| ባንኩ ለደንበኞቹ ስልጠና ሰጠ |
|
|
| Wednesday, 18 June 2008 | |
![]() ስልጠናው በተሰጠበት ወቅት ![]() የህብረት ባንክ ኘሬዚዳንት አቶ ብርሃኑ ጌታነህ በዳዊት ታዬ ዓለም አቀፉን የወጪና የገቢ ንግድ አካሄድ ባለመገንዘብ ብዙ ነጋዴዎች ለከፍተኛ ወጪና ኪሣራ የሚደረጉት በአቀፍ ደረጃ የሚሰራባቸውን የንግድ ሒደቶች መከተል ባለመቻላቸው እንደሆነ ተጠቆመ፡፡ የዓለም ባንክ ግሩኘ የሆነው ኢንተርናሽናል ፋይናንስ ኮርፖሬሽንና (““ና ህብረት ባንክ በጋራ በተዘጋጀ ስልጠና ላይ እንደተገለፀው በአሁኑ ወቅት ያለውን ዓለም አቀፍ የንግድ ሒደት ባለመገንዘብና ሊደረጉ የሚገባቸው ጥንቃቄዎች ባለመደረጋቸው አስመጪና ላኪዎች ሲጐዱ ይታያል፡፡ ባሳለፍነው ቅዳሜ በግሎባል ሆቴል በተደረገ በዚሁ ስልጠና ላይ የተገኙ የህብረት ባንክ ደንበኞች በወጪና በገቢ ንግድ ሒደት ውስጥ የሚያጋጥማቸውን ችግር በዝርዝር ያስረዱ ሲሆን ስልጠናውን የሰጡት የዓለም አቀፍ ፋይናንስ ኮርፖሬሽን ባለሙያዎችም የችግሩ ምንጭ ምን እንደሆነና የዓለም አቀፍ አሠራሮችን መስፈርት ከኮንትራት አሞላል እስከ መጨረሻው ደረጃ ያለውን ሒደት በማሳየት የመፍትሔ አቅጣጫዎችን አመልክተዋል፡፡ በስልጠናው ዙሪያ ያነጋገርናቸው የህብረት ባንክ ኘሬዚዳንት አቶ ብርሃኑ ጌታነህ እንደገለፁት ከ” ጋር በመስራት ህብረት ባንክ የመጀመሪያው መሆኑን ጠቁመው ተከታታይ ሥልጠና ለደንበኞቻቸው እንደሚሰጡ ገልፀዋል፡፡ ደንበኞች አሁን በዓለም አቀፍ ያለውን አሠራር ከተገነዘቡ የባንኮችንም ሥራ ያቃልላሉ፡፡ ሌሎች ባንኮችም ተመሳሳይ የሆነ አሠራር ቢከተሉ በወጪና በገቢ ንግድ ደንበኞች የሚገጥማቸውን ችግሮች ለማስቀረት ይችላሉ፡፡ IFC ግሎባል ትሬድ ፋይናንስ ኘሮግራም የሚባል ሥር በማደግ ላይ ላሉ አገሮች ድጋፍ እየሰጠ የሚገኝ ሲሆን ይህንን ኘሮግራም ለማስፈፀም እገዛ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ ከነዚህ እገዛዎች መካከል ባንኮችንና በወጪና ገቢ ንግድ የተሰማሩ ነጋዴዎች በዓለም አቀፍ የንግድ ሂደት ግንዛቤ እንዲጨብጡ ማስቻልና በዓለም አቀፍ የንግድ ልውውጥ ለአስመጪና ላኪዎች የገንዘብ ዋስትና መስጠትን ያጠቃልላል፡፡ ለዚህም ተግባሩ የራሱ በጀት መድቦ ይሠራል፡፡ አስመጪና ላኪዎችን ምርት ሰያስገቡና ሲልኩ ምርቱን ከሚቀበላቸው እንዲሁም እቃ ከሚገዙት ኩባንያ ጋር ሊኖር ስለሚገባው ግንኙነት ብዙ ነጋዴ በቂ ግንዛቤ የለም፡፡ እንዲህ ዓይነቱን ክፍተት ለመሸፈን IFC ትልቅ እገዛ በማድረግ ይጠቀሳል፡፡ በወጪና ገቢ ንግድ ሰንሰለት ውስጥ ብዙ ነገሮች ይካተታሉ እዚህ ውስጥ ኮንትራንት፣ ክፍያ፣ እቃ መጫንና የመሳሰሉት ይጠቀማሉ፡፡ ሆኖም እነዚህን በጥንቃቄ ባለመጠቀም ጉዳት ሊመጣ ይችላል፡፡ አንዳንድ አገሮች በተለይ እንደ ጃፓን ያሉና ሌሎችም አገሮች ለወጪና ለገቢ ንግድ የሚጠይቁት ዋስትና ከባድ በመሆኑ ይህንን ጫና ለማቃለል እንደ IFC ያሉ አገሮች ጋራንቲ ስለሚሰጡ የእኛ አገር ነጋዴዎችም በዚህ እድል ለመጠቀም እድል ይፈጥርላቸዋል፡፡ ለአንድ ምርት ማረጋገጫ ይሰጥ ወይም ኮንፈርም ይደግ ተብሎ ከተደረገ በኋላ እቃው ተይዞ እስኪመጣ ሦስት ወርም አንዳንድ እቃዎች ደግሞ ተመርተው እስኪመጡ ድረስ ከዚያም በላይ ሊወሰድ ይችላል፡፡ ስለዚህ ኮንፈርምድ እንዲሆን ከተደረገ የአገር ውስጥ ባንኮች በውጭ ባንኮች ውስጥ ካሽ ኮላተራል እንዳይዝ ስለሚደረግ ገንዘቡ እንዳይሰራ ያደርጋል፡፡ እንደዚህ ዓይነት ችግር ሲገጥመን ከውጭ ያለው አምራች ሌተር ኦፍ ክሬዲቱ በግድ ኮንፈርምድ ይሁንልኝ ብሎ ከወሰነ የተባለውን ካሽ ማስያዝ አለበለዚያም ጥሩ ግንኙነት ላላቸው የውጭ ባንኮች ጋር ዋስትና እንዲወስዱ ማድረግ ነው፡፡ ስለዚህ አሁን እንደ IFC ካሉ ድርጅቶች ጋር መስራቱ ለማስያዥ (ወይም ኮራቶራል እንዲሆን) የሚቀመጠው ገንዘብ እንዲንቀሳቀስና እነሱ ጋራንቲውን እንዲሰጡ ያስችላል፡፡ ኮንፈርምድ ይሁን ካሉ ካሽ ካለን ካሽ ማስያዝ ነው ያለት አቶ ብርሃኑ ይሔ ደግሞ ካሽ ፈንዳችንን ያጣብብናል፡፡ ስለዚህ የምናደርገው ከአንዳንድ የኮርስፖንደንት ባንኮች ጋር ባለን የረዥም ጊዜ ግንኙነት ምክንያት ክሬዲት ላይን ይሰጡናል፡፡ ኮንፎርም ያደርጉልናል፡፡ ለምሳሌ ሲቲ ባንድ ኮሜርሻል ባንክ ስታንዳርድ ቻርተርድ ባንክና የመሳሰሉት ባንኮች ከእኛ ጋር ያላቸውን ግንኙነት ግምት ውስጥ በማስገባት እኛ ኮሮቸራል ካሻችንን ከምናዝይዝ እነሱ ጋራንቲ ይሰጡናል ያሉት አቶ ብርሃኑ እንዲህ ዓይነቱን ተመሳሳይ እድል ለማግኘት ከ” ለመስራት የሚያስችል ግንኙነት ጀምረናል ብለዋል፡፡ በመሠረቱ ከኮርስፖርደንት ባንኮች ውስጥ አብዛኛዎቹ ጥሩ ግንኙነት ስላለንና ኃላፊነታችንን እንዴም ተስተጓጉሎብን ስለማናውቅ በቂ ጋራንቲ አለን ብለዋል፡፡ እንዲህ ዓይነት ስልጠናዎች ለደንበኞች መስጠት ዓለም ከደረሰበት የንግድ ልውውጥ ሂደት ጋር እንዲጓዝ ያደርጋል፡፡ ዓለም አቀፋዊ አሠራሮችን አለመረዳትም ክፍተት በመፍጠር በተለያዩ ጊዜ ላኪዎች፣ አስመጪዎችና በሻጮች መካከል አለመግባባትና ችግር ይፈጠራል፡፡ በሌላም በኩል የመደራደር አቅማቸው አነስተኛ በመሆኑ እንዲህ ያለ ስልጠናዎች ይህንንም ክፍተት ይሸፍናል፡፡ እንደ አቶ ብርሃኑ ገለፃም የስልጠናው ዋና ዓላማ ብዙ ውጣ ውረድ ያለበትንና በኢንፖርትና በኤክስፖርት ደረጃ ያሉትን ዓለም አቀፍ ሒደቶች ተረድቶ ጥንቃቄ በተመላበት ሁኔታ እንዲሠሩ ለደንበኞቻችን ግንዛቤ ማስጨበጥ ነው፡፡ በስልጠናው ላይ ከ36 በላይ የሚሆኑ አስመጪና ላኪዎች የባንኩ ደንበኞች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡ የስልጠናው ተሳታፊዎች ከስልጠናው ብዙ መማራቸውንና ሌሎች ሠልጣኞችም ይህንን ዓይነቱን እድል እንዲያገኙ መደረግ አለበት ብለው፡፡ ይህንንም ሥራ ከባንክ ውጭ ያለ እንደ ንግድ ምክር ቤቶች ያሉ ተቋማት ኃላፊነቱን መውሰድ ይገባቸዋል ባዮች ናቸው፡፡ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |