| የተባበሩት መንግስታት ለአፍሪካ... |
|
|
| Wednesday, 02 July 2008 | |
|
የተባበሩት መንግስታት ለአፍሪካ መሪዎች ጥሪ አቀረበ
ምርጫውን ተከትሎ በዚምባብዌ የተፈጠረውን ቀውስ ለማርገብ የተባበሩት መንግስታት በግብጽ ባደረጉት ስብሰባ የአፍሪካ መሪዎች መፍትሄ እንዲፈልጉ ጥሪ አቀረበ፡፡ የተባበሩት መንግስታት ምክትል ዋና ፀሐፊ አሻ ሮዝ ሚግሮ ጊዜው የአፍሪካ መሪዎች ሀቀኝነት የሚታይበት ነው ብለዋል፡፡ በስብሰባው ላይ ፕሬዚዳንት ሮበርት ሙጋቤ የተገኙ ሲሆን ከተቃዋሚ ፓርቲው ጋር ተነጋግረው የሽግግር መንግስት እንዲመሰርቱ ደቡብ አፍሪካም በበኩሏ ጥሪ ማቅረቧን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡ ተቃዋሚው የዲሞክራሲያዊ ለውጥ ንቅናቄ መሪ ሞርጋን ቻንጋራይ ራሳቸውን ከምርጫ ካገለሉ በኋላ ብቸኛ ዕጩ መሆናቸውን ሚስተር ሙጋቤ እንደ ድል ቆጥረውታል፡፡ "የእያንዳንዱ መሪ ሀቀኝነት የሚታይበት ወቅት በመሆኑ የስምምነት መፍትሄ ላይ እንዲደርስ ጥሪያችንን እናቀርባለን" በማለት ለ53 የአፍሪካ አገር መሪዎች ሚስ ሚግሮ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡ ለደቡቡ አፍሪካ ክፍል መረጋጋት ትልቅ ፈተና ነው ያሉት ሚስ ሚግሮ አያይዘውም ምርጫው እንዲካሄድ በመፍቀዱም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተጸድቷል ብለዋል፡፡ በኢራን የኒውክለር ኃይል ፍተሻ ፍንጭ አልተገኘም ኢራን ሁለት የተጠረጠሩ የኒውክለር ሥፍራዎቿን የመረጃ መዛግብትና ቁሳቁሶችን ለመርማሪዎች ልትሰጥ መሆኑን በተባበሩት መንግስታት የአቶሚክ ኃይል ዋና ሥራ አስኪያጅ አስታወቁ፡፡ የኒውክለር ፍተሻው ኢራንን ከጥርጣሬ ነፃ የሚያወጣ መሆኑን ሞሐመድ ኤልባዲ መናገራቸውንም የተባበሩት መንግስታት የዜና ወኪል ገልጿል፡፡ ኢራን የኒውክለር መሣሪያዎቿን ለነዳጅ ማምረቻ ግብአትነት ታውላለች የሚል ፍራቻ አሜሪካ እንዳላትና ኢራን ለኒውክለር ግንባታ የምትጠቀምበትን ዩራኒየም እንዳታመርት የተጣለባትን ማዕቀብ አለመቀበሏም በዘገባው ተጠቅሷል፡፡ ኢራን የኒውክለር ፕሮግራሟን አስመልክቶ ዩራኒየም ማምረት መከልከሏን እንደ ቅድመ ሁኔታ ማስቀመጧ በተባበሩት መንግስታት ተቀባይነት አላገኘም፡፡ ኢራቅ የነዳጅ ምርቷን ለመጨመር ዕርዳታ ትሻለች የቀድሞው የኢራቅ የነዳጅ ሚኒስትር ዶክተር ሞሐመድ ባህር አል ኡሎም ኢራቅ የምስራቅ ነዳጅ አምራች ድርጅቶችን ዕርዳታ እንደሚያስፈልጋት መግለፃቸውን ቢቢሲ ዘገበ፡፡ የአገሪቱን ገቢ ለማሳደግ የነዳጅ ኢንዱስትሪዎቿን ለውጭ ባለሃብቶች ክፍት ማድረጓንም ዘገባው ያመለክታል፡፡ የነዳጅን ምርት በግማሽ ሚሊዮን በርሜል ለማሳደግ የአሜሪካና የአውሮፓ ድርጅቶች ጥያቄ ማቅረባቸውም ተጠቅሷል፡፡ ኢራቅ በዓለም ሦስተኛዋ ትልቅ የነዳጅ አምራች አገር ስትሆን ምርቱን ለማሳደግና ዘመናዊ ለማድረግ ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ ያስፈልጋታል፡፡ ይሁን እንጂ በኢራቅ ምክር ቤት ኮንትራቱን ለመፈጸምም ይሁን በጋራ ለመስራት የሚያስችል ስምምነት ላይ አልተደረሰም፡፡ የተባበሩት መንግስታት ታይዋንን በአባልነት አልመዘግብም አለ ታይዋንን የዓለማት አካል አድርጌ አልቀበልም ማለቷን የቢቢሲ ዘገባ አመለከተ፡፡ በኒውዮርክ ለተሰበሰበው ዋና ዋና የተባበሩት መንግስታት ኮሚቴ ከታይዋን ወዳጅ አገሮች የቀረበላትን ዕቅድ አልቀበልም ብሏል፡፡ ቻይና አንዷ ተቃዋሚ ስትሆን ታላቋ ቻይናና ታይዋን በ1949 ባደረጉት ጦርነት መለያየታቸው ይታወሳል፡፡ ለባንኪሙን የተባበሩት መንግስታት ለምን ታይዋንን እንደ አባል አይቀበላትም የሚል ጥያቄ የቀረበላቸው ሲሆን "ይህ ፈጽሞ ሊሆን አይችልም፡፡ ምክንያቱም ታይዋን እስከ 1971 ድረስ የቻይና ሪፐብሊክ በሚል መጠሪያ ስር ተጠቃላ በመቆየቷ ነው" ብለዋል፡፡ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |