| ምላሽ መገኘቱ ደህና |
|
|
| Sunday, 13 July 2008 | |
|
ባለፈው ሰሞን መነጋገሪያ ርዕስ ጉዳይ ሆኖ የሰነበተው በመንገድ ሥራ ሳቢያ የለገሀር ባቡር ጣቢያ ጥንታዊ ሕንጻ ይፈርሳል ወይስ አይፈርስም የሚለው ነበር፡፡ የአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን ሥራ አስኪያጅ እንደማይፈርስ አስረግጠው ተናግረዋል፡፡ አንዳንድ የመገናኛ ብዙሃንም ትክክል ያልሆነ መረጃ ማሰራጨታቸውንም ገልፀዋል፡፡
ከታሪካዊ ቅርሶች ጥበቃ አንጻር አሳሳቢ ጉዳይ ነበር፡፡ በቅርስ ባለአደራ ማኅበር በተጠራው ኮንፈረንስ ላይ ርዕሰ ጉዳይ ተነስቶ ምሁራኑና ተሰብሳቢዎቹ ትኩረት እንዲሰጥበት አሳስበዋል፡፡ የሪፖርተር ጋዜጣም በኮንፈረንሱ ላይ የነበሩት የባለሥልጣኑ ተወካይ እንደማይፈርስ መናገራቸውን ጠቅሶ አቅርቦታል፡፡ ጋዜጣው ሁለቱንም አስተሳሰቦች አንጸባርቆ ሳለ ትችት መሰንዘሩ አግባብ እንዳልሆነ ይሰማኛል፡፡ ዋና ሥራ አስኪያጁ ኢንጅነር ፍቃዱ ኃይሌ “አንዳንድ የግል ጋዜጦች፣ የቅርስ ባለ አደራ ማኅበርም ሆነ ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት መንግሥት ለቅርስ ጥበቃ የሰጠውን ትኩረት ከተገነዘቡ ሊያሰጋቸው የሚገባ ጉዳይ የለም” ብለዋል፡፡ ግን እውነታው እንደሚያሳየን በዚያ ኮንፈረንስም እንደተንጸባረቀው አይፈርሱም የተባሉት በምስካየ ኅዙናን መድኃኒ ዓለም ቤተክርስቲያን (ስድስት ኪሎ) አጠገብ የነበረው የሻለቃ በልሁ ጥናታዊና ውብ ሕንፃ ለኳስ ሜዳ ተብሎ፣ ፊት በር (ሸራተን) የነበረው የሊጋባ ጥንታዊ ሕንፃ መፍረሳቸው ስጋት ስላስከተለ ነው የሥጋት ድምፅ የተስተጋባው፡፡ የሆኖ ሆኖ ከባለሥልጣኑ ተወካይ በተጨማሪ ዋና ሥራ አስኪያጁ የእንደማይፈርስ ማረጋገጫ መስጠታቸው ጥሩ ነው፡፡ (ዞሲማስ ሚካኤል፣ ከለገሀር) ንብረትን ከምዝበራ እንታደግ ሰኔ 22 ቀን 2000 ዓ.ም በወጣው የሪፖርተር ጋዜጣ በቃሊቲ ምግባ አክስዮን ማኅበር ውስጥ በአመራር ላይ ያሉት ኃላፊዎች ለሙስና የተመቻቸ አሰራር በመጠቀም በፋብሪካው 3 ንብረትና ገንዘብ ላይ ጉዳት በመድረሳቸው ሰራተኛው አቤቱታ ከማቅረቡም በላይ የራሱን እርምጃ እስከመውሰድ እንደደረሰ መገለጹ ይታወሳል፡፡ ሠራተኛው ለሚመለከታቸው አካላት በየጊዜው አቤቱታውን አቅርቦ ሰሚ አላገኘም፡፡ ይህ ጉዳይ በብዙዎቹ የሀገራችን የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ውስጥ በግዢና ሽያጭ ላይ የሚታይ ችግር በመሆኑ የሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት፣ የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ለሚቀርብላቸው አቤቱታ ትኩረት ሰጥተው መዝባሪዎችን ለሕግ በማቅረብ የፋብሪካዎችን ንብረትና ገንዘብ ከምዝበራ መከላከል ይጠበቅባቸዋል፡፡ (ማቴዎስ ሸመሎ፣ ከሐዋሣ) የሰንደቅ ዓላማ ቀን ግንቦት 30 ቀን የተከበረውን የሰንደቅ ዓላማ በማስመልከት እሑድ ሰኔ 29 ቀን 2000 በሪፖርተር ጋዜጣ የወጣውን ጽሁፍ አንብቤዋለሁ፡፡ ኢትዮጵያውያን ለዚህ አረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ ሰንደቅ ዓላማቸው ውድ ሕይወታቸው ሳይቀር ቤዛ አድርገዋል፡፡ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ቋሚ የመከበሪያ ቀን ተቆርጦለት በብሔራዊ ደረጃ እንዲከበር መደረጉ ይበል የሚያሰኝ ነው፡፡ ሃሳብ አመንጪውም ሊመሰገኑ ይገባል፡፡ ነገር ግን ከዚህ በፊት አልተነሣም እንጂ ሃሳብ ያመነጨ አልነበረም? (ሙሉጌታ ቶሬሳ፣ ከስድስት ኪሎ) እንግዳን መንከባከብ ባህላችን ነው ባለፈው ረቡዕ በፖለቲካ ገጽ ላይ በአዲስ አበባ ስለተደረገው የኤርትራ ስደተኞች የተቃውሞ ሰልፍ አንብቤ ያለሁ፡፡ ኤርትራውያን በአገራቸው ውስጥ ባለው ፍትሃዊ ያልሆነ አስተዳደር ምክንያት እየተሰደደዱና እየተበተኑ ይገኛሉ፡፡ ይህ ሆኖ እያለ ግብፅና ሊቢያ ከሞት ለመሸሽ ወደ አገራቸው የገቡ ኤርትራውያንን አስረው በግዳጅ ለሻዕቢያ መንግሥት አሳልፈው እየሰጧቸው ይገኛሉ፡፡ መንግሥታቱ ከኢሳይያስ ጋር ያላቸው ግንኙነት ለማጠናከር ሲሉ ይህንን የመሰለ ኢሰብዓዊ ድርጊት መፈጸማቸው ተገቢ አይደለም፡፡ በተቃራኒው ወደ ኢትዮጵያ የገቡ እስከ 30ሺህ የሚደርሱ የኤርትራ ስደተኞች አያያዝ የሁለቱ አገር ሕዝቦች መልካም ወዳጅነት የሚያሳይ ነው፡፡ መንግሥት የተለያዩ አማራጮችን በመፍጠር የስደተኞችን ሕይወት ለማሻሻል ጥረት በማድረጉ ኢትዮጵያን አመሰግናለሁ፡፡ እንግዳን የመንከባከብ ባህላችን ይቀጥል፡፡ (ወርቅነህ፣ ከቂርቆስ) በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ ይደረግ በሪፖርተር ጋዜጣ ሰኔ 22 ቀን 2000 ገጽ ድርቁን ያገነኑት የመያድ ሕግ እንዳይፀድቅ የሚፈልጉ ወገኖች ናቸው.. በሚል ርዕስ የቀረበው ዜና የሚያስገርምና የሚያሳዝን ነው፡፡ በመጀመሪያ እነዚህ ወገኖች የድርቁን ሁኔታ ማጋነናቸውን የሚያመለክት ተጨባጭ የሆነ ማስረጃ በዜናው ላይ አልተካተተም፡፡ የመያድ ሕግ መፅደቅና አለመፅደቅ ከድርቁ ጋር እንዴት እንደተያያዘ አልገባኝም፡፡ ድርቁን አጋንነዋል የተባሉትን በድፍኑ “ወገኖች” ከማለት ይልቅ ትክክለኛ መጠሪያቸውንና ወይም ማንነታቸውን በግልጽ ማሳወቅ ነበር፡፡ እነዚህም ወገኖች ድርቁን ማባባሳቸውን እውነት መሆኑና አለመሆኑ ደግሞ መጠየቅ ይገባቸዋል፡፡ ከዚህ ውጭ ድፍንፍን ያለ ምክንያት በማቅረብ የሥራ ጊዜን ከማባከን ይልቅ በድርቁ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች መንግሥት በአስቸኳይ ሊደርስላቸው ይገባል፡፡ (አብርሃም አበበ፣ ከካዛንቺስ) ያልደገፈ ሁሉ መሰደብ አለበት? “ኢሕአዴግ የኦዲት ሪፖርቱን በመቃወም የውሳኔ ሀሳብ አቀረበ” የሚል ዜና ሰኔ 29 ቀን 2000 ዓ.ም በሪፖርተር ወጥቷል፡፡ ጠቅላይ ሚንስትሩ የሂሳብ ሰራተኛ ሊሰራው የማይገባ ስህተት ነው፡፡ ግፋ ቢል አለማወቅ ነው” በማለት የፌዴራል ዋናው ኦዲተር ሪፖርትን ተቃውመዋል፡፡ የፌዴራል ዋናው ኦዲተር እውቅና የተሰጠውና በውስጡም ሰርቲፋይድ የሆኑ ኦዲተሮች ያሉበት መሆኑ ይታወቃል፡፡ ሆኖም አቶ መለስ “ተራ የሂሳብ...” ብለው የአንድ ሉዓላዊ አገርን ኦዲት ሪፖርት ወክለው የሚሰሩ አካላትን ማጣጣላቸው ራሱን መንግሥትን ትዝብት ውስጥ የሚጥል ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ነፃና ወገን ኦዲቱን እንዲያጣራ ጠይቀዋል፡፡ የሚቋቋመውን ገለልተኛ ወገን ምንአልባት እርሳቸው ባይደግፍ ላለማጣጣላቸው ምን ዋስትና ይኖራል? ( በላይ፤ ከአዲስ አበባ) |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |