Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
Jul 20th
Home arrow Sections arrow የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ድርጅት ተመሰረተ
የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ድርጅት ተመሰረተ Print E-mail
Wednesday, 16 January 2008
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲና የዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል በጋራ የኢትዮጵያ ጥራትና ሽልማት ድርጅት መመስረታቸውን ትላንት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ አስታወቁ፡፡

በመግለጫው ወቅት በአዲስ አበባ የኒቨርሲቲ የኢንዱስትሪ ትብብር ዳይሬክተር ዶክተር ኢንጂነር ዳንኤል ቅጣው አገር አቀፍ የጥራት ሽልማት ድርጅት ምስረታ የግልና የመንግሥት አምራችና አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶችን የጥራት አቅም እንደሚያሻሽል፣ እንደሚያሳድግና ብቃታቸውን ከፍ እንደሚያደርግ ገልፀዋል፡፡ በዚህም የሃገሪቱን ገቢና ወጪ ምርትና አገልግሎቶችን በማጠናከር በአለም አቀፍ ደረጃ ብቁ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የሚያስችል መሆኑን አብራርተዋል፡፡

የዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከልና አዲስ አበባ የኒቨርሲቲ ሀገር አቀፉን የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ድርጅትን ለመመስረት እና የሽልማት ሂደቱን ውጤታማ ለማድረግ ነሐሴ 24/1999 ዓ.ም ስምምነት ተፈራርመው ሲንቀሳቀሱ መቆየታቸው ተገል..ል፡፡

የሽልማቱ ድርጅት የግልና የመንግሥት አምራችና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት፣ በዘመናዊ የጥራት መመዘኛ ታግዘው ከሀገር አልፈው በዓለም ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የማድረግ፣ ተቋማት ጥንካሬና ድክመታቸውን እንዲሁም ሊገጥሟቸው የሚችሉ ችግሮችን በመለየት መፍትሄና ጠቃሚ አቅጣጫዎችን ማመላከት የሚችሉባቸውን ሁኔታዎች የማመቻቸትና በምርትና በአገልግሎት አሰጣጥ ለሌሎች አርአያ የሚሆኑ የግልና የመንግሥት ድርጅቶችን ለበለጠ ስራ እንዲተጉ ማድረግና ማበረታታት ዋነኞቹ የድርጅቱ አለማዎች እንደሆኑ ተብራርቷል፡፡

ዶ/ር ኢንጅነር ዳንኤል ቅጣው ድርጅቱ የሽልማት አሰጣጥ ስነ ሥርዓቱን በተመለከተ ለአምራቾች፣ በአገልግሎት ሰጪ ዘርፍ፣ ለትርፍ የማይንቀሳቀሱ የአገልግት ሰጪ ዘርፍና በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚመረጡ ድርጅቶችን በየዓመቱ አወዳድሮ ሽልማት እንደሚሰጥ ገልጸዋል፡፡

የዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል የማርኬቲንግ ስራ አስኪያጅ አቶ ማርቆስ ተክሉ በበኩላቸው የጥራት ሽልማት ድርጀት ለመመስረት ሀሳቡን ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል ማቅረቡን ገልፀዋል፡፡ አቶ ማርቆስ ድርጅቱ በተቃና መልኩ ስራውን እንዲሰራ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር መቀናጀት እንዳስፈለገ አብራርተዋል፡፡

የድርጅቱን ምስረታ አስመልክቶ ነገ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሰቲ ውስጥ አውደ ጥናት እንደሚካሄድ ተገል..ል፡፡ በአውደ ጥናቱ ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደ ጊዮርጊስን ጨምሮ ሚኒስትሮች፣ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት ተጋባዥ እንግዶች ይገኛሉ፡፡

ተሾመ ንቁ

 
< Prev   Next >