Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Thursday
Aug 28th
Home arrow Sections arrow “ኢሕአዴግ የብሄር ጥያቄን በር አንኳኳ፣...
“ኢሕአዴግ የብሄር ጥያቄን በር አንኳኳ፣... Print E-mail
Sunday, 15 June 2008
Image“ኢሕአዴግ የብሄር ጥያቄን በር አንኳኳ፣ እንጂ [የሚዘልቅበት] አይመስልም”

አቶ አስፋው ትሁኔ፣ የኦሮሞ ነፃነት ፓርቲ ም/ሊቀመንበር

በየማነ ናግሽ

አቶ አስፋው ትሁኔ የኦሮሞ ነፃነት ፓርቲ መስራችና ምክትል ሊቀመንበር ናቸው፡፡ በሽግግር መንግሥቱ ወቅት የኦሮምያ ክልላዊ መስተዳድር ዋና ፀሐፊ ሆነው ሰርተዋል፡፡ ቀጥለውም በሞያቸው  የግብርና ቢሮ ውስጥ በከፍተኛ ኤክስፐርትነት አገልግለዋል፡፡ በትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊም ሆነው ሠርተዋል፡፡

አቶ አስፋው የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በባዮሎጂ ሁለተኛ፣ ዲግሪያቸውን በሎካል ኤንድ ሪጅናል ስተዲስ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አግኝተዋል፡፡

አቶ  በፓርቲያቸው እንቅስቃሴ፣ በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ተከስተዋል በተባሉ ግጭቶችና ተያያዥነት ባላቸው ጉዳዮች ዙሪያ አነጋግረናቸዋል፡፡

ሪፖርተር፡- የኦሮሞ ነፃነት ፓርቲን  የገፋፋችሁ ምክንያት ምን ነበር?

አቶ አስፋው፡
- በ1997 ዓ.ም የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች ሃሳባቸውን በሚያንሸራሽሩበት የክርክር መድረክ በጣም አይሎ የወጣው የብሄር ብሄረሰቦች ጥያቄ የመጨፍለቅ አዝማሚያ ነበር፡፡ በዝያን ወቅት ወቅት ሃሳብ ጠነስስኩኝ፣ ሰዎችንም አሰባስበን ሚያዚያ 1997 ዓ.ም ላይ ፓርቲው ተመሰረተ፡፡ በእርግጥ ፓርቲው የጎላ እንቅስቃሴ አላደረገም፡፡ ግን ፕሮግራማችንን ሰላማዊ በሆነ መንገድ በህዝብ ውስጥ  ጥረቶች እያደረግን ነው፡፡

ሪፖርተር፡- በፓርቲያችሁ ስያሜ ላይ “ነፃነት” የሚል  ተጠቅማችኋል፡፡ ምን ለማለት ነው? መገንጠልን ያመላክታል?

አቶ አስፋው፡-
አንዳንዶች ነፃነት እንደ መገንጠል ብቻ አድርገው ይወስዱታል፡፡ ነፃነት ከድህነት መውጣትን፣ ሙሉ ሠብዓዊ መብት መጠበቁን፣ የሕግ የበላይነት መከበሩን በራስ የመወሰን መብትን ጭምር  ስለዚህ “የኦሮሞ ነፃነት ፓርቲ” በምንልበት ጊዜ አንደኛው፣ አንዲት ኢትዮጵያ ብቻ  የሚል ሃሳብ አንቀበልም፡፡ መንግሥት (ገዢው ፓርቲ) ፌዴራሊዝም ብቸኛ አማራጭ አድርጎ ነው የሚያስቀምጠው፡፡ የኦሮሞ ሕዝብ ግን ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር በአንድነት ትኖራለህ ወይ? ተብሎ የተጠየቀበት  የለም፡፡ የመገንጠል ሃሳብ በሚያራምዱ ድርጅቶችም በኩል ተገንጥለህ መኖር ትፈልጋለህ ወይ? ብለው አልጠየቁትም፡፡ ስለዚህ በእኛ ፓርቲ እምነት “ነፃነት” የኦሮሞ ህዝብ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር መኖር ይፈልጋል ወይስ መገንጠል ይፈልጋል? በራሱ የሚወስንበት የሪፈንደም የሪፈንደም ሊሰጠው ይገባል፡፡ ገዢው ፓርቲ ቢሞት ይህንን ዕድል አይሰጥም፡፡ ይህንን ይፈራዋል፡፡ በህገ መንግስቱ አንቀፅ 39 ላይ ግን ቁጭ አድርጎታል፡፡ የአንድነት ኃይሎችም ይህ መብት ይገነጠላል ብለው ስለሚፈሩ እንዲሰጠው አይፈልጉም፡፡ ነገር ግን የሚያስፈራቸው ነገር አልነበረም፡፡ የሕዝብ  ከሆነ መሸከምና መቀበል አለባቸው፡፡ ሌሎቹ ደግሞ በአንድነት እኖራለሁ ሊል  የሚል ስጋት አላቸው፡፡

ሪፖርተር፡- እንዲህ ከሆነ ከኦህዴድ (ኢሕአዴግ) ለምን ወጡ? ለተግባራዊነቱ ውስጥ ውስጥ መታገል አይችሉም ነበር?

አቶ አስፋው፡
- የገዢው ፓርቲ ፕሮግራም ሪፈረንድምን ጭምር የያዘ ነበር፡፡ በተለይ የኦህዴድን የመጀመሪያ ፕሮግራም በምናይበት ጊዜ ቁልጭ ባለ መልኩ ሪፈንድምን የሚጠይቅ ነበር፡፡ ከጊዜ በኋላ ግን ይህ ቀርቶ ፌዴራሊዝምን ብቸኛ አማራጭ ተደርጎ ወሰደ፡፡ ለዛውም ሕገመንግሥቱ ሕገመንግሥቱ ጊዜ የተወሰኑ ሰዎች ተሰብስበው አጨብጭበው ስለተቀበሉት “የኦሮሞ ህዝብ ወስኗል” ተባለ፡፡ ስለዚህ ፕሮግራሙ ተቀልብሷል ማለት ነው፡፡ ይህን ፕሮግራም ስለማምንበት ነበር ኦሕዴድ ውስጥ የገባሁት፡፡ የሪፈንደም ፕሮግረሙን ሲያስወግድ ደግሞ እኔም ከድርጅቱ ወጣሁ፡፡ ይህ እድል ለኦሮሞ ሕዝብ ሳይሰጥ በአገሪቱ  የዴሞክራሲ ስርዓት ይሰፍናል ማለት ቅዥት ነው፡፡  

ሪፖርተር፡- የኦሮሞ ሕዝብ ይህንን አማራጭ (ሪፈረንደም) ጠንቅቆ አውቆ የሚጠቀምበት ይመስሎታል? ስለሪፈረንደም ያለውስ ግንዛቤ ምን ያህል ነው?  መጠቀሚያ አይሆንም?

አቶ አስፋው፡
- ፖለቲካል ሳይንቲስት መሆን ፖለቲከኛ መሆን አይደለም፡፡ ገበሬ ስለ ድሮ ታሪኩ እንዴት እንደ ተጨቆነና ያጣውን ነገር ያውቀዋል፡፡ ስለዚህ የኦሮሞ ሕዝብ ከሌሎች ህዝቦች ጋር ሊኖው የሚገባው ግንኙነት መወሰን ያለበት ራሱ ብቻ ነው፡፡ ባለመማሩ የሚፈልገውን አጣ ማለት፣ ማለት፣ ማለት አይደለም፡፡ ተገንጥዬ እጠቀማለሁ ወይስ እጎዳሁ የሚለውን በትክክለኛ ኦሮምኛ ወይም በተሰባበረ አማርኛ ይነግርሃል፡፡

በእኛ አገር ፖለቲከኞች ሁሉጊዜ ለህዝቡ “እኛ እናውቅልሃለን” ነው የምንለው፡፡ ይሄ ይሆንሃል ብለን ስንወስድለት ታች በሚወርድበት ጊዜ አይሆንም፣ ምን ትፈልጋለህ፣ ምን ሆነሃል፣ ብለህ መፍትሄውን ብትጠይቀው ደግሞ ከፖለቲካ ሳይንቲስቶችና  ከዶክተሮች በላይ እውነተኛ መፍትሄ ታገኘዋለህ፡፡ በእርግጥ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች በህዝብ ውስጥ በሚንቀሳቀሱበት ጊዜ በተለያየ   አንዱ ሊያጋድሉ ይችላል፡፡ አሁን ሌሎች የፖለቲካ ድርጅቶችን ለምን መረጥካቸው ብትለው ፕሮግራማቸውን አውቆ ሳይሆን  ላይ ያሉት ሰዎች ከሚያደርሱት በደል የተነሳ ሊሆን ይችላል፡፡

ሪፖርተር፡- በአሁኑ ወቅት የመገንጠልም ሆነ የነፃነት ጥያቄ በኦሮሞ ሕዝብ አካባቢ እየተነሱ ያሉት ከታሪክ ቁርሾ ነው፡፡ ሁልጊዜ አንድ አገር ሲፈጠር በኃይልና በጦርነት ነው፡፡ ይሄ በየትኛውም አገር ያለ ታሪክ  

አቶ አስፋው፡- ህ
ብረተሰብ በተለያየ የእድገት ደረጃ ነው ያለፈው፡፡ ይሄ የእድገት ደረጃ ዋናው መሰረቱ  ስለሆነ በዛ ወቅት ሃብት ለመውረስ መዝመቱ አልቀረም፡፡ ወቅቶች እየተቀያየሩ በመጡ ቁጥር ያንን ሃብት በእጁ ለማስቀረት ኃይልን የመጠቀም ሁኔታ አለ፡፡ አፄ ምንሊክ ከሸዋ ተነስቶ የኦሮሞን ሕዝብ ወረሩ፡፡ በዚያ ጊዜ የገዢነት መሰረት ሌጋሲ የላቸውም፡፡ ይህ ኃይል እየተሻሻለ በሚሄድበት ጊዜ የመግዛቱን የመጨቆኑን መሳሪያ እያሳደገ ይሄዳል፡፡ እዛ አካባቢ ያለው ሃብት እዚያ  መዋሉ ቀርቶ ዋናው በጨቋኙ መደብ እየተወሰደ ነው የመጣው፡፡ እጅግ ኢ-ፍትሃዊ (ኢንጀስትስ) ሥራ ነው የተሰራው፡፡ ይሄ በአንድ ወቅት መቀልበስ ይኖርበታል፡፡ ሃብቱና አገሩ ለባለ አገሩ መሆን አለበት፡፡ ይሄ በነበረበት ይቀጥል ማለት ኢ-ፍትሃዊ ነው፡፡ እንደውም ፍትህና ዴሞክራሲ ተስፋፍቶ ቢሆን ኖሮ የበዳዩ ወገን ለተበዳዩ ካሳ መክፈል ነበረበት፡፡ ይቅርታ መጠየቅ  ይህ ቀርቶ አሁንም ጥያቄው የመጨፍለቅ አዝማሚያ አለ፡፡

ሪፖርተር፡- ማን ማንን ነው ይቅርታ ሊጠይቅ የሚችለው? ያ ሥርዓት በአሁኑ ወቅት የለም፤

 አስፋው፡-
በየወቅቱ የመጡ የኢትዮጵያ መግሥታት በኦሮሞና በደቡብ ሕዝቦች ላይ የተደረገው ጭፍጨፋ አግባብ አይደለም ብለው ይፋ ማድረግ ነበረባቸው፡፡ አፄ ምንሊክ ከሄዱ በኋላ አፄ ኃ/ስላሴ በሚመጡበት ጊዜ ምንሊክ ለሰራው ይቅርታ መጠየቅ ነበረባቸው፡፡ ይህ ማንም አላደረገም፡፡ በ1997 ምርጫ ክርክር ላይ ከአንድ  የሰማሁት “እኛ በዘር  እንሰሳ አይደለንም” ተብሎ ኢሕአዴግ በዘር፣ በጎሳ ነው የሚያስበው ተባለ፡፡ በኦሮሞ ውስጥ እጅግ በርካታ ጎሳዎች አሉ፡፡ ኢቱ፣ ከርዩ፣ ዋዩ፣ ቶለማ፣ ጫጫ፣ ስዮ፣ አርሲ መዓት ትደረድራለህ፡፡ እነኚህ ጎሳዎች ናቸው፡፡ እነዚህ ሁሉ ተጠቃልለው ኦሮሞ ብሄርን ያመጣሉ፡፡ አንድን ህዝብ ከሕዝብነት  ጎሳ ዝቅ አድርጎ ማሳነስ፣ የድሮ ናፍቆት ከቤተሰብ ተወርሶ የመጣ የአመለካከት በሽታ ተጋብቶባቸው ነው፡፡ ስለዚህ እነዚህ ወገኖች ያለፈውን ታሪክ ስህተት ነው ብለው ካላመኑና ካላወገዙ እነሱም ተመሳሳይ ፖሊሲ እያራመዱ ስለሆነ ተጠያቂዎች ናቸው፡፡ በሁለተኛ ደረጃ በዘርም/ በጎሳም ሲታሰብ እንስሳነት አይደለም፡፡ አንዱ ደህና ሁኑ ብሎ ቢሄድ ምን ክፋት አለው? ተፈጥሮአዊ መብቱ ነው፡፡ ይሄን ያህል ዓመት በድያችኋለሁኝ ወይም በድላችሁኛልና ከዛሬ ጀምሮ አብሬ መኖር አልፈልግም፡፡ ራሴን ችዬ እተዳደራለሁ ቢል ይሄ ተፈጥሮአዊ አካሄድ ነው፡፡ አንዳንዶቹ ይህ ጥያቄ ለምን እንደሚያንገሸግሻቸው አይገባኝም፡፡ ፌዴራሊዝም እንኳ ኢሕአዴግ ረስቶታል፣ ተጠቅሞባታል እንጂ፣ ፖሊሲው  ስራ ላይ ባልዋለበት፣ ትልቅ ነገር ሆኖ “ያዙን ልቀቁን” ነው የተባለው፡፡ “አንድ ኢትዮጵያ” ካልሆነ ሞተን እንገኛለን ነው፡፡ “አንድ ኢትዮጵያ” እነሱ ስለፈለጉ የሚመጣ ስለጠሉት የሚቀር ነገር አይደለም፡፡ የሕዝብ ውሳኔ ነው፡፡ ስለዚህ ይህንን አመለካከት ተሸክመው በየቦታው የሚንቀሳቀሱ የገዢው መደብ ፖለቲከኞች አሉ፡፡   

ሪፖርተር፡- እንደዚህ ዓይነት አመለካከት ያላቸው የፖለቲካ ኃይሎች ጠንካሮችና በ1997 ዓ.ም በኦሮሞ ሕዝብ ጭምር ከፍተኛ ተቀባይነት አግኝተዋል፣ የተቃውሞ መድረኩን የተቆጣጠሩትም እነሱ ናቸው፣   

አቶ አስፋው፡- 
በግምትህ ላይ አልስማም፡፡ እንደ ፖለቲካ ፓርቲ ጠንካሮች ናቸው፡፡ ምክንያቱም የውትወታ ችሎታ አላቸው፡፡ በሁለተኛ ደረጃ እነዚህ ወገኖች ያለፈው  ቀጥተኛ ተጠቃሚዎች ናቸው፡፡ ይህ ጥቅማቸው አንድ አድርጎዋቸዋል፡፡ ዓላማቸው ያቺ አይነት አንድ ኢትዮጵያ ለመፍጠር ነው፡፡  ዙሪያም ሊሰባሰቡ ችለዋል፡፡ ኢሕአዴግም ምን ያህል እንደአርበደበዱት እናውቃለን፡፡ ይሄ ግን ከእነሱ ፖሊሲና ርእዮት ጥንካሬ ሳይሆን ከኢሕአዴግ ደካማነት   

ሪፖርተር፡- እንዴት?

አቶ አስፋው፡-
በፖለቲካ ክርክሩ ኢሕአዴግ ያቀረባቸው ሰዎች በራሳቸው የማይተማመኑ ናቸው፡፡ የመከራከሪያ ነጥባቸውም እጅግ ደካማ ነበር፡፡ ኢሕአዴግ የሕዝብ ፍላጎት አልጠበቀም፡፡ አባላቱ  ጋር ናቸው ይበል እንጂ አብዛኛዎቹ ከተቃዋሚዎች ጋር ነበሩ፡፡ እነዚህን ኃይሎች መረጡ የሚባሉ ሰዎችም የኢሕአዴግን ፕሮግራም ሳይደግፉ ቀርተው ሳይሆን፣ በኢሕአዴግ ስራዎች ቅር የተሰኙ ናቸው፡፡ ፓርቲው ከሕዝብ ጋር አልተናበበም፡፡ ፖሊሲውን ተግባራዊ ለማድረግ በየደረጃው በኃላፊነት ያስቀመጣቸው ሰዎች ብቃት የላቸውም፡፡  ጋር ያጣሉትም እነሱ ናቸው፡፡ ከኢሕአዴግ ጋር የነበሩ አንዳንድ ሰዎች ብቃት ያላቸው ቢሆንም ቅሬታ ነበራቸው፡፡ ነገሩ ብራቡሬ ነው፡፡ ከአባልነት የወጣሁትም አካሄዱ ስላላማረኝ ነው፡፡ ውስጣዊ ዴሞክራሲ የለም፡፡ የሕዝብ ድምፅ አይሰማም፡፡ በህዝቡ ዘንድ ብዙ ቅሬታዎች አሉ፡፡ ስለዚህ ሊያስኬደን አልቻለም፡፡ በፊት ከነበረው ፕሮግራም አዘንብለዋል፡፡ አሁን ጨርሶ “ከኢትዮጵያ አንድነት” አቀንቃኞች አቀንቃኞች ብዙም አይራራቅም፡፡ በቃላት ይለያዩ እንጂ “የኢትዮጵያ ተሃድሶና” “የኢትዮጵያ አንድነት” ዓላማቸው አንድ ነው፡፡ የሪፈረንደም ጥያቄ፣ ራስን በራስ የማስተዳደር መብትን ወዘተ. በተግባር እየቀሩት ነው፡፡

ለምሳሌ ብሄራዊ ስሜት የመፍጠር ጉዳይ አለ፡፡ በፌዴራል ስርዓት “ብሄራዊ” ስሜት የሚባል  የለም፡፡ በፖለቲካ አነጋገር “ብሄራዊ” የሚል ነገር ከፌዴራሊዝም ጋር የሚፋለስ ነው፡፡

ሪፖርተር፡- የፌደራል ሥርዓት ዋና ግብም እኮ በመከባበር “ብሄራዊ አንድነት” መፍጠር ነው፤

አቶ አስፋው፡-
ብሄራዊ ስሜት የአንዲት ኢትዮጵያ  ማለት ነው፡፡ ይሄ ደግሞ ኦሮሞው፣ ትግራዩ፣ ሶማሊያው በአንድ ጥላ ስር በአንድ ቋንቋ፣ በአንድ ባህልና አስተሳሰብ እንዲሆን ማድረግ ነው፡፡ ይሄ መፍለቅ ያለበት ህዳሴ ከኢሕአዴግ ሳይሆን ቀስ በቀስ ከሕዝቡ ነው፡፡ በተለይ ኦሮሞው ሪፈረንደም ሳያካሂድ ፍላጎቱን ማወቅ አይቻልም፡፡ የብሄር ጥያቄ በር ያንኳኳበት ኢሕአዴግ ያኔ እንደ ዱላ የተጠቀመበት ነው እንጂ እስከ መጨረሻ የሚሄድበት አይመስለኝም፡፡

ሪፖርተር፡- ኢሕአዴግ ወደዚያ  ምክንያት ምን ይመስሎታል?

አቶ አስፋው፡
- በእኔ ግምት ደንግጧል፡፡ የኢትዮጵያ አንድነት የሚያቀነቅኑ ኃይሎች የአዲስ አበባ ሕዝብ ሙሉ ድምፅ ስለሰጣቸው ደንግጧል፡፡ ስለዚህ በይፋ አልተናገረም እንጂ ፈርቷል፡፡ ከአመጣጡ ግን ለድል ያበቃው ይሄ ርዕዮት ነበር፡፡ ኢትዮጵዊነት እኮ ስሜት ነው፡፡ በጫና፣ በግፊት፣ በማሳደድ የሚመጣ ከሆነ ነገ ተመልሶ በኢትዮጵያዊነቱ የሚማረር ዜጋ ነው የሚፈጠረው፡፡ መብቱ ለሚጠይቅ ሁሉ ትሰጠውና ተከባብሮ፣ ተማምኖ ይኖራል ወይ? ይለያያል፡፡

ሪፖርተር፡- በርካታ የኦሮሞ የፖለቲካ ድርጅቶች አሉ፡፡ ይሁን እንጂ የጋራ መድረክ ፈጥረው በሕብረት አይንቀሳሱም፤

አቶ አስፋው፡-
በኦሮሞ ሕዝብ ላይ የሚያነሱት የታሪክ ጥያቄ ራሳቸው አልተገባቡም፡፡ የቅንጅት የቅኝ ግዛት ጥያቄ፣ የብሄር ብሄረሰብ  ሌላው ወገን ደግሞ የዴሞክራሲ ጥያቄ አላቸው፡፡ አንድ በሽታ የሚፈወሰው ትክክለኛ መድሃኒቱን ሲያገኝ ነው፡፡ መፍትሄው ሊሆን የሚችለው ግን የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብት ነው፡፡ ኢሕአዴግ በሕገ መንግሥቱ አስቀመጠው እንጂ በተግባር ጥያቄው አልመለሰውም፡፡

ሪፖርተር፡- በእርስዎ ግምት ሪፊረንደም ምርጫ ቢሰጠው የኦሮሞ ሕዝብ ምን የሚል ይመስሎታል?

አቶ አስፋው፡
- አይመጣም፣ የሚፈልግ አይመስለኝም፡፡

ሪፖርተር፡- ኦነግ እስካሁን የመገንጠል  ይዞ ብዙ ዓመት ታግሏል፡፡ ሕዝቡ የሚደግፈው ቢሆን ዓላማውን ያሳካ ነበር፣

አቶ አስፋው፡-
አይደለም፡፡ እንደ ፕሮግራም ከኦሮሞ የፖለቲካ ፓርቶች በሙሉ ትክክለኛ መርህ ይዞ ነው የወጣው፡፡  አፈፃፀም ላይ ችግር አለበት፡፡ መገንጠል ብሎ  ማለት መገንጠል ብቻ አይደለም፡፡ በመገንጠል ማዕቀፍ ውስጥ ብዙ አማራጮች አሉ፡፡ በዚሁ ማዕቀፍ “ራስን በራስ የማስተዳደር መብት” ስላለ አንድነትም ሊመርጥ ይችላል፡፡ ስለዚህ አመራጮች ቀርበውለት ሕዝቡ ነው መወሰን ያለበት፡፡ ኮንፌዴሬሽንም ሊመረጥ ይችላል፡፡ የፓርቲው ችግር ግን ሁኔታዎችን እየገመገመ አስፈላጊ ከሆነ ወደ ሰላማዊ ትግል አለመግባቱ ነው፡፡ ሁለተኛ በሕዝቦች ላይ ያለው አመላካከት ትክክለኛ አለመሆኑ ነው፡፡ በ1983 ዓ.ም የተደረጉ ጭፍጨፋዎችን አይተናል፡፡

ሪፖርተር፡- አንዳንድ ምሁራን ስርዓቱ ዘረኝነትን በማስፋፋት ለመፈረካከስ በር እየከፈተ ነው ይላሉ፣

አቶ አስፋው፡-
በኢትዮጵያ ከትውልድ ትውልድ የተላለፈ በሽታ አለ፡፡ ሰዎች ዲግሪ በመያዛቸው አመለካከታቸው አይቀየርም፡፡ በቅርቡ  በአንድ ጋዜጣ ላይ “14 መንግሥታት፣ 14 ባንዲራዎች” የሚል በጥላቻ የተፃፈ ጽሁፍ አየሁ፡፡ ፀሐፊው አስቀይሞታል ማለት ነው፡፡ ሞያየም  በተፈጥሮ ጥበቃ ላይ ነው፡፡ ወደ ጫካ በምትሄድበት ጊዜ ብዝሃ ሕይወት ትጠብቃቸዋለህ፤ ምክንያቱም ውበት ነው፡፡ የብሄረሰቦችም ብዝሓት በዚህ ይገለፃል፡፡

አንድ  ቋንቋውን ሲናገር፣ ሙዚቃውን ሲሰሙ የሚከፋው አካል ካለ፤ ጥላቻ አለበት ማለት ነው፡፡ ዘረኝነት ደግሞ ጥላቻን ወይም ንቀት ነው፡፡ በትክክል ይሄ ነው ዘረኛ መባል ያለበት፡፡ የእሱ ቋንቋ ብቻ እንዲነገር እንዲሰማ የምትፈልግ ከሆነ ዘረኛ ነህ፡፡  

ሪፖርተር፡- በቅርቡ በወለጋ አካባቢ ስለተከሰተው ግጭት የመንግሥት ምላሽ በቂ ነው?

አቶ አስፋው
፡- ግጭቱ የተከሰተው በቤንሻንል ጉምዝና በኦሮሞ መካከል  በአከባቢው ያሉት አርብቶ አደሮች ናቸው፡፡ የትም ቦታ ሊያጋጥም የሚችል፣ በግጦሽ በውሃ የሚነሳ ግጭት ነው፡፡ እጅግ በጣም ዘግናኝ ነገር ነው፡፡ የተጠቃውም የኦሮሞ ሕዝብ ነው፡፡ ከወዲያኛው ወገን  በትጥቅ የታጋዘ ነው፡፡

የኦሮሞ ክልላዊ መንግሥት ዋነኛው ስራው የአካባቢው ድንበርና የሕዝቡን ደህንነትን ማስጠበቅ ነው፡፡ ተቃዋሚዎችና ሚዲያዎች ስለዚህ ይነገራሉ፤ መንግሥት ግን ችላ ብሎታል፡፡ ፌዴራል መንግሥቱ  አቋቁሞ መንስኤው  እንደሆነና የደረሰውን ጉዳት ሁሉ  አልቻለም፡፡

ሪፖርተር፡- እነዚህ ግጭቶች ስርዓቱ የፈጠራቸው ናቸው ይባላል፤

አቶ አስፋው፡-
የምትጠላውን ሰው ሽቶ አትቀባውም፡፡ ኢሕአዴግም ፌዴራሊዝም ለይቶ ማየት ያስፈልጋል፡፡ ግጭቱንና ፌዴራሊዝም በፍፁም አይያዝም፡፡ “አንድ ኢትዮጵያ” በነበረ ጊዜም እኮ ከዚህ በላይ ግጭቶች ነበሩ፡፡ ያኔ ፌዴራሊዝም አልነበረም፡፡ ድሮም በቋንቋ የተለያዩ ናቸው፡፡ ግጭቶቹ ግን አፋጣኝ ምላሽ አልተሰጣቸውም፡፡ የክልሎች ወሰንም በትክክል ተካልሎ አልተሰራም፡፡ ሕዝቦች ራሳቸው  ብለው ይለዩታል፡፡ የክልሉ መንግሥታት ድክመት

ሪፖርተር፡- እርስዎ በስልጣን ላይ በነበሩበት ጊዜ ምን አድርገዋል?

አቶ አስፋው፡-
ብዙ ችግሮች አስወግጃለሁ፡፡ ለምሳ  ወደ ቤንሻንጉል ጉምዝ በሚባልበት ጊዜ ኮሚቴ መስርቼ አወያይቼ ነው ችግሩን ያስቀረሁት፡፡ ከሚሴም (በአማራ ክልል) የኦሮምያ ዞን እንድትሆን እስከ መጨረሻ ተከታትዬ የህዝብ ውሳኔ እንድታገኝ አድርጌያለሁ፡፡ ፊቼ (ሰሜን ሸዋ) መጀመሪያ መጀመሪያ ተሰጥቶ ነበር፡፡  ጥረት ተመልሶ ወደ አባት አገሩ እንዲመለስ አድርጌያለሁ፡፡ እኔ ብቀጥል ይሄ ችግር አይኖርም ለማለት አይደለም፡፡ የከፋም ሊሆን ይችላል፡፡ ግን በወቅቱ ማድረግ የሚገባኝን ነገር አድርጌያለሁ፡፡
 
< Prev   Next >