| ሥነ ምግባር ለጋዜጠኞች |
|
|
| Wednesday, 25 June 2008 | |
|
ሥነ ምግባር በሁሉም የሥራ ዘርፎች የሚያገለግል ጠቃሚ መመሪያ ነው፡፡ ከአድሎአዊነትና ከሙስና መጽዳትን፣ ለሕዝብና ለሙያ ታማኝ መሆንን፣ የሕዝብን ባህል ማክበርና አልኮልና ሱስ ከሚያሲዝ አደገኛ እፆች ራስን ነፃ ማድረግንና የሥራ መመሪያዎችን ማክበርን ያጠቃልላል፡፡ በተለይ በጋዜጠኝነት ዓለም ሥነ ምግባር የሥራና የኑሮ የዕለት ተዕለት መመሪያ ሊሆን የግድ ይላል፡፡
በሪፖርተር ጋዜጣ ሰኔ 15 ቀን 2000 ዓ.ም እትም እኔ የምለው ገጽ "ጋዜጠኛና ሥነ ምግባር" በሚል ርዕስ የቀረበው ጽሁፍ የጋዜጠኛው ሕይወት በመልካም ሥነ ምግባር ላይ የታነጸና የተወደደ መሆን እንዳለበት ጠቁ"ል፡፡ የግል ንጽህናን መጠበቅ የጋዜጠኝነት ሥነ ምግባር ከሚጠይቃቸው በርካታ ነጥቦች መካከል አንዱ ነው፡፡ ንጽህናውን ያልጠበቀና ራሱን የጣለ ጋዜጠኛ በሕብረተሰቡ ዘንድ ተቀባይነት የለውም፡፡ ሥራውንና የተጣለበትን ኃላፊነት በአግባቡ ይወጣዋል ለማለት አያስደፍርም፡፡ ከዚህ አኳያ ሥነ ምግባር ከራስ እንደሚጀመር መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡ ለራሱ መረጃ ያህል ብቻ እንዲያውቀው የተነገረውን መረጃ (ኦፍ ዘ ሪከርድ) እየዘገበ ለሕዝብ የሚያቀርብ ጋዜጠኛ የሥነ ምግባር ችግር ተጠናውቶታል ማለት ነው፡፡ በሥነ ምግባር የታነፀ ጋዜጠኛ ለሚያቀርበው ዘገባ ሁሉ ይጠነቀቃል፡፡ ቃለ መጠይቅ ከማድረጉ በፊትም ስለ ጉዳይ በቂ ዕውቀት ለመጨበጥና መረጃም ለማግኘት ይጥራል፡፡ ከግል ንጽህናው ጀምሮ ጥያቄዎቹን በሚገባ አሰናድቶ፣ ሙሉና ዝግጁ ሆኖ ይቀርባል፡፡ ሕዝብን በሕዝብ ላይ የሚያነሳሱ፣ የጎሳና የሃይማኖት ግጭቶቹን የሚቀሰቅሱ፣ በምስጢር መያዝ የሚገባቸውን የሀገሪቷን ደህንነትና የመከላከያ እንቅስቃሴን ከመዘገብ መቆጠብ እንደሚገባ የሥነ ምግባር ደንብ/መመሪያ (ኮድ ኦፍ ኤቲክስ) ያመለክታል፡፡ የሀገራችን ጋዜጠኞችም ይህን ደንብ ሊኖራቸው ይገባል፡፡ ለዚህም እውን መሆን የሙያ ማኅበራት እንቅስቃሴ ነው፡፡ (ቃለሕይወት አበበ፣ ከጎጃም በረንዳ) |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |