| አርሴናል መመሳቀሉን ቀጥሎበታል! |
|
|
| Wednesday, 16 July 2008 | |
|
አርሴናል ባለፉት አራት የውድድር ዓመታት አንድ ጊዜ ሁለተኛ አንድ ጊዜ 3ተኛ ሁለት ጊዜ ደግሞ 4ተኛ ሆኖ ነው ያጠናቀቀው፡፡ አመት አልፎ አመት ሲመጣ ደጋፊቹ የአሸናፊው የእነ ሆነሪ መንፈስ ወደ ቡድናቸው ተመልሶ እንደሚመጣ ተስፋቸው ሙሉ ቢሆንም፣ አሁን አሁን ከወደ ኤምሬትስ ስታዲየም የሚሰሙት ዜናዎችና መግለጫዎች ተስፋ አስቆራጭ እየሆኑ መጥተዋል፡፡ አምና ዋንጫውን ለማግኘት ቀርቦ የነበረ በመሆኑ፣ በአንዳንድ ቦታዎች ላይ ማሻሻያ በማድረግ ለአዲሱ የውድድር ዘመን የተጠናከረ ቡድን ለማየት እንደሚችል ታስቦ ነበር፡፡ ከአሽበርተን ግሮቭ ቀድሞ የተሰማው ወሬ የማቲው ፍላሚኒ ወደ ኤሲሚላን መቀላቀልን የሚመለከት ነው፡፡ በአምናው ቡድን ከነበረው የጎላ ሚና አንፃር የፍላሚኒ መልቀቅ አስደንጋጭ ነበር፡፡ ደጋፊው የፍላሚኒን ቦታ ቬንገር በምን ይተኩታል ተብሎ አሳቡ ሳይቋጭ የባሰው ችግር ተደቅኗል፡፡ የአምናው የአርሴናል ቡድን በአራት ተጨዋቾች ብቃት የጎላ ነበር፡፡ በሴስክ ፋብሪጋዝ፣ በኢማኑኤል አዴባዮር፣ በአሌክሳንደር ህሌብና በማቲው ፍላሚኒ፡፡ የፍላሚኒ መሄድ ሳይወጣላቸው አዲባዮርና ህሌብ ወደ ኤሲ ሚላንና ባርሴሎና ለማቅናት መዘጋጀታቸው ተሰማ፡፡ የአስቶንቪላው ጋሬት ባሪ፣ የአያክሱ ክላር ያን ሁንትላር፣ የሪቨር ፕሌቱ ፋልካኦ፣ የዜኒት ፒተስበርጉ አርሻቪን፣ የኒውካስትሉ ቻርለስ ንዞግቢያ ስማቸው ከአርሴናል ጋር የተያያዙ ተጨዋቾች ቢሆኑም፣ አንዳቸውም የአርሴናል ምዕላድ የነበሩትን የፍላሚኒን፣ የአዲባዮርንና የህሌብን ቦታ በመተካት ለደጋፊዎቹ መጽናኛን ማምጣት አይችሉም፡፡ አርሴናል እንደ ሳሚር ናስሪና አሮን ራምሲ አይነት ወጣት ተጨዋቾችን ከማለማመድ ልምድ ያለውና ጨዋታ ማሸፍ የሚችል ተጨዋች ለምን አያስፈርምም? ተብሎ ሲጠየቅ ሁለት ምላሾች ይሰጣሉ፡፡ አንዱ አርሴናል የገንዘብ አቅም የለውም፡፡ ታላላቆቹ ተጨዋቾች ክለቡን የለቀቁትም የደመወዝ ጭማሪ አርሴናል ለማድረግ አቅም ስለሌለው ነው የሚል ነው፡፡ ሌላኛው ደግሞ ቬንገር በክለቡ ውስጥ ካላቸው ተሰሚነት አንፃር የክለቡን የአመራር ዘዴ ቢቃወም፣ መለወጥ ስለሚቻል ዞሮ ዞሮ ቬንገር የአሁኑን ስርዓት ከተቀበሉት እሳቸው ተጠያቂ ናቸው የሚል ነው፡፡ ምንም ይሁን እውነታው በሊቨርፑል፣ ቼልሲና ማንችስተር ዩናይትድ እየተካሄደ ባለው ለውጥና እድገት ጋር አርሴናል ተወዳዳሪ ሆኖ መቀጠሉ አጠራጣሪ ነው፡፡ እነ ቶተነሀም፣ ፓርትስማውዝና ማንችስተር ሲቲ ወደ አርሴናል ይበልጥ እየተጠጉ ሲሆን፣ አርሴናል ይበልጥ መመሳቀሉን ቀጥሎበታል፡፡ ቬንገር በአርሴናል ላይ የሚሰነዘሩ ቅድመ ግምቶችንና ትንቢያዎችን በማፋለስ የተሳካላቸው አሰልጣኝ ቢሆኑም፣ ዘመኑ ለታማኝነት ያለው ቦታ የጠበበ ከመሆኑ አንፃር ፍልስፍናቸው በገንዘብ የማያበረታታ በመሆኑ፣ ምስቅልቅሉን ቤታቸውን ለማረጋጋት አቅሙ ያላቸው አይመስሉም፡፡ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |