| ሳውዲ አረቢያ በቀን 9.7 ሚሊዮን... |
|
|
| Wednesday, 25 June 2008 | |
|
ሳውዲ አረቢያ በቀን 9.7 ሚሊዮን በርሜል ነዳጅ ለማምረት ወሰነች
በዳዊት ታዬ ሳውዲ አረቢያ በአለም አቀፍ ደረጃ እየጨመረ የመጣውን የነዳጅ ዋጋን ለማረጋጋት የነዳጅ ምርቷን በቀን ወደ 9.7 ሚሊዮን በርሜል ልታሳድግ መሆኗን አስታወቀች፡፡ ሳውዲ አረቢያ ጅዳ ውስጥ በተካሄደው ጉባኤ ላይ ከሐምሌ ወር ጀምሮ በቀን ተጨማሪ 200ሺህ በርሜል ለማቅረብ ቃል ገብታለች፡፡ ሳውዲ አረቢያ ከዚህ ውሳኔዋ ቀደም ብሎም ከግንቦት ወር ጀምሮ በቀን ተጨማሪ 500ሺህ በርሜል ነዳጅ ያመረተች ቢሆንም ገበያውን ሊያረጋጋ አለመቻሉ ይታወቃል፡፡ ቢቢሲ ባሰራጨው 165 መሠረት ሳውዲ ምርት በመጨመር በተወሰነ ደረጃ ገበያውን ለማረጋጋት እሞክራለሁ ብትልም ይህ ውሳኔዋ በኦፔክ አባል አገራት ዘንድ ድጋፍ ካላገኘ ብዙም ለውጥ አያመጣም የሚል ስጋት አለ፡፡ ሳውዲ ከዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰችው በተለይ ደሃ የሚባሉ አገራት በነዳጅ ግዥ የገጠማቸውን ችግር ለማቃለልና በተወሰነ ደረጃም ቢሆን የዋጋ ቅናሽ እንዲያገኙ ነው፡፡ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |