| የጓንታናሞ 9/11 አሸባሪዎች... |
|
|
| Sunday, 08 June 2008 | |
|
የጓንታናሞ 9/11 አሸባሪዎች በሞት ሊቀጡ ነው
በአልቃይዳ በሥልጣን ሦስተኛ ሰው የሆነው ካሊድ ሼክ ሞሐመድን ጨምሮ ሌሎችም የጓንታናሞ 9/11 ተከሳሾች ኩባ በተቋቋመው የአሜሪካ ችሎት ውሣኔ ከተሰጠበት በሞት እንደሚቀጡ ቢቢሲ ዘገበ፡፡ ፓኪስታን ውስጥ በ2003 በቁጥጥር ሥር የዋለው ካሊድ ሼክ ሞሐመድ ከተያዘበት ጊዜ ጀምሮ ለህዝብ ዕይታ ሲቀርብ ይህ የመጀመሪያው ነው ሲል የቢቢሲው ጋዜጠኛ ጆናታን ቤል ዘግቧል፡፡ የሞት ፍርደኛው ካሊድ ሼክ ሞሐመድ "ለያዝኩት ፖለቲካዊና ሃይማኖታዊ አቋም መሞት ለአምስት ዓመታት ስመኘው ስፈልገው የነበርኩት ነገር ነው" በማለት ፍርዱን እንደሚቀበለው ዘግቧል፡፡ ሌላው የመናዊና በአሜሪካውያኑ የመስከረም አንዱ ጥቃት አቀናባሪ የተባለው ሚስተር ባይናልሺባ እንዲሁ ለዓላማው መሞት እንደሚፈልግ የገለፀ ሲሆን በኒውዮርክ ከደረሰው ጥቃት ሌላ በሌሎች ሰላሳ የአሸባሪዎች ጥቃት ላይ እንደተሳተፈ በዘገባው ተገልጿል፡፡ * * * የነዳጅ ዋጋ ንረት በአውሮፓ ግጭት ቀሰቀሰ በመቶዎች የሚቆጠሩ አሣ አጥማጆች የአውሮፓ ህብረት መቀመጫ በሆነው ብራሰልስ የነዳጅ ዋጋን በመቃወም ሰልፍ ወጡ፡፡ በተቃውሞው የአውሮፓ ህብረት ህንፃ መስኮቶች መሰባበራቸውንና አንድ መኪና መገልበጡን የቢቢሲ ዘገባ አመልክቷል፡፡ የአውሮፓ ህብረት ለመንግሥታቱ በነዳጅ ዋጋ ላይ የገንዘብ ድጐማ ካልፈቀደ ከንግድ እንቅስቃሴ ልንወጣ እንችላለን በማለት ተቃዋሚዎቹ ስጋታቸውን ገልፀዋል፡፡ ባለፉት አምስት ዓመታት 240 በመቶ የናረውን የነዳጅ ዋጋ የሚቃወሙት የፈረንሳይ አሣ አጥማጆች የአውሮፓ ወደቦችን ከዘጉ የብሪታንያ፣ የስፔን፣ የፖርቹጋልና የጣልያን የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ጋር በመጣመር ተቃውሞአቸውን ገልፀዋል፡፡ የዋጋ ንረቱ ከሴክተሩ አቅም በላይ ስለሆነበት አዲስ የአሠራር ስርዓት እንደሚያስፈልግ በአውሮፖ ህብረት የአሣ አጥማጆች ኮሚሽነርና ዋና የፖለቲካ አማካሪ የተናገሩ ሲሆን በጣም የተበሳጩት አሣ አጥማጆች ግን ሊሰሙት የማይፈልጉት ንግግር እንደሆነ የቢቢሲው ዘጋቢ ከብራሰልስ ገልጿል፡፡ * * * ካሊፎርኒያ ድርቅ ገባ ድርቅ በካለፎርኒያ መግባቱን አገረ ገዥ አርኖልድ ሺዋዚንገር ይፋ ማድረጋቸውን አሶሽየትድ ኘሬስ ዘገበ፡፡ አገረ ገዥው እንዳሉት ባለፉት ሁለት ዓመት በካሊፎርኒያ የዝናቡ መጠን ከአማካዩ የዝናብ ፍላጎት በታች በመሆኑና የበረዶውም ቅልጠት ትንሽ በመሆኑ ድርቅ መድረሱን ለሕዝባቸው አስታውቀዋል፡፡ ሸዋዚንገር እንዳስታወቁት ከሆኑ የካሊፎርኒያ ነዋሪዎችና፣ የውሃ ክፍል ሃላፊዎች በአስቸኳይ የውሃ አጠቃቀማቸውን መቀነስ ወይም ዝናብ ካልጣለ በሚቀጥለው ዓመት የሚመጣውን ችግር ለመቋቋም መዘጋጀት አለባቸው፡፡ የካሊፎርኒያ የውሃ ሃብት መሥሪያ ቤት ከፍተኛ እጥረት ላለባቸው አካባቢዎች በአስቸኳይ ውሃ የማስተላለፍ ሥራ እንዲጀምር ሸዋዚንገር ትዕዛዝ ሰጥተዋል፡፡ * * * የአራት ሺ ኢትዮጵያውያን ፈላሻዎች ሀያኛ ሙት ዓመት በእስራኤል ተዘከረ በ1980 ወደ እስራኤል ሲጓዙ ህይወታቸው ያለፈ አራት ሺ ኢትዮጵያውያን ፈላሻዎች ሀያኛ ሙት ዓመት ሰኞ ግንቦት 25 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. በኢየሩሳለም ተዘከረ፡፡ እስራኤላዊያን ለአገራቸው ያላቸውን ፍቅር በሚገልፁበት ዓመታዊ ክብረ በዓል ላይ ኘሬዚዳንት ሺሞን ፔሬዝ የኢትዮጵያ አይሁዶች በስደት የደረሰባቸውን ችግር እና ህዝቡም የኢየሩሳሌም ተስፋ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡ ከአገራቸው ተነስተው የሱዳንን በረሃ በማቋረጥ ወደ እስራኤል ለመግባት በጉዞ ላይ የነበሩት ኢትዮጵያዊያን አይሁዶች ጀግንነታቸውና ከስደት ወደ ጽዮን ለመመለስ የከፈሉትም መስዋዕትነት ሲዘከር እንደሚኖር ኘሬዚዳንቱ ገልፀዋል፡፡ በአሁኑ ጊዜ በጦር ሰራዊቱ ውስጥ በተለያየ ሙያ የሚያገለግሉ በተለይ በአካዳሚክ፣ በባህልና ኪነ ጥበብ እንደሁም በተለይ የሃላፊነት ሥልጣኖች ላይ የሚገኙ ስደተኞች እንዳሉ ኘሬዚዳንት ፔሬዝ በበዓሉ ላይ ገልፀዋል፡፡ * * * * |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |