃ የሚታደል በመሆኑ ጋዜጣ ሊባል የሚችል አይደለም፡፡ ወደ ኤሌክትሮኒክስ ሚዲያ ስንመጣ መንግሥት 13 ያህል የንግድ ሬዲዮ ጣቢያዎችና ሦስት የቴሌቪዥን ጣቢያዎች አሉት፡፡ የሕዝብ ሚዲያ የምንለው ደግሞ የደቡብ አፍሪካ ብሮድካስት ኮርፖሬሽንና የሚያስተዳድራቸው ጣቢያዎችን ነው፡፡ ሆኖም ይህ ድርጅት ምን ያህል ከመንግሥት ተፅዕኖ ነፃ ነው የሚለው አጠያያቂ ነው፡፡ ምክንያቱም የኮርፖሬሽኑ የሥራ ኃላፊዎች የሚሾሙት በመንግሥት በመሆኑ ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ በጣቢያዎቻቸው የሚተላለፉ ዜናዎች ወደ ገዢው ፓርቲ ያደሉ ሲሆኑ ይታያል፡፡ አንዳንዴ እንደውም "የአስተዳዳሪዎቻቸው ድምፆች" እየተባሉ ይጠራሉ፡፡

የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ሕጉ እንዲሻሻል መቀስቀስና ጥረት ማድረግ ይገባችኋል፡፡ በተለያዩ ሰዎች ረቂቅ ሕጉ ያሉበትን ችግሮች/ ክፍተቶች በተመለከተ አስተያየት እየተሰጠ ነው፡፡ እነኝህን ችግሮች በተመለከተ ከአርቃቂዎቹ ጋር መነጋገር መቻል አለባችሁ፡፡ ከዚህ ሌላ ጉዳዩን ሚዲያ ላይ ልታወጡት ይገባል፡፡ ረቂቅ ሕጉ ውይይቶች የሚያሳየው ጉዳይ መሆኑ በሚዲያ ሊነገር ይገባል፡፡ ሕዝቡ ጉዳዩን በሚገባ እንዲያውቀው ተከታታይ ሥራዎች ሊሰሩም ግድ ነው፡፡ ይህ ሕግ እንዳይወጣ ሚዲያ ብቻውን ሊታገል አይችልም፡፡ በሚዲያና በመንግሥት መካከል ያለው ግንኙነት ብዙውን ጊዜ ጥሩ ስለማይሆን የሚዲያው ጉዳይ ብቻ ተደርጎ ከታየ መንግሥት እንደ መገደቢያ ሊጠቀምበት ይችላል፡፡ መረጃ የማግኘት መብት የሚዲያ ጉዳይ ብቻ ተደርጎ ሊታይም አይገባም፡፡ ይህ እንዲታወቅ ሚዲያው ሊሰራ ይገባል፡፡ ይህ መብት ዲሞክራሲንና ሰብዓዊ መብትን ለማረጋገጥ፣ ሙስናን ለመዋጋት ሊውል የሚችል ነው፡፡ መብቱ ዘርፈ ብዙ መሆኑ ሊታይ የግድ ነው፡፡ በሌሎች ሀገሮች ያሉ ጋዜጠኞች በዚህ ረገድ ያላቸውን ልምድም ልትመለከቱ ይገባል፡፡ 

 
< Prev   Next >