| አምስት የመንግስት ልማት ድርጅቶች... |
|
|
| Sunday, 13 July 2008 | |
|
አምስት የመንግስት ልማት ድርጅቶች በ386.6 ሚሊዮን ብር ተሸጡ
በፍሬው አበበ የፕራይቬታይዜሽን የመንግስት ልማት ድርጅት ኤጀንሲ ቦርድ የመንግስት ልማት ድርጅቶች በ386.6 ሚሊዮን ብር በላይ እንዲሸጡ ወሰነ፡፡ በአቶ ኃ/ማርያም ደሳለኝ የሚመራው ቦርድ ባለፈው ረቡዕ ማምሻውን ባካሄደው ስብሰባ በጨረታ ቁጥር 004/2007-2008 የ16 ድርጅቶች የሽያጭ ጨረታ መካከል ዋጋ የቀረበባቸውን የዘጠኝ ድርጅቶችን ሽያጭ ተመልክቶ አምስቱ ተገቢውን መስፈርት ያሟሉ ሆነው በመገኘታቸው እንዲሸጡ ሲወስን አራት ድርጅቶች ተገቢውን ዋጋ ተጫራቾቹ ባለመስጠታቸው ውጤታቸው እንዲሰረዝ ወስኗል፡፡ አቶ ወንድአፍራሽ አሰፋ የኤጀንሲው የማስታወቂያና ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ በተለይ ለሪፖርተር ጋዜጣ እንደተናገሩት ቦርዱ እንዲሸጡ ውሳኔ ያሳለፈባቸው ድርጅቶች የኢትዮጵያ ብረታ ብረት ማቅለጫ ፋብሪካ፣ የአቃቂ ብረታ ብረት ፋብሪካ፣ የኢትዮጵያ ቅመማ ቅመም ፋብሪካ፣ የኤካፍኮ አክስዮን ማኅበር፣ አልኪድሬዚን አክስዮን ማኅበር (ለቀለም ፋብሪካዎች ግብዐት አምራች ፋብሪካ) ናቸው፡፡ በተጨማሪም ዋጋ ቀርቦላቸው ነገር ግን የቀረበው ተገቢ ዋጋ አይደለም በሚል የጨረታው ውጤት እንዲሰረዝ የተወሰነባቸው ድርጅቶች የኢትዮጵያ ኮምፖልሳቶ ፋብሪካ፣ ጮራ ጋዝና ኬሚካል ፋብሪካ፣ የኢትዮጵያ ፕላስቲክ ፋብሪካ አክስዮን ማህበር፣ አርቲስቲክስ ማተሚያ ቤት መሆናቸውን ከአቶ ወንድአፍራሽ ገለፃ ለመረዳት ተችሏል፡፡ ከተሸጡት ድርጅቶች መካከል የኢትዮጵያ ብረታ ብረት እና አቃቂ ብረታ ብረት ፋብሪካዎችን የገዛው የሕንድ ኩባንያ የሆነው ዩኒቨርሳል ሜታል አንድ ሚኒራልስ ኃ/የተ/ግ/ኩ ሲሆን ኩባንያ ሁለቱንም ፋብሪካዎች በብር 295 ሚሊዮን 480 ሺህ ብር ለመግዛት ዋጋ አሸንፏል፡፡ አቶ ወንድአፍራሽ አያይዘውም በቦርዱ ውሳኔ መሰረት ኤጀንሲው በቅርቡ ከአሸናፊ ድርጅቶች ጋር ተገቢውን ውል ተፈራርሞ ፋብሪካዎቹን ያስረክባል፡፡ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |