Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Friday
Aug 29th
Home arrow Sections arrow ኢዴአፓ-መድኅን በሚያዚያው ምርጫ...
ኢዴአፓ-መድኅን በሚያዚያው ምርጫ... Print E-mail
Sunday, 15 June 2008
ኢዴአፓ-መድኅን በሚያዚያው ምርጫ ገዢውን ፓርቲና ተቃዋሚዎችን ተቸ

በጋዜጣው ሪፖርተር

የኢዴአፓ-መድኅን በሚያዚያ 5 እና 12/2ዐዐዐ ዓ.ም. የተካሄዱት የአካባቢና የማሟያ የማሟያ በጥቅሉ በህዝቡም፣ በተቃዋሚ ፓርቲዎችና በገዢው ፓርቲ አካላት በኩል በርካታ ጉለቶች እንደነበሩበትና በገዢው ፓርቲ በኩል በተለይ የተሻለ የምርጫ ሁኔታ ለመፍጠር እየሰራ አለመሆኑን ያሳያል ሲል ገልጿል፡፡

ፓርቲው ያለፈው ሀሙስ ባወጣው መግለጫ ከምርጫ 97 ማግስት ጀምሮ በገዢው ፓርቲም ሆነ በተቃዋሚ ፓርቲዎች በኩል፣ በምርጫው ውጤት ላይ በመመርኮዝ መንግሥትን የመለወጥ በጐ ስሜት ከመፍጠር ይልቅ ልዩነቶችን የሚያሰፋና የሚያካርር፤ ግጭትና አለመረጋጋትን በሚያስከትል አስተዋይነትን ሳይሆን ብልጣ ብልጥነትን የተመረኮዘ ስልት የመከተል አዝማሚያ እንደነበረ ገልጿል፡፡ በዚህም አካሄድ በርካታ ኢትዮጵያውያን ህይወታቸውን ማጣታቸውንና የዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ሂደትም በእጅጉ ወደኋላ መጐተቱን ፓርቲው አስታውቋል፡፡

በዚሁ ፓርቲው በመግለጫ የዘንድሮ የአካባቢና የማሟያ ምርጫ ውጤት በገዢው ፓርቲም ሆነ በተታዋሚ ፓርቲ በኩል የተፈፀሙ ስህተቶች የአገሪቱን  ስርዓት ግንባታ ወደኋላ መጐተታቸውን አመላካች እንደሆነ ገልጿል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ የገዢው ፓርቲ የተቃዋሚ ፓርቲ እጩዎች እንዳይመዘገቡ የሚያደርግ ተፅእኖና የማዋከብ ሁኔታ መፈፀሙን ኢዴአፖ መድኅን አስታውቋል፡፡ የፓርቲው መግለጫ መግለጫ አበባ ምርጫ ከህጋዊ መሠረት ውጪ ሙሉ በሙሉ አዲስ ምርጫ እንዲሆን መደረጉንና የአዲስ አበባ ምክር ቤት የሥልጣን ቆይታ በግል ያልተገለፀ መሆኑን አውግዟል፡፡

በማያያዝም ፓርቲዎች ያደረጓቸው  መድረኮች በቀጥታ ለህዝቡ አለመተላለፋቸውንና በክርክሩ ለኢህአዴግ የእጥፍ ሰዓት መሰጠቱን እንዲሁም የውጭ ታዛቢዎች ምርጫውን እንዳይታዘቡ መደረጉን በመጥቀስ፤ “ኢህአዴግ የምርጫውን ሂደት ይበልጥ ከማጠናከር ይልቅ የማዳከም አዝማሚያ እየገባ መሆኑን አሳይቷል” ሲል ፓርቲው አስታውቋል፡፡

ኢዴአፓ-መድኅን፤ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በምርጫው ከሚገባው የእጩ  አንድ በመቶ የሚሆን እጩ ያላቀረቡ መሆኑን በመጥቀስ፤ ለምርጫው ሽንፈት የኢህአዴግን ተፅእኖ ብቻ እንደምክንያት ማቅረብ አግባብ እንዳልሆነ አስታውቋል፡፡

በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በኩል አንዳንድ ማሻሻያ መኖሩን የጠቆመው የፓርቲው መግለጫ፤ “የቦርዱ ጽህፈት ቤቶችና በአጠቃላይ የቦርዱ የበታች መዋቅሮች ካለፉት ዓመታት ዓመታት መሠረታዊ የይዘትም ሆነ የአፈፃፀም ብቃት ለውጥ አልታየባቸውም” ብሏል፡፡

ፓርቲው ዲሞክራሲ በአንድ ጀምበር ሊገነባ የማይችል አዝጋሚና ብዙ መስዋዕትነትን የሚጠይቅ ሂደት መሆኑን በማመልከት “በ2002 ዓ.ም. ምርጫ ላይ በቁርጠኝነት ንቁ ተሳትፎ ለማድረግ እራሱን  እንዲያዘጋጅና በስሜት ሳይሆን በኘሮግራማቸውና በአላማቸው ጥረት በሚተማመንባቸው ፓርቲዎች ዙሪያ እንዲሰለፍ” ሲል ጥሪ አስተላልፏል፡፡
 
< Prev   Next >