Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Thursday
Aug 28th
Home arrow Sections arrow ከ10 በላይ የመንግሥት መሥሪያ...
ከ10 በላይ የመንግሥት መሥሪያ... Print E-mail
Thursday, 12 June 2008
ከ10 በላይ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በጀት ተቀነሰ
 
በዳዊት ታዬ

በአዲሱ የበጀት (2001) የበጀት አመት ድልድል ከአስር በላይ የሚሆኑ የተለያዩ የመንግሥት መስሪያ ቤቶችና የሚኒስትር መስሪያ ቤቶች በጀት እንዲቀነስ ተደረገ፡፡ የውሃ ሃብት ፈንድ ጽ/ቤት የጠየቀውን በጀት ሙሉ ለሙሉ በማግኘት ብቸኛው መስሪያ ቤት ሆኗል፡፡
ትናንት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በቀረበው የመደበኛና የካፒታል በጀት ዝርዝር መግለጫ ላይ እንደተመለከተው እነዚህ ከአስር በላይ የሚሆኑ መንግሥታዊ መስሪያ ቤቶች ለ2001 ከጠየቁት መደበኛ የበጀት ጥያቄዎች ውስጥ አንዳንዶቹ ከጠየቁት በጀት ግማሽ ያህሉ እንኳን ያልፈቀደላቸው ሲሆን ካለፈው በጀት ዓመት ጋር ሲነፃፀርም ያነሰ በጀት እንደተመደበላቸው ያሳያል፡፡

የበጀት ጥያቄቸው ከተቀነሰባቸውና ካለፈው አመት በጀታቸው ያነሰ በጀት እንደተመደበላቸው ከተደረጉት መስሪያ ቤቶች መካከል የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኤጀንሲ፣ የፕራይቬታይዜሽንና የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ኤጀንሲ፣ የኤሌክትሪክ ኤጀንሲ፣ የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር፣ የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ጽ/ቤት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

የ2001 የበጀት ዓመት ድልድልን በተመለከተ በቀረበው የበጀት ዝርዝር መግለጫ በጀታቸው እንዲቀነስ የተደረጉት መስሪያ ቤቶች እስከ 5 ሚሊዮን ብር ድረስ ቅናሽ የተደረገባቸው ይገኛሉ፡፡

በበጀት ድልድል ዝርዝሩ መሰረት የኢትዮጵያ ጉምሩክ ባለሥልጣን ለ2001 የበጀት አመት 113 ሚሊዮን ብር ጠይቆ የተፈቀደለት ግን 97.7 ሚሊዮን ብር ነው፡፡ ይህም ከጠየቀው ብቻ ሳይሆን በ2000 የበጀት ዓመት ከፈቀደለት በጀት በታች ነው፡፡ ጉምሩክ ባለሥልጣን በ2000 በጀት ዓመት ተፈቅዶለት የነበረው በጀት 101 ሚሊዮን ብር ነበር፡፡

ተመሣሣይ በሆነ መልኩ የሰራተኛ ማህበራዊ ሚኒስቴር ለ2001 በጀት ዓመት 11.02 ሚሊዮን ብር የመደበኛ በጀት ጥያቄ አቅረቦ ሊፈቀድለት የቻለው 10.4 ሚሊዮን ብር ሲሆን ይህም ከ2000 የበጀት ዓመት ተፈቅዶለት ከነበረው የ10.4 ሚሊዮን ብር በጀት ጋር ሲነፃፀር ሁለት ሚሊዮን ብር የሚጠጋ ቅናሽ እንዳለው ያሳያል፡፡

በ2001 የበጀት ድልድል ከጠየቀው በጀት ግማሽ ያህሉን እንኳን ማግኘት ያልቻለው የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ተጠቃሽ ሲሆን ቦርዱ ለበጀት አመቱ መደበኛ በጀት እንዲሆነው የጠየቀው በጀት 8.59 ሚሊዮን ብር ቢሆንም ሊደገፍ የቻለው 4.1 ሚሊዮን ብር ብቻ ነው፡፡ ባለፈው ዓመት ተፈቅዶለት የነበረው በጀት 3.1 ሚሊዮን ብር ነው፡፡

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኤጀንሲም 8.46 ሚሊዮን ብር ጠይቆ ሊፈቀድለት የቻለው 5.3 ሚሊዮን ብር ብቻ ነው፡፡ ይህም ካለፈው የበጀት ዓመት ከተፈቀደለት በጀት ከ1.3 ሚሊዮን ብር በላይ ያነሠ ነው፡፡

የፕራይቬታይዜሽንና የመንግሥት ልማት ድርጅቶችም ተመሳሳይ በሆነ መልኩ መደበና በጀቱ እንዲቀንስ ከተደረጉት መሥሪያ ቤቶች መካከል አንዱ ሆኗል፡፡ ለኤጄንሲው በ2001 በጀት አመት የተፈቀደለት መደበኛ በጀት 6.3 ሚሊዮን ነው፡፡ ባለፈው የበጀት አመት ተፈቅዶለት የነበረው ግን 7.78 ሚሊዮን ብር ነው፡፡ ጠይቆት የነበረው በጀት ደግሞ 10.9 ቢሊዮን ብር ነው፡፡

ኤጀንሲው ባለፈው የበጀት ዓመትም 11.9 ሚሊዮን ብር እንዲፈቀድለት ጠይቆ ማግኘት የቻለው 7.7 ሚሊዮን ብር ብቻ ነው፡፡

የፌዴሬሽን ምክር ቤት ደግሞ ለ2001 የተፈቀደለት መደበኛ በጀት ከጠየቀው በጀት የተፈቀደለት ግማሽ ያህሉ ብቻ ሲሆን ካለፈው በጀት አመት ጋር ሲነፃፀርም በ2 ሚሊዮን ብር እንዲያንስ ተደርጓል፡፡

ፌዴሬሽኑ እንዲሰጠው ጠይቆ የነበረው በጀት 16.7 ሚሊዮን ብር መሆኑን የሚያመለክተው የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የበጀት መግለጫ የተፈቀደለት ግን 8.4 ቢሊዮን ብር ያለፈው አመት በጀቱ ደግሞ 10.08 ሚሊዮን ብር በመሆኑ የበጀት ቅናሽ ከተደረገባቸው መስሪያ ቤቶች ተርታ ውስጥ እንዲገባ አድርጎታል፡፡

ፌዴሬሽን ምክር ቤት ለ2000 በጀት ዓመት 15.05 ሚሊዮን ብር ጠይቆ የተፈቀደለት 10.08 ሚሊዮን እንደነበር የሚታወስ ሲሆን የ1999 የበጀት ዓመት መደበኛ በጀቱ ደግሞ 3.7 ሚሊዮን ብር ብቻ እንደነበር ይታወሳል፡፡

በ2000 የበጀት ዓመት 9.9 ሚሊዮን ብር በጀት ተመድቦለት የነበረው የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ዘንድሮ በጀቱ ወደ 8.5 ሚሊዮን ብር ወርዷል፡፡ የጠየቀው በጀት ግን 14.7 ሚሊዮን ብር እንደነበር ያመለክታል፡፡

በጀቱ እንዲቀነስላቸው የተደረጉት መስሪያ ቤቶች ለበጀት ቅናሹ ምክንያት ለተለያዩ እቃዎች ግዥ ለቢሮ እድሳት የጠየቁት በጀት፣ ለአዲስ ሰራተኛ ቅጥርና ለመሣሠሉት ተግባራት ያቀረቡት ጥያቄ ድጋፍ ባለማግኘቱ ነው፡፡ በተለይ የተሽከርካሪ ግዥ በበጀት አመቱ ብዙ ድጋፍ አላገኘም፡፡

በጥቅሉ በጀት አመት በአስተዳደርና ጠቅላላና አገልግሎት ሥር የሚገኙት 36 መስሪያ ቤቶች በ2001 በጀት ዓመት ለያዙዋቸው በጀት ማስፈፀሚያ ከመንግሥት ግምጃ ቤትና ለውስጥ ገቢ ለደመወዝ አበልና ሥራ ማስኬጃ 6.6 ቢሊዮን ብር ተጠይቆ 5.6 ቢሊዮን ብር መደገፉን የበጀት ድልድሉ ሪፖርት ያመለክታል፡፡

ይህም ከ2000 በጀት አመት ጋር ሲነፃፀር 1876.2 ሚሊዮን ብር ወይም በ184 በመቶ ብልጫ ያሳያል፡፡

ለበጀት ጭማሪው ዋናው ምክንያት ሆነው በሪፖርተር ከተቀመጡት ውስጥ ከ1999 ዓ.ም ጀምሮ ለመንግሥት ሠራተኞች በተደረገው የደመወዝ ጭማሪ ምክንያቶችና ለአገር መከላከያ ሚኒስቴር 500 ሚሊዮን ብር ተጠቅሷል፡፡

በሌላ በኩል በዚህ የበጀት ድልድል የጠየቀው በጀት ሙሉ ለሙሉ ድጋፍ ያገኘው የውሃ ሃብት ፈንድ ጽ/ቤት ሲሆን 1.31 ሚሊዮን ብር በጀት ጠይቆ የጠየቀው በጀት ሁሉ የተፈቀደለት ብቸኛ መስሪያ ቤት ሆኗል፡፡

ይህ መስሪያ ቤት ኢኮኖሚያዊ አዋጭነታቸው ለሚረጋገጥላቸው የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን እንዲሁም የመስኖ ልማት ፕሮጀክቶች የረዥም ጊዜ ብድር በማፈላለግ በማድረግ የሚሰራ መስሪያ ቤት ነው፡፡

መስሪያ ቤቱ በ2000 በጀት ዓመት ተፈቅዶለት የነበረው በጀት 1.05 ሚሊዮን ብር ነበር፡፡

 
< Prev   Next >