Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Friday
Aug 29th
Home arrow Sections arrow የሱዳኑ ኘሬዚዳንት በዘር...
የሱዳኑ ኘሬዚዳንት በዘር... Print E-mail
Sunday, 13 July 2008

የሱዳኑ ኘሬዚዳንት በዘር ማጥፋት ወንጀል ሊከሰሱ ነው

የሱዳን ኘሬዚዳንት ኦማር ሐሰን አልበሽር በዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት ከዘር ማጥፋት ወንጀል ጋር በተያያዘ ክስ ሊመሰረትባቸው እንደሚችል ቢቢሲ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ምንጮችን ጠቅሶ ዘገበ፡፡

 

የዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት ዐቃቤ ሕግ ከኘሬዚዳንቱ ክስ ጋር በተያያዘ ማስረጃዎቹን ነገ ያቀርባል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

አልበሽር የዓለም አቀፉን ማህበረሰብ ተደጋጋሚ ክስ ሲያስተባብሉ መቆየታቸውን ቢቢሲ አስታውሷል፡፡

ባለፉት አምስት ዓመታት በዳርፉር ብቻ ከሁለት ሚሊየን በላይ ሕዝብ የመንግሥት ድጋፍ ባለው ጃንጂዊድ የተሰኘ ታጣቂ ሚሊሺያ መገደላቸውን አስታውሷል፡፡

የዓረብ ዝርያ አለው የሚባለው ጃንጂዊድ ሚሊሽያ በጥቁር የአካባቢው ነዋሪ ሲቪሎችን የጥቃቱ ዒላማው አድርጎ ኖሯል፡፡

የዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት ዐቃቤ ሕግ በነገው ዕለት ማስረጃዎቹን ለፍርድ ቤቱ ካቀረበ በኋላ በኘሬዚዳንት ኦማር አልበሽር ላይ የእሥር ትዕዛዝ እንደሚያወጣ አስታውቋል፡፡

በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሱዳን አምባሳደር አብዱል መሐመድ አብዱል ሐሊም መሐመድ ለዋሽንግተን ፖስት እንደተናገሩት "ዐቃቤ ሕግ አካምፓ በእሳት እየተጫወቱ ነው" ሲል ማስፈራሪያ አዘል አስተያየት ሰጥተዋል፡፡



የሶማሊያው ጠቅላይ ሚኒስትር የሰላም ጥሪ አቀረቡ

ላለፉት 18 ዓመታት በጦርነት ስትታመስ የቆየችው ሶማሊያ በቅርቡ የሰላም ተስፋ እየታየባት መሆኑ አጃንስ ፍራንስ ኘሬስ ዘገበ፡፡

እንደዘገበው የሶማሊያው ጠቅላይ ሚኒስትር የአገራቸው ህዝብ ሁሉ በአገሪቱ ሰላም እንዲሰፍን ለአንድ ወር የተደረሰውን የሰላም ስምምነት እንዲደግፍ የሰላም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ከደች የእርዳታ ሚኒስትር በርት ኮንደርስ ጋር ከተወያዩ በኋላ "ከ18 ዓመታት ችግርና መከራ በኋላ ዛሬ የሰላም አዲስ ተስፋ አለ፡፡ መረጋጋት ምናልባት በሶማሊያ መልሶ ሊመጣ ይችላል" ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ኑር ሃሰን ሁሴን ተናግረዋል፡፡

"መንግሥት፣ ባህላዊ መሪዎች፣ ሃይማኖታዊ ወኔዎች እንዲሁም ዲያስፖራው ተባብሮ ከሰራ በሱማሊያ ሰላም ለማምጣት ይቻላል" ሲሉም ሚ/ር ኑር ሁሴን ገልፀዋል፡፡


የዙምባቡዌ ገዢው ፓርቲና ተቃዋሚዎች እየተወያዩ ነው


በዙምባቡዌ ገዢ ፓርቲ (ዛኑ) እና ሙቭመንት ዴሞክራቲክ ቼንጅ መካከል ይፋዊ ባልሆነ መንገድ በደቡብ አፍሪካ አደራዳሪነት ውይይት ለመጀመር በሚያስችል ሁኔታ ላይ መምከር ጀመሩን ቢቢሲ አስታወቀ፡፡

በዙምባቡዌ ከኘሬዚዳንታዊ ምርጫ በኋላ የተከሰተውን ቀውስ ተከትሎ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታ ካውንስል አስገዳጅ ማዕቀብ ለመተግበር በእንቅስቃሴ ላይ በሚገኝበት በዚህ ወቅት ከምርጫው በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ሁለቱ ወገኖች ሐሙስ ዕለት ይፋዊ ባልሆነ መንገድ በደቡብ አፍሪካ መገናኘት ችለዋል፡፡

ሁለቱ ወገኖች በዚሁ ምክክራቸው ለቀጣይ ውይይት የሚሆኑ አጀንዳዎች በመቅረፅ የጋራ መግባባት ላይ መድረስ፣ ጉባዔ አደራጅ ኮሚቴ መሰየም ይሰይማሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ሆኖም ሕትመት እስከገባንበት ከትላንት በስቲያ ምሽት ድረስ ስለሁለቱ ወገኖች ውይይት የተገለፀ አዲስ ነገር የለም፡፡


ፖሊስ በኦልመርት ላይ ምርመራ አካሄደ

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ኢሁድ ኦልመርት በሙስና ተጠርጥረው በፖሊስ እየተመሩ መሆኑን የቢቢሲ ዘገባ አመለከተ፡፡

በዘገባው መሠረት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስልጣን ከመያዛቸው በፊት ፈፅመውታል ተብለው በተጠረጠሩበት የሙስና ወንጀል ፖሊስ ምርመራ እያካሄደ መሆኑ ታውቋል፡፡ የሀገሪቱ ፖሊስና የፍትህ ሚኒስቴር በጋራ ባወጡት መግለጫ "ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከእስራኤል ውጭ ላደረጉት ጉብኝት ከመንግሥት ተቋማት በተጭበረበረ ሁኔታ ከፍተኛ ገንዘብ ወስደዋል" በሚል የተጠረጠሩ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

በተያያዘ ዜና ኦልመርት ስልጣን ከያዙ በኋላ ከአሜሪካው የፋይናንስ ባለሙያ ሞሪስ ታላስኪ በመቶ ሺዎች የሚቆጠር ገንዘብ በጉቦ መልክ መቀበላቸውን አስመልክቶ ፖሊስ ምርመራ እያደረገ መሆኑ ታውቋል፡፡ ሞሪስ ታላስኪ በበኩላቸው "ገንዘቡን የሰጠሁት በጉቦ መልክ ሳይሆን በስጦታ መልክ ነው" ሲሉ ገልፀዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በበኩላቸው ገንዘቡን ለምርጫ ቅስቀሳ ማዋላቸውን አስታውቀዋል፡፡

 
< Prev   Next >