| የንግድ ባንክ ባለሙያዎች የመንግሥትን... |
|
|
| Wednesday, 16 July 2008 | |
|
የንግድ ባንክ ባለሙያዎች የመንግሥትን ፖሊሲና ስትራቴጂ እያጠኑ ነው
በጋዜጣው ሪፖርተር
ከሐምሌ 7 ቀን 2000 ዓ.ም ጀምሮ ሲኤምሲ አካባቢ በሚገኘው የኢትዮ ቻይና ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ እየተካሄደ ባለው ሥልጠና ላይ የባንኩ ከፍተኛ ባለሙያዎች መሳተፋቸውን ምንጮቻችን ተናግረዋል፡፡ የባንኩ ባለሙያዎች በዚሁ ሥልጠና ላይ የኢፌዴሪ የውጪ ጉዳይና የአገራዊ ደህንነት ፖሊሲና ስትራቴጂ፣ የኢፌዴሪ የኢንዱስትሪ ልማት ስትራቴጂ፣ የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ጉዳዮች ስትራቴጅ፣ የገጠር ልማት ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች ስልቶች፣ የኢፌዴሪ መንግሥት የማስፈፀም አቅም ግንባታ ስትራቴጂና ፕሮግራም በሚሉት ርዕሶች ላይ ትምህርትና የቡድን ውይይቶች ይካሄዳሉ፡፡ ቀደም ብሎ ባንኩ ባሳወቀው ፕሮግራም መሰረት ሥልጠናው ለ11 ቀናት ይካሄዳል ከተባለ በኋላ ወደ 16 ቀናት መራዘሙ እንደተነገራቸው ምንጮቻችን ጠቁመዋል፡፡ የንግድ ባንክ ሐምሌ 2 ቀን 2000 ዓ.ም በአቶ ሰይፉ ቦጋለ ፊርማ ለሠራተኞቹ ይፋ ባደረገው የሥልጠና መግለጫ ላይ እንደተመለከተው በሥልጠናው ሂደት ተሳታፊዎች ንቁ ተሳትፎ ማድረጋቸውን ለመመዘን በዚህ ጉዳይ በተሰየሙ ገምጋሚዎች በምልከታ እና የቡድን ግምገማ እንደሚካሄድ በመጨረሻም በውጪ አካላት የፅሑፍ ፈተና እንደሚሰጥ ጠቁሟል፡፡ የፌዴራል መንግሥት የሲቪል ሰርቪስ አገልጋዮች (የመንግሥት ሰራተኞች) የመንግሥትን ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች ጠንቅቀው ሊያውቁ ይገባል የሚል አቋም ከያዙ በኋላ ይህንኑ ለማውሳት ለተለያዩ መ/ቤቶች ሰራተኞች ተመሣሣይ ሥልጠና ሲሰጥ መቆየቱ ይታወሳል፡፡ የዚህ ዓይነቱ ሥልጠና ከገዥው ፓርቲ ፖለቲካ ጋር በቀጥታ በማስተሳሰር ተገቢ አለመሆኑን የሚተቹ አንዳንድ ወገኖች መኖራቸውም አይዘነጋም፡፡ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |