| በአየር ንብረት ለውጥ... |
|
|
| Sunday, 13 January 2008 | |
|
በአየር ንብረት ለውጥ ሴቶች የበለጠ ተጠቂ ናቸው በእስያ የዓለም ሙቀት መጨመር የሚያስከትለውን ተጽዕኖ በተመለከተ ጥናት ያከናወነ አካባቢና የልማት ባለሙያዎች ቡድን በአየር ንብረት ለውጥ የበለጠ ተጠቂ የሆኑት ሴቶች መሆናቸውን አመልክቷል፡፡
እንደ ጥናት ቡድኑ የዚህ ምክንያቶች ብዙ ሲሆኑ ሴቶች የኢኮኖሚ ጫና ያለባቸውና ሁሉንም ኃላፊነት የሚሸከሙ መሆናቸውና ወንዶች ጥለዋቸው የሚሄዱበት አጋጣሚም ስለሚኖር የአየር ንብረት ለውጥ የሚያመጣውን ፈተና ብቻቸውን ለመጋፈጥና ለመቋቋም አይችሉም፡፡ በአየር ንብረት ለውጥ ውጤቶች በድርቅና በጎርፍ፣ በደን መመናመን ምክንያት ሴቶች ማገዶ ፍለጋ ያሉ ተግባራት ለሴቶች አስቸጋሪ ይሆናሉ፡፡ በዚህ ረገድ የአየር ንብረት ለውጥ በሴቶች ላይ የሚያደርሰው ተጽዕኖ በተመለከተ የአገራት መንግስታትና ፖሊሲ አውጪዎች ትኩረት ሰጥተው ጥናቶች ሊያደርጉ እንደሚገባ ቡድኑ አስተያየት መስጠታቸውን ኢንዶ-ኤዥያ ዜና አገልግሎት ዘግቧል፡፡ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |