Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version

Friday
Nov 21st
Home arrow Sections arrow ለሕፃናት የገና ስጦታ ተበረከተላቸው
ለሕፃናት የገና ስጦታ ተበረከተላቸው E-mail
Sunday, 13 January 2008
የካፒታል ጋዜጣ ማኔጅመንት ሠራተኞች የገናን በዓል ምክንያት በማድረግ በኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ምክንያት ወላጅ አልባ ለሆኑ 50 ሕፃናት ልዩ ልዩ ዓይነት የስጦታ እቃዎችን አበረከቱ፡፡

ከአራት እስከ አሥር ዓመት ዕድሜ ላላቸው ለእነዚሁ ሕፃናት የተበረከቱላቸው ስጦታዎች ጫማዎች፣ የትምህርት ቤት መሳሪያዎችና አሻንጉሊቶች፣ ለወንዶች ኳስ ለልጃገረዶች ደግሞ የቪዲዮ መጫወቻዎች ናቸው፡፡ በዝግጅቱ ላይ ለተገኙ እንግዶች የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የሕይወት ኤች.አይ.ቪ ኤድስ መከላከያና ድጋፍ ሰጭ ድርጅት ተወካይ ሲስተር አብረኸት ግርማይ ናቸው፡፡ ይህን ፕሮግራም ካፒታል ከሕይወት ኤች.አይ.ቪ/ ኤድስ መከላከያና ድጋፍ ሰጭ ድርጅት እንዲሁም ከፕሮፕራይድ ኢትዮጵያ ጋር በመሆን ነው ያዘጋጀው፡፡

ትዕግስት ይልማ የካፒታል ጋዜጣ ማኔጂንግ ዳይሬክተርና ምክትል ዋና አዘጋጅ ..ከሕፃናቱና ከቤተሰቦቻቸው ጋር የገናን ዋዜማ አብረን በማሰለፋችን ከፍተኛ የሆነ ደስታ ይሰማናል.. ብላለች፡፡

በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል አቅራቢያ በሚገኘው ቤቶች ኤጀንሲ  አስተዳደር መምሪያ አዳራሽ በተከናወነው በዚሁ ስነ ስርዓት ላይ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣ የግል ሚዲያ ባለንብረቶች ተገኝተዋል፡፡

ከዚህም ሌላ አቶ ብርሃኑ ኃይሉ ማስታወቂያ ሚኒስቴርን በመወከል አቶ ቴዎድሮስ ተፈራ፣ እንዲሁም የአዲስ አበባ ሚሌኒየም ምክር ቤቱን በመወከል አቶ ቴዎድሮስ ዘውዴ ተገኝተዋል፡፡ 

 
< Prev   Next >