| ከ3ሺ 400 በላይ የቀበሌ ሥራ አስኪያጆች ተመደቡ |
|
|
| Wednesday, 02 July 2008 | |
|
በደቡብ ክልል በቀበሌ ደረጃ መልካም አስተዳደርን በማስፈን ሕዝቡ ቀልጣፋና ፈጣን የመንግስት አገልግሎት እንዲያገኝ ለማስቻል ከ3.ሺ 400 በላይ የቀበሌ ሥራ አስኪያጆች መመደባቸውን የክልሉ አቅም ግንባታ ቢሮ አስታወቀ፡፡
በክልሉ በሚገኙ 3ሺ 447 ቀበሌዎች፣ የቀበሌ ሥራ አስኪያጆች ቅጥር መፈጸሙን፣ ሥራ አስኪያጆቹ ከሠርተፍኬት በላይ የትምህርት ደረጃ ያላቸው መሆናቸውን፣ ሥራ ከመጀመራቸው በፊት በዋና ዋና የገጠርና የከተማ ልማት ፖሊሲና ስትራቴጂ እንዲሁም በአቅም ግንባታ ፕሮግራሞች፣ ተግባርና ኃላፊነታቸውን አስመልክቶ ስልጠና እየተጣቸው እንደሚገኝ አብራርቷል፡፡ (ዋኢማ) ኢትዮጵያውያኑ “ብሔራዊ ይሁንታ ድምጽ” የሚል ፕሮግራም ማሰራጨት ጀመሩ በእንግሊዝ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ለንደን ከተማ በሚገኘው የአፍሪካ ድምጽ ሬዲዮ አማካኝነት የብሔራዊ ይሁንታ ድምጽ የሚል ፕሮግራም ማሰራጨት ጀመሩ፡፡ ኢትዮጵያውያኑ በእንግሊዝ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የኮሙኒቲ ጉዳዮችና ኮንስቲትወንሲ ግንባታ ክፍል ጋር በመተባበር ኤፍ.ኤም 94 ነጥብ 3 በሚል በሚታወቀው የአፍሪካ ድምጽ ሬዲዮ አማካኝነት የተለያዩ ፕሮግራሞችን በሳምንት ሁለት ቀናት ዘወትር ሐሙስና እሁድ ለአንድ ሰዓት እየተሰራጨ ነው፡ ፕሮግራሞቹ ሰላም በውይይት ለማስፈን የሚደረገውን ጥረት ማበረታታት፣ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ተወላጆች በፀረ ድህነት ትግል ላይ እንዲሳተፉ መቀስቀስ ስለ ኤች.አይ.ቪ/ኤድስና ሌላ ተላላፊ በሽታዎች መከላከል እንዲቻል ትምህርት ማስፋፋትና በሴቶች መብት ማስጠበቅ ላይ ያተኮሩ መሆናቸውንና፣ ፕሮግራሞቹን በብብብ. ethiopian consensusradio.com መከታተል ይቻላል ብለዋል፡፡ (ኢዜአ) በሆቴል ውስጥ ፈንጅ ያፈነዳው ግለሰብ በዕድሜ ልክ እስራት ተቀጣ ነገሌ ከተማ ውስጥ በአንድ ሆቴል ላይ ፈንጂ በማፈንዳት በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት ያደረሰው ግለሰብ በእድሜ ልክ እስራት እንዲቀጣ የወሰነበት መሆኑን የጉጂ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አስታወቀ፡፡ ፍርድ ቤቱ በግለሰቡ ላይ ቅጣቱን ያስተላለፈው ግንቦት 19 ቀን 2000 ዓ.ም ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ላይ ፈንጂውን በማፈንዳት በሰዎች ላይ ጉዳት በማድረሱና ከ275ሺ ብር በላይ የሚገመት ንብረት እንዲወድም በማድረጉ መሆኑን ገል"ል፡፡ (አዲስ ዘመን ሰኔ 23 ቀን 2000 ዓ.ም) ኢትዮጵያዊው የፈጠራ ድርጅት ዓለም አቀፍ ተሸላሚ ሆነ ኢትዮጵያ ውስጥ በኢታኖል የሚሰራ ምድጃን ሰርቶ በአገሪቱ በሚገኙ የስደተኞች መጠለያ ውስጥ ጥቅም ላይ እንዲውል በማድረግ የተዋጣለት ተግባር ያከናወነውና ጋያ ኦስሲየሽን በመባል የሚጠራው ያልሆነ ድርጅት ዓለም አቀፍ ሽልማት አገኘ፡፡ እንግሊዝ አገር ለንደን ላይ ሽልማቱን የወሰደው ኢትዮጵያዊወ ድርጅት፣ ከተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነር (ዩ ኤን ኤች ሲአር) አጋር የሆነው ማህበሩ ያከናወነው ተግባር የአካባቢ ጥበቃን ለማጠናከር የሚካሄደውን እንቅስቃሴ በከፍተኛ ደረጃ ያግዛል ተብሏል፡፡ (ኢዜአ) |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |