Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
Sep 07th
Home arrow Sections arrow ሞቃዲሾ በደረሰው ፍንዳታ ሦስት...
ሞቃዲሾ በደረሰው ፍንዳታ ሦስት... Print E-mail
Wednesday, 25 June 2008
ሞቃዲሾ በደረሰው ፍንዳታ ሦስት ወታደሮች ሞቱ

በሶማሊያ መንግሥት ወታደሮች መኪና ላይ በደረሰው ፍንዳታ ሦስት የመንግሥት ወታደሮች መሞታቸውንና በአራት ሰዎች ላይ የመቁሰል አደጋ መድረሱን ሸበሌ ሚዲያ ኔትወርክ ከሞቃዲሾ ዘገበ፡፡
ፍንዳታው ከሞቃዲሾ ከደረሰ በኋላ በመኪናው ውስጥ የነበሩት ወታደሮች መሞታቸውን የዓይን እማኞች የገለፁ ሲሆን ስለፍንዳታው ከመንግሥት ባለሥልጣናት በኩል ምንም ዓይነት አስተያየት አለመሰጠቱን ዘገባው ያመለክታል፡፡

በሶሪያ የኔውክለር ፍተሻ ምንም መረጃ አልተገኘም

ሶሪያ በድብቅ ገንብታለች የተባለውንና ከዘጠኝ ወራት በፊት እስራኤል ያፈነዳችውን የኒውክለር ማዕከል የተባበሩት መንግሥታት ኒውክለር ፈታሾች አሰሳ እያደረጉ መሆናቸውን ሮይተርስ ከቪየና ዘገበ፡፡

የእስራኤል ወታሮች የደበደቡት በሰሜን በረሃማ ክፍል በኪባር የተገነባውን የወታደሮች ካምፕ ነው፡፡ በማለት ሦርያ ማስተባበሏንም ያመለክታል፡፡

ፈታሾቹ በሦሪያም ሆነ በቪየና አውቶሚክ ሃይልን በተመለከተ ያገኙት ማስረጃ የለም፡፡

ፍተሻው ምንም እንኳን አንገብጋበ ጉዳይ ቢሆንም ፕሬዚዳንት በሽር አልአሳድሞ ሆነ የሞርየ ባልሥለጣናት ምንም ከማድረግ ተቆጥበው ዝምታን እንደመረጡ ተዘግቧል፡፡

ከ2003 ጀምሮ በምርመራ ስር የምትገኘው ሦርያ በሰሜን ኮርያ ዕርዳታ የማዕከሉን ግንባታ እያጠናቀቀች መሆኗንና በሰሜን ኮርያ ስርዓተ ሙከራ ማድረጓንም በዘገባው ተገል”ል፡፡

የነዳጅ ዋጋ ንረት በኔፓል ከፍተኛ ቁጣ ቀሰቀሰ


በነዳጅ ዋጋ ንረት ምክንያት የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች የማቆማቸው በነዋሪዎች ከፍተኛ ቁጣ መቀስቀሱን ቢቢሲ ዘገበ፡፡
የነዳጅ ዋጋ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ከ25 በመቶ በላይ ጨምሯል፡፡ መንግሥት ቅሬታችንን እንድናሰማ ከልክሎናል በማለት የትራንስፖርት ድርጅቶቹ ተናግረዋል፡፡
ኔፓል በዓለም አንደኛ ድሃዋ አገር መሆኗም በተማሪዎች ቁጣ መቀስቀሱንና መንግሥት የዋጋን ንረት ለማረጋጋት እንደሚሞክር ስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡
በነዳጅ ዋጋ በመናሩ በኔፓል ላለፉት ስምንት ዓመታት የትራንስፖር ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩንም ቃል አቀባዩ ለሮይተርስ ገልፀዋል፡፡
ለተማሪዎች የትራንስፖርት ክፍያ 45 በመቶ ቅናሽ እንደሚደረግላቸውም የአገሪቱ ባለሥልጣናት ሰኞ መግለፃቸውም ተዘግቧል፡፡  

በእስራኤል የሮኬት ፍንዳታ ደረሰ

በእስራኤል ድንበር ላይ ቢያንስ ሁለት ሮኬቶች ትላንት መፈንዳታቸውን ቢቢሲ ዘገበ፡፡ በመጀመሪያው ፍንዳታ ምንም ሰው ባይጎዳም ፍንታው ግን ጠብ አጫሪነት መሆኑን እስራኤል አስታወቀች፡፡

እስላሚክ ጂሀድ በበኩሉ አፀፌታውን የሰጠሁት በዌስት ባንክ ለተገደሉብኝ ታጣቂዎች የበቀል እርምጃ ለመውሰድ ነው ብሏል፡፡

እስራኤል ምን ዓይነት እርምጃ እንደምትወስድ የገለፀችው ነገር የለም፡፡ ሰላሙን ያደፈረሰችው እስራኤል ናት በፍልስጥኤም አሳ አጥማጆች ላይ ተኩስ ከፍታለች በማለት የኢስላሚክ ጂሀድ አባላት ቅሬታቸውን ገልፀዋል፡፡
 
< Prev   Next >