Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Thursday
Aug 28th
Home arrow Sections arrow ከድርቁ ችግር ጋር በተያያዘ...
ከድርቁ ችግር ጋር በተያያዘ... Print E-mail
Sunday, 22 June 2008
ከድርቁ ችግር ጋር በተያያዘ የዩኒሴፍ ኃላፊዎች ኢትዮጵያን እየጐበኘ ነው

ድርቅ በታየባቸው በደቡብና ምስራቅ ደቡብ ኢትዮጵያ የዩኒሴፍ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ለአራት ቀናት የሚቆይ ጉብኝት እያደረጉ መሆኑን የተባበሩት መንግሥታት ዜና አገልግሎት ዘገበ፡፡
ምክትል ዳይሬክተሩ ከመንግሥት ባለሥልጣናት፣ ከተባበሩት መንግሥታት ኃላፊዎችና ከእርዳታ ድርጅቶች ጋር ይወያያሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ በአጠቃላይ 4.6 ሚሊዮን ህዝብ ከበልግ ዝናብ እጥረትና ከዋጋ ንረት የተነሳ የምግብ እጥረት እንዳለበት ዘገባው ያትታል፡፡

በተለይ በኦሮሚያ በሶማሊያና በደቡብ ህዝቦች ክልል ድርቁ የከፋ መሆኑንና 75 ሺ የሚገመቱ ህፃናትም ተጠቂ መሆናቸው ተዘግቧል፡፡

በተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ ጉዳዮች ቢሮ ባለፈው ወር ወደ 325 ሚሊዮን ዶላር እርዳታ ሰጥቷል፡፡


ኘሬዚዳንት ሙሴቪኒ ለዳርፉር ቀውስ መፍትሄ እንዲፈለግ ጥሪ አቀረቡ

ለአምስት ዓመታት የዘለቀውን የአረቡንና የጥቁር አፍሪካውን ግጭት የእስላማዊው ድርጅት (OIC) አባል ሀገራት መፍትሄ እንዲፈልግለት የዩጋንዳው ኘሬዚዳንት ጥሪ አቀረቡ ሲል ሱዳን ትሪቡን ከካምፓላ ዘገበ፡፡

የኦርጋናይዜሽን ኦፍ እስላሚክ ኮንፈረንስ (OIC) ባደረገው ስብሰባ ላይ ኘሬዚዳንቱ እንደተናገሩት አባል አገራቱ የደቡብ ሱዳኑን ግጭት ለመፍታት ጣልቃ መግባት አለባቸው፡፡ ይህንን ካላደረጉ ግን ግጭቱ የድርጅቱን ህብረት ሊያናጋ ይችላል ብለዋል፡፡

"ጥቁሮች ብቻ ይሞታሉ ብላችሁ አትጠብቁ፤ ከሆነም እኛም ዝም ብለን አንቀመጥም" ሲሉ አስጠንቅቀዋል፡፡

የተባበሩት መንግሥታት ሪፖርት እንደገለፀው ከሆነ ከ2ዐዐ3 ጀምሮ በዳርፉር ቀውስ 30"000 የሚደርሱ ሰዎች ሲሞቱ 20.5 ሚሊዮን የሚሆኑት ደግሞ ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል፡፡



ባንኪሙን ፆታዊ ጥቃት እንዲቆም አሳሰቡ

የተባበሩት መንግሥታት ዋና ፀሃፊ ባንኪሙን ጦርነትን አስታኮ እየጨመረ የመጣው የሴቶች ፆታዊ ጥቃት እንዲቆም ለድርጅቱ ባለሥልጣናትና ለተሰብሳቢዎች አሳሰቡ፡፡

"በአንዳንድ ህብረተሰብ ውስጥ በሴቶች ላይ የሚደርሰው ጥቃት ይፋ አይወጣም፡፡ ስለዚህም ሴቶቹ ከችግራቸው ለመላቀቅ አልቻሉም" ሲሉ በጦርነት አካባቢዎች የሴቶችን ጥቃት ለመከላከል በሚወያየው ስብሰባ ላይ ተናግረዋል፡፡

ጥቃቱን ለማስቆም የተቀናጀ ስትራቴጂ ስለሚጠይቅ ሁሉም ተባብሮ መሥራት እንዳለበትና ድርጅታቸውም ሆነ እራሳቸው ባንኪሙን የሴቶችንና ህፃናትን ጥቃት ለማስቆም እስከ መጨረሻው እንደሚሰሩ ገልፀዋል፡፡

ምክትል ፀሃፊዋ ሚስተር አሻ ሮዝ ሚግሮ እንደገለፁት "በጦርነት አካባቢ በሚደርሱ አስከፊ ወንጀሎች ላይ በሚደረገው የደህንነት ሥራ ሴቶችን ከወንዶች እኩል ማሳተፍ በቂ ውጤት ያስገኛል" ብለዋል፡፡



በኮንጐ የሰብአዊ መብት ረገጣው አልቆመም

በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጐ የመንግሥት ወታደሮች፣ ፖሊስና ታጣቂዎች የሰብአዊ መብት ረገጣ እንደሚያደርጉ የተባበሩት መንግሥታት ዘገበ፡፡

ድርጅቱ እንደዘገበው ከሆነ የመንግሥት ወታደሮችና ፖሊስ አስገድዶ በመድፈርና በሌሎችም ወንጀሎች ተሳትፈዋል፡፡

እስካሁን 2 የግድያ፣ 13 አስገድዶ የመድፈር እና ሌሎችም 1ዐዐ የሚሆኑ የዝርፊያ ወንጀሎች የተፈፀሙ ሲሆን ጥፋተኛ ወታደሮችም ከ5 እስከ 15 ዓመታት በሚደርስ ቅጣት ወህኒ ገብተዋል፡፡ ወህኒ ቤት ሰብረው የሚወጡ ወንጀለኞችም ከአገሪቱ መንግሥት ቁጥጥር ውጪ መሆናቸውን ዘገባው አመልክቷል፡፡
 
< Prev   Next >