| የመንግሥቱ ኃ/ማርያም ዕጣ ፈንታ . . . |
|
|
| Thursday, 12 June 2008 | |
|
የዝምባቤው ፋይናንሽያል ጋዜጣ እንደዘገበው
ከሁለት ሳምንት በፊት በኢትዮጵያ ጠቅላይ ፍ/ቤት በዘር ማጥፋት ወንጀል የሞት ቅጣት የተፈረደባቸው የቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት መንግሥቱ ኃ/ማርያም በዝምባብዌ የመቆየታቸው ሁኔታ ጥያቄ ውስጥ ገብቷል፡፡ “የኢትዮጵያ ገዳይ” (Butcher of Ethiopia) በመባል የሚታወቁት እኚህ የቀድሞ አምባገነን መሪ ስለወደፊት ዕጣ ፈንታቸው በውል የሚታወቀው የዛሬ ሁለት ሳምንት (ሰኔ 2ዐ) ዝምባብዌያን ቀጣይ ፕሬዚዳንታቸው ለመመረጥ ዳግም ድምፃቸውን ሲሰጡ ግዜ ነው፡፡ አንዳንድ የፖለቲካ ተንታኞች ለጋዜጣው በሰጡት አስተያየት የቀድሞ ፕሬዚዳንት መንግሥቱ ኃ/ማርያም በዝምባብዌ የመቆየታቸው ሁኔታ የሚወሰነው ባለፈው መጋቢት ወር ላይ በተካሄደው የአገሪቱ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ፕሬዚዳንት ሙጋቤ ንቅናቄ ለዴሞክራሲያዊ ለውጥ (MDC) መሪ በሆኑት ሞርጋን ሻንጋራይ የደረሰባቸውን ሽንፈት በድጋሚው ምርጫ መቀልበስ ከቻሉ ብቻ ነው፡፡ ተንታኞቹ እንደሚት አስተያየት ድጋሚ ምርጫው በሸንጋራይ አሸናፊነት የሚጠናቀቅ ከሆነ መሪው ከዚህ በፊት እንደተናገሩት ለአምባገነን መሪዎች የሚሰጡት አለኝታ የሌለ በመሆኑ ለቀድሞ የኢትዮጵያ ብርቱ መሪ የሚሰጡት ተስፋ የጨለመ ነው፡፡ በዝምባብዌ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ ፕሮፌሰር የሆኑት አልደርድ ማስኑንኑር ጉዳዩን አስመልክተው “የሰውየው ዕጣ ፈንታ የሚወሰነው በአገሪቱ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ውጤት እንደሚሆን ምንም ጥርጥር የለውም” ብለዋል፡፡ “የምርጫው ውጤት ለመቆየታቸው ወይም ለመባረራቸው ወሳኝ ነው” በማለት አብራርተዋል፡፡ መንግሥቱ ኃ/ማርያም በ1983 ዓ.ም በኢህአዴግ ከስልጣን ከተወገዱ ጀምሮ በፕሬዚዳንት ሙጋቤ ከለላ በዝምባብዌ በምቾት ህይወት ሲኖሩ ቆይተዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት የፕሬዚዳንት ሙጋቤን መንግሥት በመቃወም ግንባር ቀደም የሚጠቀሱ አሜሪካውያን መንግሥቱ ኃ/ማርያም ወደ ዝምባብዌ እንዲጓዙ ያመቻቹ ሰዎች እንደነበሩ ይታመናል፡፡ ለዝምባብዌ መንግሥት ቅርበት ያላቸው ምንጮች እንደሚጠቁሙት መንግሥቱ ባለፉት 17 ዓመታት በሐራሬ ከተማና በአካባቢዋ ትልቅ የእርሻ ቦታና ቤቶች አካብተው፣ ከነቤተሰቦቻቸው ጋር በዝምባብዌ መንግሥት ደህንነታቸው ተጠብቆ የተረጋጋ ህይወት ይመራሉ፡፡ የክርስትያን ኣሊያንስ ኦፍ ዝምባብዌ አስተባባሪ ኡስኒ ሲባና ምርጫው በተቃረበ ወቅት መንግሥቱ ኃ/ማርያም ዕንቅልፍ ሊያሳጡ የሚችሉ ሌሊቶች ሊሆኑ እንደሚችሉ ተናግረዋል፡፡ “ለእሳቸው የመከራ ጊዜ ነው፡፡ የተቃዋሚው ድል ለእሳቸው አደጋ አለው፤ በህይወት ዕጣ ፈንታቸው ላይ ከፍተኛ ጭንቀት ያደረባቸው ይመስለኛል፡፡ ምንአልባትም ፕሬዚዳንት ሙጋቤ ድል እንዲያደርጉ ፀሎት እያደረጉላቸው ሊሆን ይችላል” ብለዋል፡፡ ፕሮፌሰር ማስኑንጉር በበኩላቸው ..ሞርጋን ሻንጋይ የሚያሸንፉ ከሆነ መንግሥቱ ኃ/ማርያም የማይፈለጉ እንግዳ ይሆናሉ.. በማለት ግምታቸውን ሰጥተዋል፡፡ የሙጋቤ መንግሥት ግን በስልጣን እስከቆየ ድረስ መንግሥቱ ኃ/ማርያምን በመልካም እንግዳነት የማስቀመጥ ዕቅድ እንዳለው አሁንም አቋሙን አረጋግጠዋል፡፡ የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚ/ር ብራይት ማቶንጋ ይህንን አስመልክቶ፣ “በዝምባብዌ እንግዳ ሆነው ቆይተዋል፡፡ ለወደፊቱም በዝምባብዌ ይኖራሉ፣ እንደ በፊቱም ደህንነታቸውን እንጠብቃለን” ብለዋል፡፡ የዋነኛው ተቃዋሚው (MDC) ከፍተኛ ኃላፊዎች እንደሚሉት ግን ምርጫው ሲጠናቀቅ መንግሥቱ ወደ መጡበት ይመሳሰሉ፡፡ የፓርቲው ቃል አቀባይ ኔልሰን ጫሚሳ “አዲሷ ዝምባብዌ” እንደ መንግሥቱ የመሳሰሉ ወንጀለኛ አምባገነኖች በእንግድነት አታስተናድም ብለዋል፡፡ ጫሚሳ፣ ሻንጋይ የሚያሸንፉ ከሆነ መንግሥቱን አሳልፈው ለመስጠት (ለማስወጣት) ያላቸውን እምነት ሲገልፁ “መሬታችን የአምባገነኖች መጠለያ እንዲሆን አንፈልግም” ብለዋል፡፡ በማከልም “በእርግጥ እንደ MDC እምነት ግድያን ወይም የሞት ቅጣትን ጉዳይ ችላ የምንለው አይደለም፡፡ ሆኖም የሟች ቤተሰቦችና የአካልና የአእምሮ ጥቃት ሰለባ የሆኑት ዜጎች ሁሉ ፍትህ እንዲያገኙና እንዲካሱ እንፈልጋለን” ብለዋል፡፡ “ከአምባገነኖች ጋር የሚውለው አምባገነን ብቻ ነው፡፡ They are birds of the Same feather (ተመሳሳይ ወፎች በአንድ ላይ እንደሚበሩ ናቸው”)፡ ለዚህም ነው ዛኑ-ፒ.ኤፍ ረየፕሬዚዳንት ሙጋቤ ፓርቲሪ ከመንግሥቱ ጋር ሙጥኝ የሚለው፡፡ እኛ ግን እንዲህ ዓይነት ፈላጭ ቆራጮች በምድራችን አንፈልግም፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ እጅግ ረዥም ለሆነ ጊዜ አሰቃይተዋል፡፡” የዲፕሎማሲ ምንጮች እንደሚጠቁሙት፣ የኢትዮጵያ መንግሥት እስከአሁን መንግሥቱን አሳልፎ እንዲሰጠው ለዝምባብዌ መንግሥት ኦፊሻላዊ ጥያቄ አላቀረበም፡፡ ባለፈው ዓመት ጥር ወር ላይ ፌዴራል ፍ/ቤት መንግሥቱ ኃ/ማርያምና ሌሎች የደርግ ባለስልጣናት በዘር ማጥፋት ወንጀል ጥፋተኛ ሆነው በመገኘታቸው የዕድሜ ልክ እስራት ፈርዶባቸው የነበረ ቢሆንም፣ ዓቃቤ ህግ ይግባኝ በማለቱ ጠቅላይ ፍ/ቤት ከሁለት ሣምንት በፊት የሞት ቅጣት መፍረዱ ይታወሳል፡፡ የቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት መንግሥቱ ኃ/ማርያምን ጨምሮ 18 ከፍተኛ የደርግ ባለስልጣናት በ2000 ሰዎች ኢሰብአዊ ግድያና በ2400 ሰዎች አካላዊና አእምሮአዊ ስቃይ በመፈፀም በተከሰሱበት የዘር ማጥፋት ወንጀል መንግሥታቸው ተጠያቂ ሆኖ በመገኘቱ የሞት ቅጣት ተወስኖባቸዋል፡፡ ላለፉት 17 ዓመታት የዝምባብዌ መንግሥት መልካም እንግዳ ሆነው የቆዩት መንግሥቱ ኃ/ማርያም በ1983 ዓ.ም ከስልጣን እስከወረዱ ድረስ ተቀናቃኞቻቸው በረሃብና በ”ቀይ ሽብር” ማጥፋታቸው ይታወሳል፡፡ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |