Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Thursday
Aug 28th
Home arrow Sections arrow ትኩረት ለባህላዊ የዘመን ቀመሮች
ትኩረት ለባህላዊ የዘመን ቀመሮች Print E-mail
Sunday, 15 June 2008
Image
ፕሮፌሰር ኤፍሬም ይስሐቅ
በሔኖክ ያሬድ

አዲስ አበባ በቅርቡ የኢትዮጵያ ሺሕ ዓመት (አምአት) ምክንያት በማድረግ የዓለም ባሕረ ሐሳብ ጉባኤ ማስተናገዷ ይታወሳል፡፡ ከምሥራቁም ሆነ ከምዕራቡ ዓለም እሙራን ሊቃውንት በዘመን አቆጣጠርና በሥነ ፈለክ ዙሪያ ጥናቶቻቸውን ያቀረቡ ሲሆን በጥንታዊው የኢትዮጵያ አቆጣጠር ባሕረ ሐሳብ ዙሪያም ልዩ ልዩ ሐሳቦች ተስተናብረዋል፡፡
ጉባኤው በዓለም አቀፍ ደረጃ የመጀመሪያው መሆኑን የተቀረው ዓለም ከስምንት ዓመት በፊት የሚሌኒየሙን መባቻ ሲያከብር እንዳልተካሄደ ያወሱት ፕሮፌሰር ኤፍሬም ይስሐቅ ወጣቱ ትውልድ የማንነቱ መለያ በመረዳት እንዲያተኩር ያግዘዋል ብለዋል፡፡

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በዐውደ ጥናቱ የቀረቡ የጥናት ወረቀቶችና በውይይቱ ሂደት የተነሱ ነጥቦች በስንኝት (ፕሮሲዲንግ) እንደሚያሳትም ይጠበቃል፡፡ የኢትዮጵያን ዘመን አቆጣጠሮች ለማስተዋወቅ መድረኮች ማዘጋጀት አስፈላጊነቱ አያጠያይቅም፡፡ ኢትዮጵያ በውስጧ ባሉት ብሔረሰቦች የተለያዩ ባህላዊ የዘመን አቆጣጠሮች ያሏት በመሆኑ በኅብረተሰቡ ዘንድ እንዲታወቁ ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሆነ የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን ሁሉን አቀፍ የዘመን አቆጣጠር ጉባኤ ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡ የሲዳማ፣ የኦሮሞ፣ የጋምቤላ፣ ወዘተ. ሥርዓቶች ከኢትዮጵያ ሦስተኛው ሺሕ አቀባባል ጋር መከበር ይገባቸዋል፡፡ እምብዛም ትኩረት ባላገኘው የልዩ ልዩ ዘመን አቆጣጠሮች መልኮች በትውልዱ እንዲታወቅ መጪው ትውልድም በዕውቀት ላይ ተመሥርቶ እንዲያከብረው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ድርሻ በከፍተኛ ደረጃ ይጠበቃል፡፡
 
< Prev   Next >