Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Wednesday
Aug 20th
Home arrow Sections arrow ከሥራ ተባረርን ያሉ ሠራተኞች...
ከሥራ ተባረርን ያሉ ሠራተኞች... Print E-mail
Wednesday, 02 July 2008
ከሥራ ተባረርን ያሉ ሠራተኞች ሠላማዊ ሰልፍ ሊያደርጉ ተስማሙ

በዳዊት ታዬ

የካንትሪ ዴቨሎፕመንት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ውስጥ ተቀጥረው ሲሠሩ የነበሩ ከ269 ሠራተኞች ከህግ ውጪ ከሥራ ተባረናል በማለት ተቃውሟቸውን ገለፁ፡፡ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ወሰኑ፡፡

ባሳለፍነው እሁድ የድርጅቱ የሠራተኞች ማህበር ባደረገው ጠቅላላ ጉባኤ ላይ እንደተገለፀው የድርጅቱ ሠራተኞች ከህግ ውጪ እያባረረና በተለይ የማህበሩ አባላትን ሙሉ ለሙሉ ማባረሩን ገልፀዋል፡፡

የሠራተኛ ማህበር መሪዎቹ እንደገለፁት ድርጅቱ ከሠራተኛው ጋር የህብረት ስምምነት ለማድረግ በመጠየቁ ምክንያት ይህንን ጥያቄ የሚያነሱትን የማህበር መሪዎችና የማህበሩ አባላት የሆኑትን ሠራተኞች ለማጥቃት የወሰደው እርምጃ እንደሆነም ይገልፃሉ፡፡ ሆኖም የተባረሩበት ምክንያት በሲሚንቶ እጥረት ሳቢያ በገጠመ ችግር እንደሆነ መሰናበታቸውን የሚያመለክተው ማስታወቂያ ያስረዳል፡፡

በሌላ በኩልም ይህ ከህግ ውጭ ያለውን አሠራር ህጋዊ መስመር እንዲይዝና ድራጅቱ ሠራተኞችን እንዲመልስ የቀረበለትን ጥያቄ አዎንታዊ በሆነ መልኩ ሊመልስ ባለመቻሉ ሰላማዊ ሰልፍ በመውጣት ጉዳዩን ለመንግሥት ለማሳወቅ ወስነዋል፡፡

ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ እንዲችሉም ከትናንት በስቲያ ፍቃዱን ለሚሰጠው አካል ደብዳቤ ለማስገባት በዝግጅት ላይ እንደነበሩም ለማወቅ ተችሏል፡፡

በሌላም በኩል የአገር አቀፍ የኮንስትራክሽንና የመሳሰሉ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ዘገየ ለሪፖርተር እንደገለፁት የአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ አንቀፅ 19 ላይ እንዲህ ዓይነት የማቴሪያል እጥረት ሲኖር ለክልሉ ማህበራዊ ጉዳይ ማሳወቅ እንደሚገባው ገልፀው ማህበራዊ ጉዳይ ሄዶ በትክክል ያለውን ችግር ካጣራ በኋላ የእገዳውን ቁጥር ይገልፅለትና በዚሁ መሠረት ችግር እገዳ እንደሚያደርግ ያለበት፡፡ ነገር ግን ሥራውን እየሠራ በዚህ ሰበብ ሠራተኞችን ማሰናበት አይችልም ብለዋል፡፡

እነዚህ የማህበር መሪዎች የህብረት ሥራ ስምምነት ድርድር ጥያቄ አቅርበው ችግር እንደተፈጠረባቸው ለኦሮሚያ ፕሬዚዳንት ቢሮ፣ ለኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ማሳወቃቸውን አቶ ዘገየ ገልፀዋል፡፡

የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ጉዳዩን እያጣራ ቢሆንም ውጤቱ እስካሁን አልታወቀም፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ ድርጅቱ አዳዲስ ሠራተኞችን ቀጥሮ እያሠራ ነው፡፡ በግንባርም አነጋግረናቸው ነበር፡፡ የህብረት ስምምነት ድርድር የሚደረገው በ2001 ዓ.ም ሲሆን ከዚያ ወዲህ አልችልም የሚል መልስ ሰጥቶናል፡፡

በአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ ላይ በአስር ቀን ውስጥ አሠሪው መቅረብ አለበት የሚል ነው፡፡ ይህንን ካላደረገ በአዋጁ 10 ሺህ ብር የሚያስቀጣው ነው፡፡

አሁን ያለው ችግር አስመልክቶ ባለፈው እሁድ ባደረገው ስብሰባ ላይ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ወስኗል፡፡

ይህንንም አቋሙን ለኢሠማኮና ለፌዴሬሽኑ አሳውቋል፡፡ ከሰኞ ጀምሮ ለሠላማዊ ሰልፉ የፍቃድ አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት ይከናወናል ብለዋል፡፡
 
< Prev   Next >