| የመጀመሪያዎቹ |
|
|
| Wednesday, 02 July 2008 | |
|
ዳግማዊ አጤ ምኒልክ በ1896 ዓ.ም የመንገድ መዳመጫ ሩሎ እና ሰረገላ አስመጥተው የመንገድ ሥራ አስጀመሩ፡፡ የመጀመሪያውም መንገድ 56 ኪ.ሜ ርዝመት ያለው ከአዲስ አበባ እስከ አዲስ ዓለም ድረስ የተሰራው ነው፡፡
በ17ኛው ክፍለ ዘመን በአፄ ሱስንዮስ ዘመነ መንግሥት በዓባይ ወንዝ ላይ በእንቁላልና በእንገር የተሰራው የአልታ ድልድይ በአገራችን የመጀመሪያው ድልድይ ነው፡፡ ድልድዩም ከባህር ዳር ከተማ 3ዐ ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ ከምኒልክ ዘመነ መንግሥት በፊት ወፍጮ ቢመጣም ግልጋሎት ላይ የዋለው የመጀመሪያው ወፍጮ መጥቶ የተተከለው በ1893 ዓ.ም ነው፡፡ ብስክሌት አዲስ አበባ የገባው በ1893 ዓ.ም ነው፡፡ ምኒልክ የብስክሌቷን አነዳድ ከተመለከቱ በኋላ ተደንቀው ያልገባኝ ነገር እግር ከመወዛወዝ ካላረፈ ድካሙ ምን ቀረለት አሉ ይባላል፡፡ (ቴሌ ነጋሪት፣ መስከረም፣2000) ሳንተያይ አልቻልሁትም ጨዋታሽን አልቻልሺውም ፍቅሬን ስሸሽሽ ተንበርክከሽ ስከተልሽ እየሸሸሽ፡፡ መገናኛችን ፍቅር መሆኑ ቀርቶ በእኛ መሃል ለርህራሄ ቦታ ጠፍቶ ሳንባክን የዶግ አመድ ሁነን ሳንኰነን እንቀትር ብሌን ወድቀን እንለያይ በዳሰሳ ሳንተያይ ይብረድልኝ መለስለስሽ ይድረቅልሽ ፍቅሬ፣ የነሃሴ ጐርፉ ደረቅ ሰማይ በመብረቅ መጦፉ፡፡ (ሰሎሞን ዴሬሳ፣ ልጅነት፣ 1963) ትርጉም የሌላቸው ጨዋታዎች በልጆች ጨዋታ ጊዜ ትርጉም ሳይኖራቸው የጨዋታውን ክዋኔ ለማድመቅ ወይም ለድምጻቸው፣ ለምታቸውና ለዜማቸው ሲባል የሚባሉ ቃላትንና ሀረጋትን የያዙ የጨዋታ ዓይነቶች እናገኛለን፡፡ ለምሳሌ በከተሞች በአብዛኛው ከሚሰሙት ጨዋታዎችና ትርጉም ከሌላቸው መካከል የሚከተለው በምሳሌነት ሊጠቀስ ይችላል፡፡ ዲምቢሽ ለዲምቢሽ ዲምቢሽ ኖራ ኖራ መስኮራ መስኮር ኮርኪ ኮርኪ ሰላሌ ሰላሌ እምቦ ሌምቦ ክፍሌምቦ ክፍሌ ላንካ ላንካ የሸማኔ ዋርካ ትላንትና ማታ ጭቃ ስታቦካ በትልቁ ማንካ በትንሹ ማንካ፡፡ (ዘሪሁን አስፋው፣ የስነ ጽሑፍ መሠረታውያን፣ 1992) የስኬት ወይም የፀሐይ መሥመር ፀሐይ ለምድር በምትሰጠው ብርሃንና ሙቀት መሬት ለምነትን፣ ሀብትንና ደስታን እንደምታጎናጽፈን ሁሉ፣ ይህም መሥመር ለእጆቻችን የዚያኑ ያህል ጠቃሚ ነው፡፡ በተለይም ለዕጣ መሥመር በጣም የሚጠቅም ነው፡፡ ከማንኛውም በእጅ ላይ ካሉ መስመሮች ሁሉ ምሥጢራዊ ነው፡፡ በእጅ ላይ ከታየበት ቀን ጀምሮ በተለይም ከዕድል መሥመር ከተነሳ የዚያ ሰው መልካም አጋጣሚ ወይም ጥሩ ዕድል የሚያጠራጥር አይደለም፡፡ የስኬቱ ዓይነት የሚገመተው መሥመሩ በታየበት የእጅ ዓይነት ነው፡፡ የተዋጣለት የመጽሐፍ ቅዱስ ሰባኪ ይህ መሥመር ሊኖረው እንደሚችል ሁሉ፣ የተዋጣለት ወንጀለኛም ሊኖረው ይችላል፡፡ መሥመሩ ልክ እንደ ፀሐይ ለግለሰቡ ምኞትና ፍላጎት ሙሉ ተስፋ ይሰጣል፡፡ ዝናንና መታወቅን ለከያንያን ያመጣል፡፡ መሥመሩ ለግለሰቡ የገናናነት የመነሻ ነጥብ ሊሆን ይችላል፡፡ ለሠዓሊ የመጀመሪያ የታወቀ ሥዕል፤ ለደራሲም የመጀመሪያ ተቀባይነት የሚያገኝ ድርሰቱ ይሆናል፡፡ ይሁንና የሰው እጣ ለአንዴና ለሁሌም በሕይወት ጐዳናው የከባድ ክንዋኔዎች የድንጋይ ምልክት ነው፡፡ (ኃይለሚካኤል ለቴራ፣ መዳፍ እንደ መጽሐፍ"ትርጉም"፣ 1984) የውሃ ወራጅ ዳኛ ሁለት ሰዎች በጐዳና ላይ ሲጣሉ ወይም አንድ ገንዘብ አበዳሪ ገንዘቡን ተበድሮ አልመልስ ያለውን ባለእዳ በድንገት ሲያገኝ በአካባቢው ካሉት ሰዎች መካከል ወደ አንዱ ቀረብ በማለትና የጊዜውን የአገር መሪ ስም እየጠራ በመማጠን "በ . . . አምላክ ዳኘን" ይለዋል፡፡ ይህን መሳይ ጥያቄ የቀረበለትም ሰው ለጊዜው የግሉን ጉዳይ ወደ ጐን ተወት በማድረግ የከሳሽና የተከሳሽን ጉዳይ ራሱ ለመሸምገል ወይም ሁለቱን ወደ ዳኛ ለማድረስ አስፈላጊውን እርምጃ ይወስዳል፡፡ ተከሳሽ የዚህን የልማዳዊ ህግ አስገዳጅነትን ቸል በማለት በእምቢተኝነት እዳኛ ዘንድ አልቀርብም ብሎ ቢያንገራግርና አልቆም ብሎም መንገድ ቢጀምር ዳኝነት የተጠየቀው ሰው፣ ወዴት ልትሄድ ነው በል ቁም እንጂ" በሕግ ቁም ሲሉት እንኳን ሰው ውሃ ይቆማል፡፡ እያለ ያስጠነቅቀዋል፡፡ በዚህም ጊዜ ተከሳሽ ከሕግ በላይ አለመሆኑን በመገንዘብ ይቆማል፡፡ ከዚህ በኋላ ሰውየው ከሚወስዳቸው እርምጃዎች አንዱ ከሳሽና ተከሳሽ የለበሷቸውን ነጠላ ጫፎች በአንድነት በማቋጠር ሁለቱን ባለጉዳዮች ካቆራኘ በኋላ በአቅራቢያው ወደሚገኘው ዳኛ ማድረስ ነው፡፡ ሁኔታውን ለዚሁ ዳኛ ካብራራና ማህበራዊ ግዴታውን ከተወጣ በኋላ ወደ ግል ጉዳዩ ይመለሳል፡፡ ይህን መሰሉ ዳኛም ፣የውሃ ወራጅ ዳኛ፣ እየተባለ ይታወቅ ነበር፡፡ (ሺበሺ ለማ፣ ተጠየቅ፣ 1985) ገራገር በሁለት ቀናት 10"000 የሞቱ የወባ ትንኝ ገዢዎች አመለከቱ ቻይናዊው የሞቱ የወባ ትንኞችን እንደሚሸጥ በድረ ገፅ ካስታወቀ በኋላ ወደ 10"000 የሚጠጉ ገዢዎች እንዳመለከቱ ገለፀ፡፡ ሰውዬው ሻንጋይ ውስጥ በድረ ገፅ ለሚሸጣቸው ጌጣጌጦች ማስታወቂያ እንዲሆንለትና ጐብኝዎች እንዲመጡ ሃሳቡን ማፍለቁን ተናግሯል፡፡ መደብሩን እንዴት ማስተዋወቅ እንዳለብኝ አስቤ ይህን ሃሳብ በአዕምሮዬ ሊመጣ ችሏል ማለቱን የኪንሎንግ ዜና ያመለክታል፡፡ ሂን ናን የተባለው ይህ ቻይናዊ በስድስት የን የሚሸጣቸውን የሞቱ ትንኞች በትክክል በሰው እጅ የተገደሉ፣ ለሣይንሳዊ ምርምር፣ ለጌጣጌጥና ለስብስብ የሚሆኑ እያለ አስተዋውቋል፡፡ የአውስትራሊያው ወይን ጠጅ ፋብሪካና የሻንጋይ ድርጅቶችም ከእነርሱ ጋር እንዲሰራ የጋበዙት ሲሆን እርሱ ግን የራሱን ሥራ መሥራትና መታወቅ እንደሚፈልግ ገል"ል፡፡ እሥረኛው በወረቀት አበባ ይቅርታ ጠየቀ ከአሜሪካ እስር ቤት ያመለጠው እስረኛ ከመፀዳጃ ቤት ወረቀት አርቴፊሻል አበባ በመሥራት የይቅርታ መልዕክት አስቀመጠ፡፡ እስረኛው ከተያዘ በኋላ ለምን እንዲህ እንዳደረገ በፖሊስ ሲጠየቅ ይህ የመፀፀቴ ምልክት ነው ብሏል፡፡ ካማቾ ሚንዲዛ የተባለው እስረኛ በሁለተኛ ቀን ከተያዘ በኋላ በእስር ቤቱ የምግብ ማብሰል ሥራ እንዲሠራ ተደርጓል፡፡ ከመፀዳጃ ወረቀት የሠራውን አበባ ለእስር ቤቱ አስተዳዳሪ በስጦታ አቅርቤያለሁ ያለው ካማቾ ሚንዲዛ የተፈረደበት ከሜክሲኮ አደንዛዥ ዕፅ በማዘዋወር ወንጀል ነው፡፡ ተጋጭቶ ፈተና ያልወደቀው ተማሪ የ20 ዓመቱ መኪና ተለማማጅ የመጋጨት አደጋ ቢደርስበትም እንኳ ፈተናውን አልወደቀም ሲል ደይሊ ሚረር ዘገበ፡፡ ግጭቱ ከደረሰበት በኋላ ፈተናውን ሳያቋርጥ እንዲቀጥል አለማማጁ ባዘዙት መሠረት ሲጨርስ የመንጃ ፍቃዱ ተሰጥቶታል፡፡ ተማሪው "የመንጃ ፍቃዱን ሲሰጡኝ ለማመን ተቸግሬያለሁ" ብሏል፡፡ ከግጭቱ በኋላ ያለምንም ስህተት ቢቀጥልም እግሮቹ ግን እየተንቀጠቀጡ እንደነበር አልደበቀም፡፡ የስዕል ኤግዚቢሽኑ በሩጫ ታጀበ የማርቲን ክሪድ 850ኛ የፈጠራ ሥራ ብልጭ ድርግም በሚለው ብርሃን ፍጥነት አትሌቶች በጋለሪው ውስጥ በአጭር ርቀት ሲሮጡ መሆኑን ዴይሊ ቴሌግራፍ ዘገበ፡፡ አምሳ የስፖርት ክለቦች የተመዘገቡ ሲሆን በሰዓት 10 ዩሮ እንዲከፈላቸው መስማማታቸውና አትሌቶቹ በሚፈልጉት መጠን መሮጥ እንደሚችሉም ተገልጿል፡፡ የ39 ዓመቱ ሚስተር ክሪድ "ሩጫው የማስመሰል ሳይሆን የእውነት የሚሮጥበት ነው፡፡ ይህም ልክ እንደ ስዕሎቹ የሚታይ ነገር ነው፡፡" ብሏል፡፡ ሌላው አርቲስት ዌክፊልድ በበኩሉ "እኔ ሰዎች ሲሮጡ ማየት ደስ ይለኛል፡፡ ማናችንም ልናደርገው የምንችለውም ነው፡፡ ለዚህም ይመስለኛል ማራኪ የሚሆነው" ብሏል፡፡ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |