Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
Jul 20th
Home arrow Sections arrow በኬንያ ትምህርት ቤቶች ተከፈቱ
በኬንያ ትምህርት ቤቶች ተከፈቱ Print E-mail
Wednesday, 16 January 2008

በኬንያ የፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ውጤትን ተከትሎ በተነሳው ግጭት ምክንያት የተዘጉት ትምህርት ቤቶች ተከፍተው ሥራ መጀመራቸውን ቢቢሲ ዘገበ፡፡

በአብዛኛው የአገሪቱ ክፍል የሚገኙ ትምህርት ቤቶች የተከፈቱ ሲሆን አንዳንድ ትምህርት ቤቶች ግን በግጭቱ በደረሰባቸው ጉዳት ምክንያት የመማር ማስተማር ስራን መስራት አለመቻላቸው ተገልጿል፡፡ የትምህርት አመራር ባለስልጣናት በበኩላቸው ትምህርት ቤቶች ቢከፈቱም አስተማሪዎችና ተማሪዎች ያልተገኙ መሆኑ እንዳሳሰባቸው አስታውቀዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ የአገሪቱ የተቃዋሚ ፓርቲ ሶስት ቀን የሚቆይ የተቃውሞ ሰልፍ እንደሚጠራ ማስታወቁን ተከትሎ ውጥረት መንገሱ ታውቋል፡፡ በቅርቡ በአገሪቱ በተካሄደው ግጭት ምክንያት ከስድስት መቶ በላይ ሰዎች መገደላቸውና ከሁለት መቶ ሃምሳ ሺ በላይ ሰዎች መፈናቀላቸው ይታወሳል፡፡

የፈረንሳይ የእርዳታ ሰራተኞች ፍርድ ቤት ቀረቡ

በቅርቡ ቻድ ውስጥ ሕፃናትን በማስኮብለል ወንጀል ተከስሰው የተፈረደባቸው የፈረንሳይ የእርዳታ ሰራተኞች ፈረንሳይ ውስጥ ፍርድ ቤት መቅረባቸውን የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘገባ አመለከተ፡፡

የእርዳታ ሰራተኞቹ የቻድ ፍርድ ቤት ስምንት አመት እስራትና የከፍተኛ ሥራ ቅጣት ፈርዶባቸው እንደነበር ይታወሳል፡፡ በፈረንሳይ መንግስት ጥያቄ መሰረት ወንጀለኞቹ በአገራቸው ውስጥ ቅጣታቸውን እንዲፈጽሙ ተፈቅዷል፡፡ ይህንኑ ተግባራዊ ለማድረግ በፈረንሳይ ፍርድ ቤት መቅረባቸው ታውቋል፡፡ በዘገባው መሰረት ወንጀለኞቹ ከአገሪቱ የወንጀል ቅጣት ጋር በሚጣጣም ሁኔታ የሚፈርድባቸው መሆኑ ታውቋል፡፡

የደቡብ አፍሪካ ፍርድ ቤት ሰለቢ ላይ የተጀመረውን ክስ ውድቅ አደረገ

የደቡብ አፍሪካ አቃቤ ሕግ የአገሪቱ ፖሊስ አዛዥ ሚስተር ሰለቢ ላይ የመሰረተውን የሙስና ወንጀል ክስ ውድቅ ማድርጉን ቢቢሲ ከስፍራው ዘገበ፡፡

ሚስተር ሰለቢ ባለፈው ሳምንት በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ክስ ተመስርቶባቸው እንደነበር ይታወቃል፡፡ ሚስተር ሰለቢ ምንም አይነት የወንጀል ድርጊት አለመፈፀማቸውን በመግለጽ ውንጀላው መሰረተ ቢስ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ የአገሪቱ የወንጀል ምርመራ ቡድን ሚስተር ሰለቢ በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ማድረጉ ይታወሳል፡፡ ሚስተር ሰለቢ አንድ መቶ ሰባ ሺ ዶላር ተቀብለው የወንጀል ድርጊት እንዲፈፀም አድርገዋል በማለት ነበር የአገሪቱ የወንጀል ምርመራ ባለስልጣን የከሰሳቸው፡፡ ሚስተር ሰለቢ የደቡብ አፍሪካ እንዲሁም የአለም አቀፍ የፖሊስ ተጠሪ ነበሩ፡፡ ከውንጀላው በኋላ በራሳቸው ፈቃድ ስልጣናቸውን ለቀዋል፡፡

የእስራኤልና የፍልስጥኤም ባለስልጣናት የሰላም ውይይት ጀመሩ

የእስራኤልና የፍልስጥኤም ባለስልጣናት በአካባቢው ሰላም የሚሰፍንበትን መንገድ ለማፈላለግ በእየሩሳሌም ውስጥ ውይይት መጀመራቸውን የቢቢሲ ዘገባ አመለከተ፡፡

በውይይቱ ላይ የእየሩሳሌም ሁኔታ፣ የፍልስጥኤም አስተዳደር፣ የአይሁዳውያን ሰፈራ፣ በዌስት ባንክ፣ የስደተኞች ጉዳይና የውሃ አጠቃቀም ሁኔታን አስመልክቶ ድርድር እንደሚደረግ ታውቋል፡፡ የፍልስጥኤም አስተዳደር ሊቀመንበር መሀመድ አባስ ርዕሰ ጉዳዮቹን በተመለከተ ስምምነት ላይ ከተደረሰ በአካባቢው ሰላም ይሰፍናል ሲሉ አስተያየታቸውን ገልፀዋል፡፡

 
< Prev   Next >