| ኢትዮጵያ ኋላ ቀር አስተራረስዋን... |
|
|
| Sunday, 22 June 2008 | |
|
ኢትዮጵያ ኋላ ቀር አስተራረስዋን እንድታስተካክል ተጠየቀ
በጋዜጣው ሪፖርተር ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት የገጠማትን የምግብ እጥረት ሣቢያ በሚሊዮን የሚቆጠር ህዝቧ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸውና ይህንን ሁኔታ ለማሻሻልም አገሪቱ ኋላ ቀር የአስተራረስ ዘዴዋን ማስተካከል እንዳለባት የዓለም ባንክ አስታወቀ፡፡ ወቅቱን የጠበቀ ዝናብ ባለመኖሩ ለ4.5 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን አስቸኳይ የምግብ እርዳታ እንደሚያስፈልግ የገለፀው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በምስራቁ የሃገሪቱ ክፍልም የምግብ ዋጋ ንረቱንም መባባሱን ከትናንት በስቲያ የተላለፈው የሮይተርስ ዘገባ ያመለክታል፡፡ በዓለም ባንክ ሲኒየር ቫይስ ኘሬዚዳንትና ዋና ኢኮኖሚስት ጀስቲን ሊን ይፋ እንደሚሉት ..ኢትዮጵያ ባለፉት ሦስትና አራት ዓመታት ተጨባጭ የኢኮኖሚ እድገት አስመዝግባለች፡፡ ይሁንና የተወሰኑ የሃገሪቱ ክፍሎች በሚከተሉት ኋላ ቀር የአስተራረስ ዘዴ ለድርቅ ተጋልጠዋል.. ከሰሀራ በታች ካሉ አገሮች በሕዝብ ብዛቷ ሁለተኛ ደረጃ ላይ የምትገኘው ኢትዮጵያ በከፍተኛ ሁኔታ ችግር ውስጥ ላሉ በተለይም በደቡብና በደቡብ ምሥራቅ አካባቢ ለሚገኙ ሰዎች እርዳታ የሚውል አራት መቶ ሺህ ሜትሪክ ቶን እህል ለመግዛት 325 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር እንደሚያስፈልጋት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ማስታወቁንም ይኸው የሮይተርስ ዘገባ ያመለክታል፡፡ 85 በመቶ በመሆነው የኢትዮጵያ ሕዝብ ውስጥ 81 ሚሊዮን የሚሆነው ከእጅ ወደ አፍ በሆነ ባህላዊ የአስተራረስ ዘዴ የሚጠቀም በመሆኑ ይህ ሊሻሻል እንደሚገባው ጀስቲን ሊን ይፉ ተናግረዋል፡፡ ..ባለው መልካም የአየር ፀባይ፣ የተለያዩ የተፈጥሮ ሀብቶችና የሰው ኃይል በአገሪቱ ይህ ነው የሚባል ለውጥ ማምጣት አስቸጋሪ ይሆናል ብዬ አላስብም.. በማለትም በኢትዮጵያ ጉዳይ ለሮይተርስ በሰጡት አስተያየት ገልፀዋል፡፡ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |