Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
Jul 20th
Home arrow Sections arrow የካንሰር በሽታን ለመከላከልና...
የካንሰር በሽታን ለመከላከልና... Print E-mail
Sunday, 13 January 2008

የካንሰር በሽታን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ኅብረተሰቡ በቂ ትምህርት ማግኘት አለበት

በኢትዮጵያ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተስፋፋ የመጣውን የካንሰር በሽታ ለመከላከልና ለመቆጣጠር መንግስት ከጀመረው ጥረት በተጨማሪ ኅብረተሰቡ ስለ በሽታው መንስኤና መከላከል በሚችልበት ሁኔታ በቂ ግንዛቤ እንዲኖረው አስፈላጊው ጥረት ሊደረግ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ካንሰር ሶሳይቲ አሳሰበ፡፡

በዘልማድ እንደሚነገረው ካንሰር የጥቂት ሰዎች ህመም ሳይሆን በመላው ዓለም የሰው ልጅ ህይወትን በማጥፋት የሚታወቅና በቶሎ ከታወቀም የሚድንና መከላከል የሚቻል እንደሆነ፣ በዓለም አቀፍ የካንሰር ድርጅት መረጃ መሠረት እስካሁን በዓለም ላይ በየዓመቱ ሰባት ሚሊዮን ህዝብ በካንሰር በሽታ ህይወቱን እንደሚያጣና 11 ሚሊዮን ተጨማሪ ህዝብ በበሽታው እንደሚያዝ አስታውቋል፡፡

(ኢዜአ)

ማዘጋጃ ቤቱ 13 የሥራ ኃላፊዎችን ለህግ አቀረበ

የወልቂጤ ማዘጋጃ ቤት የተጣለባቸውን ኃላፊነት ወደ ጎን በመተው የግል ጥቅማቸውን ሲያሳድዱ ነበር ያላቸውን 13 ተጠርጣሪ የሥራ ኃላፊዎች ለህግ መቅረባቸውን የከተማው አስተዳደር ገለፁ፡፡

የሥራ ኃላፊዎቹ ለሕግ እንዲቀርቡ የተደረገው የከተማው ነዋሪዎች ባቀረቡት አቤቱታ መሰረት በተደረገው ማጣራት ስልጣናቸውን ተጠቅመው በዘመድ ስም የከተማ ቦታ፣ በጨረታ ላይ ያለ አግባብ መወሰናቸውና የገንዘብ ጉድለት በማድረሳቸው መሆኑን አብራርቷል፡፡

(አዲስ ዘመን ታህሳስ 30 ቀን 2000 ዓ.ም)

ለስድስት ነጥብ ሁለት ሚሊዮን እናቶች የመንጋጋ ቆልፍ በሽታ መከላከያ ክትባት ይሰጣል

በዘንድሮው ዓመት በመውለድ ክልል ለሚገኙ ስድስት ነጥብ ሁለት ሚሊዮን እናቶች የመንጋጋ ቆልፍ በሽታ መከላከያ ክትባት የሚሰጥ መሆኑን የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ የአገሪቱን የሃይጂንና አካባቢ ጤና አገልግሎትን ወደ 70 በመቶ ለማሳደግ እቅድ መያዙንም ገልጿል፡፡

አገልግሎቱ ከሚሰጣቸው እናቶች ውስጥ 1 ነጥብ 8 ሚሊዮን የሚሆኑት የቲታነስ (መንጋጋ ቆልፍ) ክትባት እንደሚያገኙ፣ 4 ነጥብ 4 ሚሊዮን የሚሆኑና በመውለድ ዕድሜ ክልል ያሉ እናቶችም ክትባቱን በዘመቻ እንዲያገኙ ይደረጋል ብሏል፡፡

(ዘ ኢትዮጵያን ሔራልድ ጃንዋሪ 9 ቀን 2008..)

ማኅበራቱ 50ሺ ኩንታል እህል በተመጣጣኝ ዋጋ ሊያቀርቡ ነው

በሀዲያ ዞን በሚገኙ አሥር ወረዳዎች በግብይት የተሳተፉ ማኅበራቱ ከ10 ሚሊዮን ብር በላይ 50ሺ ኩንታል የእህል ምርት ከአርሶ አደሩ ገዝተው በተመጣጣኝ ዋጋ ለገበያ ለማቅረብ እንቅስቃሴ መጀመራቸውን የዞኑ የኅብረት ሥራ ሥራ ጽህፈት ቤት ገለፀ፡፡

ማኅበራቱ በዞኑ ካለፈው ወር ጀምሮ የሰብል ግዢ እያካሄዱ ያሉት በሉቻ የሀዲያ ገበሬዎች ኅብረት ሥራ ዩኒየን ሥር የተደራጁ 38 ማኅበራት ሲሆኑ፣ ግዢውን የሚፈጽሙት በራሳቸው ካፒታልና ከክልሉ የገጠርና የፋይናንስ አገልግሎት ፈንድ ባገኙት ብድር መሆኑን፣ ስንዴ፣ በቆሎ፣ ጤፍ፣ ባቄላና አተርን በዋናነት እየገዙ መሆናቸውን፣ እንዲሁም የአፈር ማዳበሪያና ምርጥ ዘር ለአባሎቻቸው በማከፋፈል አበረታች እንቅስቃሴ እያደረጉ በመሆናቸውን አስታውቋል፡፡

(ዋኢማ)

 
< Prev   Next >