| የልማት ትብብሩ አራት ፕሮጁክቶችን... |
|
|
| Sunday, 13 July 2008 | |
|
የልማት ትብብሩ አራት ፕሮጁክቶችን ተግባራዊ ማድረግ ጀመረ
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የልማት ትብብር በጤናና በትምህርት ላይ ትኩረት ያደረጉ አራት ፕሮጄክቶችን በሶስት የመንግሥት ትምህርት ተቋማት ውስጥ መጀመሩን የብሪቲሽ ካውንስል ሐምሌ 4 ቀን 2000 ባወጣው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ አስታወቀ፡፡ የመምህራንና የተማሪዎችን እውቀት፣ ችሎታና ብቃት ወደ ላቀ ደረጃ ከፍ ለማድረግ ያስችላሉ የተባሉት እነዚሁ ፕሮጀክቶች ተግባራዊ የሚሆኑት በአዲስ አበባ፣ በባህርዳር እና በአዳማ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ መሆኑን መግለጫው አመልክቷል፡፡ እነዚሁ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ለፕሮጀክቱ ተግባራዊነት ለንደን ከሚገኙት ኪንግ ኮሌጅ፣ ሌድስ ሜትሮፕሌታንና ሳውዝአፕተን ዩኒቨርስቲዎች ጋራ ተባብረው እንደሚንቀሳቀሱ መግለጫው ያስረዳል፡፡ ከመግለጫው ለመረዳት እንደተቻለው በትምህርት፣ በጤና፣ በሳይንስ፣ በሠላምና ደህንነት ላይ ትኩረት ያደረገው ይሄው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የልማት ትብብር የሚንቀሳቀሰው በዩናይትድ ኪንግደም ዓለም አቀፍ የልማት ዲፓርትመንት በሚመደብ በጀት ነው፡፡ የልማት ትብብሩ በዩናይትድ ኪንግደምና በኢትዮጵያ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መካከል ለሦስት ዓመት የሚቆይ መሆኑንም መግለጫው ይፋ አድርጓል፡፡ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |