Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Thursday
Aug 28th
Home arrow Sections arrow ከ250 ሺህ ነጋዴዎች አባል የሆኑት...
ከ250 ሺህ ነጋዴዎች አባል የሆኑት... Print E-mail
Sunday, 29 June 2008
ከ250 ሺህ ነጋዴዎች አባል የሆኑት 6 በመቶ ብቻ ናቸው

በዳዊት ታዬ

በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በተለያዩ የንግድ ዘርፎች ለመሰማራት ፍቃድ ከወሰዱት ነጋዴዎች የከተማው ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት አባላት ሆነው የተመዘገቡት ስድስት በመቶው ብቻ መሆናቸው ተጠቆመ፡፡

የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት የአባላት ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ አቶ አበራ ታፈሰ እንደገለፁት፣ የንግድ ፍቃድ ከሚሰጡ መንግሥታዊ መሥሪያ ቤቶች የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው በአዲስ አበባ ውስጥ 250 ሺህ ፍቃድ የወሰዱ ነጋዴዎች ቢኖሩም የም/ቤቱ አባል ሆነው የተመዘገቡት 15 ሺህ የሚሆኑት ብቻ ናቸው፡፡

በከተማዋ ውስጥ አሉ ከሚባሉት ነጋዴዎች 15 ሺህ ብቻ አባል መሆናቸውና ይህም ከጠቅላላው የነጋዴ ቁጥር ጋር ሲነፃፀር አባላት የሆኑት 6 በመቶ ብቻ መሆናቸውን የሚያሳይ በመሆኑ ነጋዴው የንግድ ም/ቤት አባል ለመሆን ያልቻለበትን ምክንያት እንዲጠና አስገድዷል፡፡

የአባላት ቁጥር ለማሳደግ ም/ቤቱ አዳዲስ አሠራሮችን በመቀየስ ላይ ሲሆን የአባላት ቁጥር በማነሱ ዙሪያ በተደረገ ጥናት የተለያዩ ምክንያቶች መሰንዘራቸውን አቶ አበራ አስታውቀዋል፡፡

አባል ላለመሆን ከተጠቀሱ ምክንያቶች መካከል የአባልነት ክፍያ ከፍተኛ መሆን፣ የመንግሥትና የግሉ ዘርፍ የጋራ ምክክር መድረክ ጠንካራ ባለመሆኑና በመቋረጡ፣ የንግዱ ህብረተሰብ ችግሮች ለመንግሥት እየቀረቡ በተቻለ መጠን መፍትሔ ሊገኝባቸው ባለመቻላቸውና የመሳሰሉት ተጠቅሰዋል፡፡

የአዲስ አበባ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ከ60 ዓመታት በላይ እድሜ ያለው ሲሆን በምስረታው ወቅት የነበሩት የአባላት ቁጥር 300 ብቻ እንደነበሩም ተጠቁሟል፡፡
 
< Prev   Next >