| ደጀና ኢንዶውመንት ተሸለመ |
|
|
| Sunday, 15 June 2008 | |
|
ደጀና ኢንዶውመንት በእርሻና አግሮ-ኘሮሰሲንግ ልማት፣ ዘመናዊ መስኖ አጠቃቀም በአካባቢ ጥበቃ፣ በእንስሳት ሃብት ልማት ዙሪያና ሌሎች አዳዲስ ሀሳቦች በማመንጨትና ኢንቨስትመንት በማካሄድ ድህነትን ድል ለማድረግ አበክሮ በመሥራት የሚገኝ አገር በቀል ድርጅት መሆኑ ተገልጿል፡፡
ድርጅቱ ግንቦት 26 ቀን 2ዐዐ8 (እ.አ.አ) ኒውዮርክ ላይ በተካሄደው የ22ኛው ዓለም አቀፍ ኳሊቲ ሳሚት የወርቅ ደረጃ ተሸላሚ መሆኑን ተናግሯል፡፡ * * * በ11 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር የእንግዳ ማረፊያ ህንፃ ሊገነባ ነው መስቀል አደባባይ አካባቢ በሚቀጥለው አንድ ዓመት ተኩል ውስጥ ተገንብቶ የሚጠናቀቅ ሁሉን ነገር ያሟላ የእንግዳ ማረፊያ ሕንፃ በ11 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር እንደሚገነባ ተገለፀ፡፡ ዲዛይኑ በብስራተገብርአል አየለ የተሰራውና ግንባታው በኑርልኝ ደስታ አጠቃላይ ኮንትራክተር የሚካሄደው የእንግዳ ማረፊያ ህንፃ ባለ 45 ፎቅ የሚይዝ ሲሆን በርካታ ክፍሎች እንደሚኖሩት፣ እያንዳንዱ ክፍል ሳተላይት ቲቪ፣ ፍሪጅ፣ ማብሰያና ዘመናዊ በሆኑ ዲዛይኖች ያጌጠ መሆኑን፣ የኢንተርኔት፣ የባርና ሬስቶራንት፣ ቪዛና ማስተር ካርድ እንደሚቀበል ባለቤቶቹ መኪዳ ይፍሩና አቶ ውብሸት ተፈራ ገልፀዋል፡፡ ማረፊያ ቤቱ በምድር ቤቱ ውስጥ ሬስቶራንት፣ መዝናኛ ቦታ፣ ፑል ማጫወቻና የፊልም ማሳያና ቀጥታ የእግር ኳስ ግጥሚያዎችን የሚያስተላልፍ ስክሪን ቲቪዎችም እንደሚኖሩት ተገልጿል፡፡ ማረፊያው ለአንድ ሰውና ባለሁለት መኝታ ክፍሎች ከቁርስ ጋር በተመጣጣኝ ዋጋ ሊያቀርብ እንደሚችል ባለቤቶቹ ገልፀዋል፡፡ * * * ከ4.7 ሚሊዮን በላይ ኩንታል የአትክልት ምርት ተገኘ በምስራቅ ሸዋ ዞን በበጋ ወራት በባህላዊ ዘመናዊ መስኖ ከለማው መሬት ከ4.7 ሚሊዮን በላይ ኩንታል የአትክልት ምርት መገኘቱን የዞኑ ግብርናና ገጠር ልማት ጽሕፈት ቤት አስታወቀ፡፡ የአትክልት ምርቱ ሊገኝ የቻለው በዞኑ 11 ወረዳዎች ውስጥ በባህላዊና በዘመናዊ መስኖ በ46 ሺ 359 ሄክታር መሬት ከለማው አትክልት መሆኑን፣ የቲማቲም፣ ሽንኩርት፣ ድንች፣ ካሮት፣ ቀይ ስር፣ ቀሪያና ጥቅል ጐመን ምርቶች አራት ሚሊዮን ኩንታል ከዘመናዊ መስኖ የተገኘ መሆኑን ገልጿል፡፡ (ዋኢማ) * * * ሦስት ሰዎችን ገድሎ በዘጠኝ ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት ያደረሰ ግለሰብ በሞት እንዲቀጣ ተወሰነ በትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በቂም በቀል ተነሳስቶ ሦስት ሰዎችን ገድሎ በዘጠኝ ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት ያደረሰ አንድ ግለሰብ በሞት እንዲቀጣ መወሰኑን የዞኑ ፍትህ መምሪያ አስታወቀ፡፡ እጮኛዬን ሊነጥቁኝ አስበዋል በሚል ቂም በቀል ተነሳስቶ በዞኑ አስገደ ዕንብላ ወረዳ እንዳባኩና ቀበሌ ባለፈው ዓመት ግንቦት ወር ግለሰቡ ሰዎቹን በአሰቃቂ ሁኔታ በጥይት መግደሉና በዘጠኙ ሰዎች ላይ ቦምብ በመወርወር ከባድና ቀላል የአካል ጉድለት ማድረሱ በማስረጃ በመረጋገጡ በሞት እንዲቀጣ ፍርድ ቤቱ ወስኗል፡፡ (ኢዘአ) * * * |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |