Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Monday
Sep 08th
Home arrow Sections arrow ለአዲሱ ዓመት ከተመደበው በጀት...
ለአዲሱ ዓመት ከተመደበው በጀት... Print E-mail
Sunday, 15 June 2008
ለአዲሱ ዓመት ከተመደበው በጀት 22 ቢሊዮን ብር ከእርዳታና ከብድር የሚጠበቅ ነው
በዳዊት ታዬ

ከሐምሌ 1 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል ተብሎ በመንግሥት ከተያዘው 54.3 ቢሊዮን ብር የአገሪቱ በጀትና ይሰበሰባል ተብሎ በታቀደው ገቢ መካከል የ8.8 ቢሊየን ብር የበጀት ጉድለት የሚታይና 22 ቢሊዮን ብር የሚሆነው ገንዘብም ከእርዳታና ብድር የሚጠበቅ ነው፡፡
በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትር በኩል በቀረበው የ2001 የበጀት ዓመት ድልድል መግለጫ ላይ እንደተመለከተው በ20ዐ1 በጀት ዓመት ጠቅላላ የፈደራል መንግሥት ወጪ 54.3 ቢሊዮን ብር የሚሆንና በዚሁ ዓመት ይገኛል ተብሎ በሚጠበቀው ገቢ ግን 45.4 ቢሊዮን ብር በመሆኑ በገቢና በወጪው መካከል የ8.8 ቢሊዮን ብር ጉድለት እንዳለ ያሳያል፡፡

እንደ አቶ ሶፊያን ገለፃ ከሆነ ይህንን በበጀት ዓመቱ በተመደበውና ይገኛል ተብሎ በሚጠበቀው ገቢ መካከል ያለውን ልዩነት ለመሙላት በዋናነት ከአገር ውስጥና  በሚገኝ ብድር ለመሞላት ታቅዷል፡፡

በእቅዱ መሠረትም ለጉድለቱ ማሟያ ይሆናል ተብሎ ከታሰበውና ከ8.8 ቢሊዮን ብሩ ውስጥ ከ44 በመቶ በላይ ወይም 3.7 ቢሊዮን ብር የሚሆነውን ከውጭ ከሚገኝ ኘሮጀክት ብድር የሚሞላ እንደሚሆን ታሳቢ ተደርጐ የተሰራ በጀት ነው፡፡ ከ55 በመቶ በላይ ወይም ከግማሽ በላይ የሚሆነውን የበጀት ጉድለት ለመሙላት የታቀደው ደግሞ ከአገር ውስጥ በሚገኝ ብድር ነው፡፡ ይህም ለአገር ውስጥ እንደሚገኝ ታስቦ የተያዘው የብድር መጠን 5.3 ሚሊዮን ብር ሲሆን ቀሪው 164.6 ሚሊዮን ብር ደግሞ ከእዳ ማቃለያ የሚሸፈን እንደሚሆን ያመለክታል፡፡

ይህም በበጀት ዓመቱ የሚታየውን በጀት ጉድለት በ2ዐዐዐ የበጀት ዓመት ከታየው የበጀት ጉድለት በሁለት እጥፍ ማደጉን ያመላክታል፡፡

በ2ዐዐዐ የበጀት ዓመት የአስር ወራት የፌዴራል መንግሥት ገቢ የቀጥታ በጀት ድጋፍና እዳ ቅነሳን ጨምሮ ብር 25.3 ቢሊዮን ብር እንደነበር የሚታወቅ ሲሆን ወጪው ደግሞ ብር 27.5 ቢሊዮን ብር በመሆኑ በዚህ ጊዜ ውስጥ የታየው የበጀት ጉድለት 2.3 ቢሊዮን ብር መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡

እንደ አቶ ሶፊያን ገለፃ ደግሞ ይህንን በአሥር ወራት ውስጥ የታየውን የ2.3 ቢሊዮን ብር የበጀት ጉድለት ለመሙላት መንግሥት አንድ ቢሊዮን ብር ከውጭ ብድር የተሸፈነ ሲሆን ቀሪው ደግሞ አገር ውስጥ ብድር ተሸፍኗል፡፡
 
የበጀት ዓመቱ የሚያስፈልገውን ገንዘብ ለማሟላት በዋናነት ታሳቢ የተደረገው ከታክስ ይሰበሰባል የተባለው ገንዘብ ነው፡፡ በእቅዱ መሠረት ከታክስ ገቢ ከ25.4 ቢሊዮን ብር በላይ ለመሰብሰብ ታቅዷል፡፡

ይህም ሊሰበሰብ የታቀደው ገቢ ከአምናው ሊሰበሰብ ከታቀደው ገቢ ከ5 ቢሊዮን ብር በላይ ብልጫ እንዲኖረው ተደርጐ የተሰራ ሲሆን ታክስ ካልሆኑ ገቢዎች ደግሞ 6.4 ቢሊዮን ብር ይጠበቃል፡፡ በጥቅሉ ከአገር ውስጥ ይገኛል ከተባለው 32.09 ቢሊዮን ብር  ነገር ግን በ2ዐዐዐ የበጀት ዓመት ከጠቅላላ የአገር ውስጥ ገቢ ይሰባሰባል ተብሎ የታቀደው 26.3 ቢሊዮን ብር ሲሆን በአሥር ወር የተሰበሰበው 21.5 ቢሊዮን ብር ነው፡፡

በበጀት ዓመቱ ከውጭ አገር እርዳታ ይገኛል ተብሎ ታሳቢ የተደረገው ደግሞ 13.5 ቢሊዮን ብር ሲሆን ከውጭ አገር ይገኛል ተብሎ የታመነው የብድር መጠን 3.54 ቢሊዮን ብር ነው፡፡ ይህም ከእርዳታና ከብድር ይገኛል ተብሎ የተያዘው በጀት የጠቅላላ የበጀቱን ከ38 በመቶ በላይ ድርሻ እንዳይዝ የሚያደርግ ሲሆን በጥቅሉ ከብድርና እርዳታን ይገኛል ተብሎ የሚጠበቀው የገንዘብ መጠን 2ዐ ቢሊዮን ብር እንደሚሆን ያመለክታል፡፡

በዚሁ የበጀት ድልድል መሠረት ከውጭ እርዳታ ይሰጣሉ ተብለው የተጠቀሱት አገሮች ድርጅቶች ከ17 በላይ ናቸው፡፡ እነዚህም ድርጅቶችና አገሮች ከ285 ሺህ 500 እስከ 1.3 ቢሊዮን ብር እትዳታ ይሰጣሉ ተብሎ የታመነባቸው ሲሆኑ ትልቁን ብድር ይሰጣል ተብሎ የሚጠበቀውም የዓለም አቀፍ ፈንድ ይሰጣል ተብሎ የሚጠበቀውም 1.3 ቢሊዮን ብር ነው፡፡ ዓለም አቀፍ የአቶሚክ ኃይል ድርጅት ደግሞ 932.1 ቢሊዮን ብር በመስጠት በሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡

በእርዳታ ከተለያዩ ተቋማት ይገኛል ተብሎ ከሚጠበቀው 2.009 ቢሊዮን ብር ውስጥ ትልቁን እርዳታ እንደሚያደርግ የሚጠበቀው የኔዘርላንድ የልማት ድርጅት  ድርጅቱ ይሰጣል የተባለው ገንዘብ 247.1 ሚሊዮን ብር እንደሚሆን ያመለክታል፡፡
 
እርዳታና ብድር ይሰጣሉ ተብለው ከተጠቀሱት የገሮችና ድርጅቶች ሰንጠረዥ ውስጥ ከኢትዮጵያ ጋር በጐ ግንኙነት እንዳላት የምትጠቀሰው አሜሪካ በተባበሩት የአሜሪካ መንግሥታት ልማት ወኪል ትብብር በኩል 67.1 ቢሊዮን ብር እርዳታ የምትሰጥ ሲሆን፤ የእንግሊዝ የውጭ ኢኮኖሚ ትብብር መምሪየ 112 ሚሊዮን ብር፣ የቻይና መንግሥት ደግሞ 3.4 ሚሊዮን ብር ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ከዓለም አቀፍ ድርጅቶች ይሰጣሉ ተብሎ ከሚጠበቀው 3.5 ቢሊዮን ብር ውስጥ 2.35 ቢሊዮን ብር ብድር በመስጠት ትልቁን ድርሻ የያዘው ዓለም አቀፍ የልማት ማህበር ሲሆን የቻይና መንግሥት ደግሞ 79.5 ሚሊዮን ብር እንዲሁም ከሳውዲ ፈንድ 65.5 ሚሊዮን ብር ይሰጣሉ፡፡

በሌላ በኩልም ለካፒታል በጀት ከተመደበው 23.29 ቢሊዮን ብር ውስጥ ከፌደራል መንግሥት ግምጃ ቤት 14.088 ወጪ እንደሚደረግ ታሳቢ ተደርጐ በጀቱ የተሰራ  ቀሪውን የካፒታል በጀት ለመሙላት የታቀደው ደግሞ ከእርዳታ፣ ከየመስሪያ ቤቱ ገቢና ከብድር እንደሆነ ያመለክታል፡፡

በበጀት ድልድሉ ቀመር መሠረት ለካፒታል በጀት የተያዘው ገንዘብ ከእርዳታ ይገኛል ተብሎ የታሰበው 5.98 ቢሊዮን ብር ሲሆን 3.29 ቢሊዮን ብር ደግሞ በብድር በሚገኝ ገንዘብ የካፒታል በጀቱን ወጪ ለመሸፈን ታቅዷል፡፡ ከመሥሪያ ቤቶች ገቢ ድርሻ ደግሞ 69.05 ቢሊዮን ብር ነው፡፡

ይህ የካፒታል በጀት ድልድል እንደሚያመለክተው ከ4ዐ በመቶ በላይ የሚሆነው ከእርዳታና ከብድር ይገኛል ተብሎ በሚታሰብ ገንዘብ መሸፈኑን ያሳያል፡፡ ይህም አገሪቱ ለዓመታዊ በጀትዋ ከእርዳታና ከብድር የሚገኘው ገንዘብ የበጀት ድልድሉ ከፍ እያለ መምጣቱን ያሳያል፡፡

የበጀት ድልድሉን አስመልክቶ የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትሩ ባቀረቡት ማብራሪያም ከውጭ የልማት አጋሮች ከሚገኝ መሠረታዊ አገልግሎቶች አሠጣጥ የበጀት ድጋፍ (Protection of Basic Services) እርዳታ 6.7 ቢሊዮን ብር እንደሚደርስ የሚጠበቅ ሲሆን ይህም መጠን ከ2ዐዐዐ በጀት የ40.5 በመቶ ብልጫ እንዳለው ማመላከታቸውም ይህንኑ ያረጋግጣል፡፡

የ2001 በጀት ዓመት የፌዴራል መንግሥት ገቢ ከአገር ውስጥ የፋይናንስ ምንጭ 32.1 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ በማቀዱ ገቢው ከ2ዐዐዐ በጀት ዓመት ክንውን ጋር ሲነፃፀር በ28.8 በመቶ እንደሚጨምር ታሳቢ ተደርጐ የተሰላ መሆኑን ያሳያል፡፡

ታክስ ያልሆኑ ገቢዎች ደግሞ 21.6 በመቶ እንደሚጨምር የተገመተና ከዚህም መካከል የኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒኬሽን የኢንቨስትመንት ገቢ ትልቅ ግምት እንደተሰጠው ያመለክታል፡፡ ኮርፖሬሽኑ በ2ዐዐዐ በጀት ዓመት ዘጠኝ ወራት ብቻ 1.2 ቢሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ማግኘቱን መግለፁ ይታወሳል፡፡

የቀጥታ ታክስ ገቢ ከ2ዐዐዐ በጀት ዓመት የ28  እድገት እንደሚያሳይ የተገመተ ሲሆን ይህም እቅድ የንግድ ትርፍ ገቢ ባለፉት ሦስት ተከታታይ ዓመታትና በዘንድሮ በጀት ዓመት የተገኘውን ውጤት ታሳቢ በማድረግ የተሰላ ነው፡፡

ቀጥታ ያልሆኑ የአገር ውስጥ ታክሶች ከ2ዐዐዐ በጀት ዓመት 38.7 በመቶ ከአፈፃፀሙ ግምት የ31.1 በመቶ እድገት እንደሚያሳይ ተገምቷል፡፡ 
 
< Prev   Next >