| ሁለቱ የኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጮች... |
|
|
| Sunday, 15 June 2008 | |
|
ሁለቱ የኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጮች ማኅበራት መለሰው ለመዋሃድ መግባባት ላይ ደርሰዋል
በዳዊት ታዬ በኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጮች ማኅበርና በኢትዮጵያ ደረጃ አንድ የኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጮች ማኅበር መካከል ተፈጥሮ የነበረውን አለመግባባት ለመፍታትና በአንድ ማኅበር ሥር መልሶ ለመጠቃለል የሚያስችል ቅድመ ስምምነት መደረጉ ተጠቆመ፡፡ ከኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን የሥራ ተቋራጮች ማኅበር የተገኘው መረጃ እንዲያመለክተው በሁለቱ ማኅበራት መካከል ያለውን ልዩነት ለመፍታት ሁለቱም ወገኖች ፍላጎት በማሳየታቸው በዚሁ ፍላጎት መሠረት መልሰው በአንድ ማኅበር እንዲጠቃለሉ የሚያስችል ቅድመ ሥራዎች እንዲከናወን በመወሰኑ ወደ ውህደት ሊያስኬድ የሚችል ሥራ በመሠራት ላይ ነው፡፡ እንደ ኢትዮጵያ የሥራ ተቋራጮች የሥራ ኃላፊዎች ገለፃ ማህበሩ በአዲስ አመራር እንዲተካ ከተደረገ ወዲህ በሁለቱ ማህበራት በኩል ተፈጥሮ የነበረውን አለመግባበት ለማስቀረት ጥረት ተደርጓል፡፡ ይህም ጥረት ወደፊት ለሚጠበቀው ውህደት የሚረዳ የመግባቢያ ሰነድ ረቂቅ ህግ እንዲዘጋጅ በር የከፈተ በመሆኑ የረቂቅ ህጉ ሥራ በመሠራት ላይ ይገኛል፡፡ የመግባቢያ ሠነድ ረቂቅ ህጉ እንደተጠናቀቀም ወደ ውህደት ሊገቡ ይችላሉ የሚል እምነት ያላቸው ሲሆን በጥምረት መስራታቸውም ለኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው ትልቅ ጉልበት ይሆናል ባይ ናቸው፡፡ ደረጃ አንድ ኮንትራክተሮች ማኅበር ሊቋቋም የቻለው ከ13 ዓመት በላይ ከቆየው ኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን የሥራ ተቋራጭ ማኅበር በወጡ የደረጃ አንድ ኮንትራክተሮች እንደሆነ ያስታወሱት እኚሁ የሥራ ኃላፊዎች በወቅቱ ይህንን እርምጃ ሊወስዱ የቻሉትም ቀደም ብለው ከነበሩት የማኅበሩ አመራሮች ጋር መግባባት ባለመቻላቸው እንደነበር ተጠቁሟል፡፡ አሁንም በሁለቱም ማኅበራት ውስጥ የደረጃ አንድ ታቅፈዋል፡፡ በተለያዩ የሥራ አጋጣሚዎችም የሚገኙና ለብቻቸው ሆነው ማኅበር ለመስራት ያነሳሳቸው ችግር አሁን የተወገደ በመሆኑ ከዚህ በኋላ ለመዋሃድ ብዙም ችግር አይኖርም ባይ ናቸው፡፡ የደረጃ አንድ ኮንትራክተሮች ማኅበርም በሁለቱ ወገኖች መካከል ያለውን ልዩነት ለመፍታትና ወደ ውህደት ለማምራት በተደረሰው ስምምነት መሠረት ፍላጎቱን በደብዳቤ ጭምር ማሳወቁን ለማወቅ ተችሏል፡፡ በአሁኑ ወቅት ደረጃ አንድና ከዚያም በላይ የሆኑ ኮንትራክተሮች ቁጥር ከ2000 በላይ እንደሚሆን የሚገመት ሲሆን ሁለቱም ማኅበራት ግን በአባልነት ያቀፏቸው የኮንትራክተሮች ቁጥር አነስተኛ እንደሆነ ይታመናል፡፡ በመጀመሪያ የተቋቋመውና ከ13 ዓመት በላይ እድሜ ያለው የኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጮች ማኅበር በአሁኑ ወቅት ያሉት አባላት 150 አይሞላም፡፡ የደረጃ አንድ ኮንትራክተሮች የተሰባሰቡት እና ከተቋቋመ ሁለት ዓመታት ያስቆጠረም ቢሆን ያቀፋቸው አባላት ቁጥርም አነስተኛ እንደሆነ ታውቋል፡፡ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |