Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
Sep 07th
Home arrow Sections arrow በላይቤሪያ ሰላም አስከባሪዎች...
በላይቤሪያ ሰላም አስከባሪዎች... Print E-mail
Sunday, 13 January 2008

በላይቤሪያ ሰላም አስከባሪዎች በሴቶች ላይ የሚያደርሱት ጥቃት ቀነሰ

በላይቤሪያ የተባበሩት መንግስታት ሰላም አስከባሪ አባላት በአገሪቱ ሴቶች ላይ የሚፈጽሙትን መሲባዊ ጥቃትና ብዝበዛ በተመለከተ የሚቀርቡ ሪፖርቶች በግማሽ መቀነሳቸውን አፍሮል ኒውስ ዘግቧል፡፡

በቅርቡ የወጣው ሪፖርት በ2006 ወጥቶ ከነበረው የፆታዊ ጥቃት መጠን ጋር በእጅጉ የተለያየ ነው ተብሏል፡፡

የጥቃቱ መቀነስ የሰላም አስከባሪ ልዑክ ሪፖርት በሚደረጉ ጉዳዮች ላይ የሚወስደውን ርምጃ በተመለከተ ይፋ መረጃ የመስጠቱ ውጤት መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

ልዑኩ ከላይቤሪያ መንግስትና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር በመሆን ጥቃቱን ለማስቆም በመሥራቱ እንደሚቀጥል ኃላፊው ሜጀር ጄኔራል ሙሐመድ ጣሂር መግለፃቸውንም ዘገባው አስነብቧል፡፡

ከዚህ ሌላ በሴቶችና በህፃናት ላይ የመፈፀሙ ወሲባዊ ጥቃትና ብዝበዛዎችን በተመለከተ ህዝቡን የማሳወቅ ሥራው እንደሚቀጥል ተጠቁሟል፡፡

 
< Prev   Next >