| ከሱዳን ጋር የቤንዝን ግዥ ስምምነት ተፈረመ |
|
|
| Wednesday, 16 January 2008 | |
|
በኢትዮጵያና በሱዳን መካከል የአንድ ዓመት የቤንዚን ግዥ ስምምነት ተፈረመ፡፡ ለአንድ አመት ኮንትራት የተራዘመው የቤንዚን ግዥ ስምምነት ከአምስት አመት በፊት የተደረገው ስምምነት ከመጠናቀቁ በፊት በቀረበ ጥያቄ መሆኑን የኢትዮጵያ ማዕድንና የሃይል ምንጭ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ የኢትዮጵያ ነዳጅ ድርጅት የግዥውን ስምምነት የማስፈፀም ኃላፊነት አለበት፡፡ ስምምነቱን የተፈራረሙት የኢትዮጵያ ነዳጅ ድርጅት ሥራ አስኪያጅና የሱዳን የነዳጅ ኮርፖሬሽን ዳይሬክተር ናቸው፡፡ ኢትዮጵያዊው በለንደን ዕጩ ሆነው ተመረጡ የኢትዮጵያ የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ዳይሬክተር ዴነራል ዶ/ር ተወልደ ብርሃን ገብረ እግዚአብሄር በለንደኑ ጋርዲያን አንሊሚትድ ፕላኔቶቻችንን መታደግ የሚችሉ ሃምሳ ሰዎች ብሎ ከሾማቸው ሳይንቲስቶች መካከል አንዱ ዕጩ ሆነው ተመረጡ፡፡ በመጥፋት ላይ ያሉ የሰሜንና የደቡብ ዋልታ ድቦች፣ በመቅለጥ ላይ ያሉ ታላላቅ የበረዶ ግግሮች፣ እየደረቁ ያሉ ወንዞችና በአስደንጋጭ ፍጥነት እዚህም እዚያም ጉዳት እያደረሱ ያሉ የውሃ ሙላቶች /ጎርፍ/ የ2007 ዋና ዋና ገጽታዎች መሆናቸውን፣ እነዚህን ጥፋቶች ለማስቆም አቅም ያለው ሰው ማን ሊሆን ይችላል? በሚል የጋርዲያን ፓናል ከዋና ዋና የአካባቢ ጥበቃ ተሟጋቾችና ለጉዳዩ ቅርበት ካላቸው ሰዎች መካከል 50 ሰዎችን የመጨረሻዎቹ የአረንጓዴው ዘመቻ አቀጣጣይ ጀግኖች በሚል ሾሟል፡፡ ሲሾም ኢትዮጵያዊ ዶ/ር ተወልደ ገ/እግዚአብሄር አንዱ ዕጩ ሆነው ተመርጠዋል፡፡ /አዲስ ዘመን ጥር 6 ቀን 2000 ዓ.ም/ በሕገ ወጥ መንገድ ወደ ሱዳን ሊወጡ የነበሩ 150 የቀንድ ከብቶች ተያዙ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የተለያዩ ወረዳዎች ተሰብስበው በህገ ወጥ መንገድ ወደ ሱዳን ሊወጡ የነበሩ 150 የቀንድ ከብቶች መያዙን የአሶሳ ዞን ንግድ ትራንስፖርትና ኢንዱስትሪ መምሪያ ገለፁ፡፡ የቀንድ ከብቶቹ በኩምሩክ፣ በጊዘን፣ በያቡስና በተለያዩ አካባቢዎች ወደ ሱዳን ሊወጡ ሲሉ የተያዙ መሆናቸውን ገልፀው፣ ከብቶቹን በህገወጥ መንገድ ለማስወጣት የሞከሩ 28 ነጋዴዎችም በቁጥጥር መዋላቸውን፣ መምሪያው ከሉካንዳ ቤት ነጋዴዎች ጋር ባደረጉት ውይይት የከብት ሥጋ በኪሎ 38 ብር ይሸጥ የነበረውን ወደ ብር 28፣ አንድ ብር ከ60 ሳንቲም ይሸጥ የነበረውን አንድ እንቁላል ወደ አንድ ብር ዝቅ እንዲል ማድረጉን ገልጿል፡፡ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ አውቶቡሶች ሥራ ሊጀምሩ ነው ሩስ አፍሮ ትሮሊ ባስ ኃ/የተ/የግል ማኅበር ከአምስት ሚሊዮን ብር በሚበልጥ ወጭ ከውጭ ያስገባቸው በኤሌክትሪክ ሃይል የሚንቀሳቀሱት ሁለት የከተማ አውቶቡሶች በቅርቡ አዲስ አበባ ውስጥ የሙከራ ሥራ እንደሚጀመሩ አስታወቀ፡፡ በኤሌክትሪክ ኃይል የሚንቀሳቀሱት አውቶቡሶቹ ወደ አገር ውስጥ የገቡት መንግስት በፈቀደው ከቀረጥ ነፃ እድል ሲሆን፣ አካል ጉዳተኞችን ከግምት ውስጥ በማስገባት የተሰሩትና 130 ሰዎችን የመጫን አቅም እንዳላቸውና የመንገድና የትራንስፖርት ባለስልጣን ከጊዮርጊስ እስከ አዲሱ ገበያ ያለውን መስመር የፈቀደ መሆኑን ገለጿል /ኢዜአ/
አካባቢያዊ ችግሮችን በባህላዊ የግጭት መፍቻ ዘዴ ለመቅረፍ የተደረገው ጥረት ውጤት እያስገኘ መሆኑን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የልማት ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ የሃይማኖት አባቶች በእምነት መርሆዎች፣ የአገር ሽማግሌዎች፣ በባህላዊ ዘዴዎች ችግሮችን ለመፍታት የሚያደርጉት ጥረት በአገራችን ታሪክ ልዩ ቦታ ያለውና ታላቅ እሴት መሆኑን ገልጿል፡፡ /ዋኢማ/ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |