| ምክር ቤቱ ጥያቄውን ለአዲሱ አስተዳደር አቀረበ |
|
|
| Wednesday, 02 July 2008 | |
|
በዳዊት ታዬ
የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ለማስገንባት ያቀደውን አዲስ አፍሪካ ዓለም አቀፍ የኤግዚቢሽን ማዕከል ከአዲስ አበባ አስተዳደር ጋር ለመገንባት ለአዲሱ የከተማው አስተዳደር ጥያቄ አቀረበ፡፡ የንግድ ምክር ቤቱ ኃላፊዎች ለሪፖርተር ጋዜጣ እንደገለፁት ከ240 ሚሊዮን ብር በላይ ይፈጃል የተባለው የኤግዚቢሽን ማዕከልን በንግድ ቤቱ አቅም ብቻ የሚሠራ ባለመሆኑ አዲሱ አስተዳደር ስልጣን ከመረከቡ በፊት ቅድመ ስምምነት የተደረገ በመሆኑ በዚሁ ስምምነት መሠረት አዲሱ አስተዳደርም ቀደም ብሎ የተጀመረውን እንቅስቃሴ ከዳር እንዲያደርስ ተጠይቋል፡፡ ማዕከሉን በጋራ ለመገንባት ሃሳቡን ያመነጨው የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ሲሆን ሃሳቡን በመቀበል የቀድሞ የከተማው ከንቲባና የምክር ቤቱ ፕሬዚዳንተ የመጀመሪያ ደረጃ ቅድመ ስምምነት ካደረጉ በኋላ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከሁለቱም ወገን የተውጣጣ ኮሚቴ ተቋቁሞ የጋራ ግንባታው በምን መልኩ ይሁን በሚለው ጉዳይ ላይ እንዲመክሩና የደረሱበትን ድምዳሜ እንዲያሳውቁ ለማድረግ ቢሆንም ይህ ኮሚቴ ሳይዋቀር አዲሱ አስተዳደር ስልጣን መረከቡን ለማወቅ ተችሏል፡፡ በአሁኑ ወቅትም አዲሱ አስተዳደር የተጀመረውን ሥራ ለማስጨረስ ውይይትና ቀጣይ ሥራዎች እንዲሠሩ በላከው ደብዳቤ አስታውሷል፡፡ ለአስተዳደሩ የተላከው ደብዳቤ ከሦስት ሳምንት በላይ ያስቆጠረ ቢሆንም እስካሁን መልስ ያልተሰጠው ሲሆን በጉዳዩ ላይ ያነጋገርናቸው አንድ የምክር ቤቱ ኃላፊ ግን አስተዳደሩ በጉዳዩ ላይ መልስ ለመስጠት የዘገየው አዲስ በመሆኑና በሁለቱ ወገኖች መካከል ተደርጐ የነበረው ስምምነት በድጋሚ መመልከት ስለሚኖርበት ነው ብለዋል፡፡ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |