| አፍሪካውያንና ኦሊምፒክ |
|
|
| Wednesday, 18 June 2008 | |
|
ትዮጵያ የኦሊምፒክ ኮሚቴ አባል በመሆን እ.ኤ.አ በ1928ቱ የአምስተርዳም ኦሊምፒክ ለመካፈል ጥያቄ አቅርባ የተሰጣት መልስ ““. የአፍሪካ አገሮች ኢትዮጵያን ጨምሮ የኦሊምፒክ ጨዋታዎችን ለማስተናገድም ሆነ በውድድሮቹ ለመካፈል ብቃት የላቸውም”“. የሚል እንደነበር “ኢትዮጵያ በኦሊምፒክ” የተሰኘና በኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ በ1995 ዓ.ም የተዘጋጀ መፅሔት ያስረዳል፡፡
በአፍሪካውያን ብቃት ላይ ቅኝ ገዥዎች የነበራቸው የተሳሳተ አመለካከት በነፃነት ትግል ተወገደ፡፡ የመጀመሪያው አህጉር አቀፍ የአትሌቲክስ መድረክ እ.ኤ.አ ታህሳስ 27 ቀን 1974 በጋና በማስተናገድ የመላ አፍሪካ ዩኒቨርሲቲ ጨዋታዎች እውን ሆነ፡፡ ይህን መድረክ ለማሳካት እ.ኤ.አ በ1971 በናይጄሪያ ሌጐስ በተደረገ ልዩ ስብሰባ ውድድሩን የሚመራ የአፍሪካ ዩኒቨርሲቲ ስፖርቶች ፌዴሬሽን እንደተቋቋመ ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የተገኘ መረጃ ያስረዳል፡፡ ከአህጉር አቀፍ ውድድር በፊት በቀጣና ደረጃ የምዕራብ አፍሪካ ዩኒቨርሲቲ ጨዋታዎች ከ1965 ጀምሮ ይካሄዱ እንደነበርና በምሥራቅ አፍሪካም፣ በኬንያና በተለያዩ ቦታዎች እነዚሁ የዩኒቨርሲቲ ጨዋታዎች እንደተካሄዱ መረጃው ያሳያል፡፡ (የአፍሪካ ፈርጦች መፅሔት 2000) የማይረሣ ታሪክ ታሪክ መሥራት የሚለው አባባል በስፖርት ዓለም ውስጥ ተደጋግሞ ይጠቀሳል፡፡ ይሆናል፡፡ የሞሮኮዋ ናዋል ኤል ሞትዋኬል እ.ኤ.አ በ1984ቱ የሎስ አንጀለስ ኦሊምፒክ የ400 ሜትር መሰናክል ዝላይ ስታሸንፍ በሚቀጥሉት ትውልዶች ሁሉ የሚታወስ ታሪክ መሥራት የቻለች ሯጭ ለመሆን በቅታለች፡፡ በዓለም አቀፍ የግራድ ፕፋክስ ሻምፒዮናዎች ላይ በመወዳደር የተሳካላት የ22 ዓመቷ ሯጭ ናዋል የኦሊምፒክ ድል በተቀዳጀችበት ወቅት በአሜሪካ የሚገኘው የአይዋ ስነት ዩኒቨርሲቲ ተማሪ ነበረች፡፡ ድሏ በታላቁ የኦሊምፒከ መድረክ ውድድሮች በአፍሪካ ሴት የተገኘ የመጀመሪያው የወርቅ ሜዳሊያ ነበር፡፡ ይህም በአፍሪካና በዓረብ ለሚኖሩ ሴት ስፖርተኞች ሰብሮ መውጫ መንገድ ፈር የቀደደ ነበር፡፡ በአንፀባራቂ ድሎች ከተሞላው የውድድር ዘመኖቿ በኋላ ኤል ሞተዋኬል የስፖርታዊ አስተዳደር ሥራዎችን ስትሠራ ቆይታለች፡፡ እ.ኤ.አ በ1995 የዓለም አቀፍ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማኅበር አባል ስትሆን ከሶስት ዓመት በኋላ ደግሞ የዓለም አቀፍን ኮሚቴን ተቀላቀለች፡፡ እንደ ፕሬዚዳንትነቷ እ.ኤ.አ በ2012 የክረምት ኦሊምፒክ አዘጋጅ አገርን በመምረጥ አኳያ ባሳየችው ሚና ዓለም አቀፍ እውቅናን አትርፋለች፡፡ ባለፈው ዓመት የሞሮኮ ስፖርት ሚኒስቴርነት ማዕረግ ካገኘች በኋላ ወጣት ሴቶች በስፖርት ያላቸውን ተሳትፎ ለመጨመር ከፍተኛ እንቅስቃሴ እያደረገች ትገኛለች፡፡ (ልዩ የአትሌቲክስ መፅሔት 2000) ባሮን ፒየር ዴ ኩበርቲን የመጀመሪያው ኦሊምፒክ ጨዋታ በዓለም አቀፍ ደረጃ እንዲደረግ ሃሳቡን ያፈለቀው እንግሊዛዊው መምህር ሲሆን፣ ለዚህ ወሳኝና አስፈላጊ ራዕይ ከግብ መድረስ የጐላ ሚና የተጫወቱት ግን ፈረንሣዊው ባሮን ፒየር ዴ ኩበርቲን ናቸው፡፡ በእግር ኳስ የተዋጣላቸው ተከላካይና ቦክሰኛ እንደነበሩ የሚነገርላቸው ኩበርቲን እ.ኤ.አ በ1887 ወደ እንግሊዝ በሄዱበት ወቅት ተማሪዎች በየትምህርት ቤቶቻቸው ሲያደርጉት የነበሩትን የአትሌቲክስ ውድድሮች ስለተመለከቱ መሰል ውድድሮችን በዓለም አቀፍ ደረጃ የማከናወኑ ሃሳብ ተከሰተላቸው፡፡ በዚያን ጊዜ በአንድ ትምህርት ቤት ያስተምር የነበረው እንግሊዛዊው ቶማስ ኦርኖልድ በራግቢ ስፖርት ተማሪዎችን እያሰለጠነ ያወዳድር ስለነበረ መነሻ ሆነላቸው፡፡ በብርቲን በራዕያቸው ኦሊምፒክ የሰው ልጆች አንድነትንና ሠላምን የሚያጐለብት መድረክ አድርገው ቀርፀውታል፡፡ ይህን ሐሳባቸውን ተግባራዊ ለማድረግ እ.ኤ.አ በ1889 ዓለም አቀፍ ኦሊምፒክ ኮሚቴ (አይ ኦ ሲ) እንዲመሠረት ፈር ቀደዱ፡፡ ለዚህም የፈረንሳይ መንግሥት ከፍተኛ እገዛ አድርጐላቸዋል፡፡ በእቅዱ መሠረት የመጀመሪያው ኦሊምፒክ ጌምስ ሊደረግ የታሰበው እ.ኤ.አ በ1900 በፓሪስ ቢሆንም ከብርቲን ለውድድሩ በአፋጣኝ መጀመር ከፍተኛ ጉጉት ስላሳደረባቸው እ.ኤ.አ በአቴንስ እንዲካሄድ ተደርጓል፡፡ (አቴንስ ልዩ መፅሔት 2004) ድርና ማግ ለኢትዮጵያውያን ልብስ የሚሆን ድርም ሆነ ማግ በኢትዮጵያውያን ሴቶች ብቻ ተፈትሎ የሚገኝ ነበር፡፡ የሚሸጥ ጨርቅ የሚገኘው ከአውሮፓ ወይም ከኤስያ ተሰርቶ የሚመጣው ብቻ ነው፡፡ ይህም ከውጭ የሚመጣው ጨርቅ ዋጋው ውድ በመሆኑ ከጥቂት ሐብታሞች በስተቀር የሚገዛና የሚለብሰው አልነበረም፡፡ ዳግማዊ አጤ ምኒልክ የሸማኔዎችን አሰራር ለማሻሻል በተነሱበት ጊዜ ሸማኔዎች ጉድጓድ ቆፍረው መሥራታቸው የሚቀርበት ዘዴ እንዲፈለግ ሲመክሩ በውጭ አገር ድር ወይም ማግ በመኪና ተፈትሎ በብዛት እንደሚሸጥ ሰሙ፡፡ ከዚህ በኋላ አስመጡልኝ ብለው በ1897 ዓ.ም ድር መጣ፡፡ ስለዚያን ጊዜው ድር አመጣጥ ጉዳይ ዲፕሎማቲክ “ኤንድ ኮንሰለር ሪፖርት ፎር ላይ ““. ምኒልክ ጨርቁን ከማስመጣት ይልቅ ክሩ እንዲመጣ በማድረጋቸውና ልብሱ አገር ውስጥ በመሠራቱ የልብስ ዋጋ ረከሰ፡፡ ክሩም ለአበሾች መን የተስማማ ነው፡፡ ይህም በመሆኑ በውጭ የተሰራ ጨርቅ ዋጋው እየቀነሰ ሄደ፡፡”“. (አጤ ምኒልክ 1984፣ ጳውሎስ ኞኞ) የክፋት ተጋብኦነት ከሰል የሚሸጥ ሰው ልብስ አጣቢን አለው ለቤት ኪራይ ብለኸ ገንዘብ የምትከፍለው ቀሪ እንዲሆንልኸ አብረኸ ከኔ ጋራ ኪራይ ሳትከፍል ተቀምጠኸ ብትሠራ ይበቃናል አንድነት እንኑር፡፡ ልብስ አጣቢ ሰምቶ ይህንኑ ምክር አመሰግናለሁ በማሰብኸ ለኔ ግን የማይጠቅመኝ ነው ካንተ ጋር መሆኔ ታጥቦ ታጥቦ ጭቃ የሚባለው ተረት እንደሚደርስብኝ አስበኸ ተመልከት እኔ የማጥበው ልብስ ካንተ ከሰል ጋራ ይቆሽሽ የለም ወይ አብረን ስንሠራ ከሰል ለነጭ ልብስ ነውና ጠላት የማይሆን ሐሳብ ነው ሲል መለሰለት፡፡ ከሰል ለነጭ ልብስ እንዲሆነው አጥፊ ከክፉም የዋለ ክፋትን አትራፊ ከመሆን አይድንም ምን ቢጠነቀቅ ዐመል ሳይበላሽ ጠርቶ እንዲጠበቅ ከመጥፎ ጓደኛ ይገባል መራቅ፡፡ (ከበደ ሚካኤል፣ የቅኔ ውበት፣ 2000) ገራገር ከንቲባዋ ለአባቶች ቀን ነፃ ኮንዶም አደሉ በሰሜናዊው ሜክሲኮ በምትገኘው ስኩቢዶ ከተማ ወንዶች ለየት ባለ መልኩ መልካም የአባቶች ቀን ማክበራቸውን አሶሽየትድ ፕሬስ ዘግቧል፡፡ ለወንዶች አስደሳች የአባቶች ቀን የተባለው ደግሞ ቀኑ የሚከበርበት ቀን ከንቲባ ማርገሬት ማርቲንዝ ለወንዶች ነፃ ኮንዶምና የወሲብ ማነቃቂያ በማደላቸው ነበር፡፡ “ስጦታው በወንዶች የስነ ተዋልዶ የጤና ችግሮች ላይ ግንዛቤ ለመፍጠር የተደረገ ነው” ሲሉ ከንቲባዋ ተናግረዋል፡፡ ከንቲባ ማርቲንዝ እንዳሉት “ጠንካራ ቤተሰብ ጤነኛ ወንድ ይፈልጋል፡፡ ጤናማ የወሲብ ህይወት ደግሞ የጠቅላላ ጤንነት ክፍል ነው” በኮንዶምና በወሲብ ማነቃቂያ እንክብል ዘመቻው ላይ ዶክተሮችና ነርሶች ተሳታፊ የሆኑ ሲሆን ነፃ የጤና ምርመራም ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡ በመሳቋ ከሥራ ተባረረች በፍሎሪዳ በሚገኝ ምግብ ቤት ውስጥ ትሠራ የነበረች አስተናጋጅ በሥራ ላይ እያለች በመሣቋ ከሥራ ለመባረር በቅታለች፡፡ ሎካል 6 ኒውስ እንደዘገበው በኒው ፐርት ሪቺ በሚገኘው ትሪኒቲ ግሪል ትሠራ የነበረችው አስተናጋጅ ከሥራዋ ለመባረር የበቃችው ከዚህ ቀደም ሰምታ የማታውቀው ዓይነት ትዕዛዝ በምግብ ቤቱ ሊስተናገድ የመጣ ሰው ስለጠየቃት ነበር፡፡ “በመጠጥ ክፍል ውስጥ እንግዳ ነበረኝ፡፡ የቤቱ ባለቤት መጣና ፣እባክሽ አትሳቂ፣ አለኝ፡፡ እኔም እንግዳውም ሳቅን፡፡ አስከትዬም ፣እውነትህን ነው?፣ ስል ባለቤቱን ጠየቅኩት፡፡ እሱም ድጋሚ ከሳቅሽ ከሥራ አባርርሻለሁ አለኝ” በማለት የገለፀችው የሆቴል ቤቱ አስተናጋጅ ዳራ ኮሊኦስ ነች፡፡ ኮሊኦስ ወዲያው ነበር ከሥራ የተባረረችው፡፡ ጓደኞቿን የተለየ ሳቅ ስቃ እንደሆነ ጠይቃ ያገኘችው መልስ የተለየ እንዳልነበረ ነው፡፡ ሆኖም አሰሪዋ “እንግዶች ለምን እንደዚህ ሳቀች ብለው አስተያየት ባያቀርቡም እኔ ቤቴ ፀጥታ የሰፈነበት እንዲሆን እፈልጋለሁ” ብሏል፡፡ የሴቶችን ብብት የሚያሸተው ተቀጣ የ36 ዓመቱ የሲንጋፖር ነዋሪ የ14 ዓመታት የእስር ቅጣት የተወሰነበት ሴቶችን በማጥቃትና ብብት በማሽተት ወሲባዊ ትንኮሳ በመፈፀሙ ነው፡፡ ሮይተርስ እንደዘገበው ሰውየው ከዚህ ቀደምም ከሃሽሽና ከወሲብ ጋር በተያያዘ ጥፋት ሲፈፅም ቆይቷል፡፡ ባለፉት 15 ወራት ብቻ 23 ሴቶችን በአሳንተርና በቤታቸው ውስጥ ፆታዊ ትንኮሳ ፈፅሞባቸዋል፣ ብብታቸውንም አሽትቷል፡፡ አንዲት የቤት እመቤት ለፖሊስ ባመለከተችው መሠረት በቁጥጥር ስር የዋለው ሰው በሲንጋፖር ህግ መሠረት ለወንድ ወንጀለኞች ተፈፃሚ የሚሆነውን 18 ጊዜ የመቀመጫ ላይ ግርፊያም ይጠብቀዋል፡፡ ከመጠን ያለፈው ሳቅ መዘዝ ክሪስ ኮከር በቢቢሲ ቲቪ የሚተላለፈውን “ሀቭ አይ ጐት ፎር ዩ” የተሰኘውን ፕሮግራም እያየ ነበር ከመጠን ያለፈ ሣቅ ይስቅ የነበረው፡፡ የ36 ዓመቱ ኮከር ከሳቁ ብዛት ሶፋ ላይ ይወድቃል፡፡ እሱ ከሚኖርበት ክፍል ስር የነበረ ጐረቤቱ ድምፅ መስማቱን ጠቅሶ ለፖሊስ ያሳውቃል፡፡ “ከሳቄ ብዛት የተነሳ ወደቅኩ፡፡ ከዚያም ከመሬት ተነስቼ እንደገና ፕሮግራሙን መከታተል ጀመርኩ፡፡ ወዲያው በሬ ተንኳኳ ፖሊሶች ነበሩ” ሲል ኮከር ለቢቢሲ ገል”ል፡፡ ሚ/ር ኮከር በወቅቱ ፖሊሶቹን ለማነጋገርም ሆነ ለመተግበር ፈቃደኛ አልነበረም፡፡ በመሆኑም ፖሊሶች በቤቱ ውስጥ አይን የሚቆጠቁጥ ስፕሬይ በመንፋት ከቤቱ ይዘውት ሄደዋል፡፡ ሌሊቱንም ያሳለፈው በእስር ቤት ውስጥ ነበር፡፡ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |