| ኢትዮጵያና ጃፓን የ7 ነጥብ 4 ሚሊዮን... |
|
|
| Wednesday, 11 June 2008 | |
|
ኢትዮጵያና ጃፓን የ7 ነጥብ 4 ሚሊዮን ዶላር ስምምነት ተፈራረሙ
በኢትዮጵያና በጃፓን መካከል የ7 ነጥብ 4 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር እርዳታ ተፈራረሙ፡፡ እርዳታው በትግራይ ክልል የገጠር መጠጥ ውሃ ኘሮጀክትን በገንዘብ ለመደገፍና ለብሔራዊ ሙዚየም ለሆሚኒንድ ቅሬታ አካል ምርምር የሚውሉ መሳሪያዎችን ለማሟላት መሆኑ ተገልጿል፡፡ (አዲስ ዘመን ሰኔ 3 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም.) ለቤት እንስሳት ክትባትና ህክምና ተሰጠ በድሬዳው ጊዜያዊ አስተዳደር በዚህ ዓመት ከ25ዐ ሺ ለሚበልጡ የቤት እንስሳት ክትባትና ሕክምና መስጠቱን የአስተዳደሩ ግብርናና ገጠር ልማት ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡ ከ1 ሺ 6ዐዐ በላይ እንስሳት ገዝቶ ማከፋፈሉንም ገልጿል፡፡ ፅህፈት ቤቱ 3ዐዐ ሺ ለሚጠጉ የቤት እንስሳት ክትባትና ሕክምና ለመስጠት አቅዶ ከ25ዐ ሺ ለሚበልጡ መስጠቱን፣ በዝናብ እጥረት ምክንያት የደረሰውን የዝናብ እጥረት ለማቃለል ከምግብ ዋስትናና ከመንግሥት በተመደበ 27ዐ ሺ ብር የእንስሳት መኖ ገዝቶ ለ12 ቀበሌ ገበሬ ማህበራት ማከፋፈሉን ገልጿል፡፡ (ኢዜአ) በድንገተኛ አደጋዎች የ8ዐ ሰዎች ህይወት አልፏል በተያዘው በጀት ዓመት ዘጠኝ ወራት ጊዜ ውስጥ በአዲስ አበባ ከተማ በተከሰቱ የተለያዩ ድንገተኛ አደጋዎች የ8ዐ ህይወት ማለፉን ከ29 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ንብረት መውደሙን የከተማው እሳትና ድንገተኛ አደጋዎች አገልግሎት አስታወቀ፡፡ በሰውና በንብረት ላይ የደረሰው ከሐምሌ 1 ቀን 1999 ዓ.ም. እስከ መጋቢት 3ዐ ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. በመዲናዋ በተከሰቱ 385 አደጋዎች መሆኑን፣ 347ቱ የእሳት 38ቱ ደግሞ በሌላ አደጋዎች መሆኑን ገልጿል፡፡ (ኢዜአ) ማህበሩ ሁለት ሚሊዮን ቶን ዕቃ አጓጓዘ የኢትዮጵያ ንግድ መርከብ አ/ማ ሁለት ሚሊዮን ቶን የሚጠጋ ገቢና ወጭ ዕቃ ማጓጓዙን አስታወቀ፡፡ ማህበሩ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ውስጥ ያጓጓዘው እቃ ላለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ61 ከመቶ ብልጫ እንዳለው፣ ማህበሩ በቅርቡ በሥራ ላይ ያሰማራቸው ግቤና ሸበሌ የተባሉት አዳዲስ ሁለት መርከቦች ብትንና በኮንቴይነር የታሸጉ እቃዎች በመጫኑ ችግሩ መቃለሉን ገልጿል፡፡ (አዲስ ዘመን ሰኔ 2 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም.) ከ12 ሺ ኩንታል የሚበልጥ ጤፍ ተከፋፈለ በምስራቅ ጐጃም የሚገኙ የገበሬዎች ህብረት ሥራ ማህበራት ከ12 ሺ ኩንታል የሚበልጥ ጤፍ ለተጠቃሚዎች በተመጣጣኝ ዋጋ ማቅረባቸውን የዞኑ የህብረት ሥራ ማህበራት ማስፋፊያ ጽህፈት ቤት ገለፁ፡፡ ዩኒዮኖቹ ከየካቲት ወር 2ዐዐዐ ጀምሮ ለከተማ ነዋሪዎች፣ ለሸማቾች የህብረት ሥራ ማህበራትና ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ያቀረቡት ጤፍ አሁን ገበያ ላይ ላለው ዋጋ ከ3ዐ ብር እስከ 1ዐዐ ብር ቅናሽ እንዳለው፣ ዩኒዬኖቹ 62 መሠረታዊና ከ722 ሺ የሚበልጥ አባላት እንዳሏቸው ገልፀዋል፡፡ (ኢዜአ) የነዳጅና የምግብ ዋጋ ማሻቀብ ለአዳጊ አገሮች ትልቅ ፈተና ሆኗል በቅርቡ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተከሰተው የነዳጅና የምግብ ዋጋ ማሻቀብ በአዳጊ አገሮች የልማት ጥረት ላይ ትልቅ ፈተና እየደቀነ መሆኑን የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትር አስታወቀ፡፡ የልማት ወደፊት የገፋ አንዳንድ አገሮች የምጣኔ ሀብት እድገት ዘገምተኛ መሆን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ በመልማት ላይ ባሉ አገሮች እድገት ላይ ከባድ ተፅእኖ እያሳረፈ መሆኑን፣ ለችግሩም አስቸኳይ መፍትሄ ማፈላለግ እንዳለባቸው ገልጿል፡፡ (ኢዜአ) |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |