| በእንስሳት ማድለብ ሥራ 1ዐ... |
|
|
| Wednesday, 16 July 2008 | |
|
በእንስሳት ማድለብ ሥራ 1ዐ ሚሊዮን ብር ትርፍ ተገኘ
በእንስሳት ማድለብ ሥራ የተሰማሩት ዘጠኝ ሺ 7ዐዐ አርሶ አደሮች ሲሆኑ፣ እያንዳንዳቸው በአማካኝ አንድ ሺህ ብር ትርፍ ማግኘት መቻላቸውን ገልጿል፡፡ (ኢዜአ) ዞኑ በ30 ኩሬዎች የዓሣ እርባታ ጀመረ በምዕራብ ጐጃም ዞን በ30 ኩሬዎች የዓሣ እርባታ መጀመሩን የዞኑ ግብርናና ገጠር ልማት መምሪያ አስታወቀ፡፡ በዞኑ ሰባት ወረዳዎች በአርሶ አደሮቹ በጋራና በተናጠል ተቆፍረው በተዘጋጁት ኩሬዎች ለተጨመሩ ጫጩቶች የአትክልትና ፍራፍሬ ቅጠሎችንና ተረፈ ምርቶችን በመጨመር ምግባቸውን እንዲያገኙ እየተደረገ መሆኑን፣ አርሶ አደሮቹ በዓመት ሁለት ጊዜ በማምረት የቤተሰቦቻቸውን የምግብ ፍላጐት እንደሚያሟሉ ገልጿል፡፡ (ኢዜአ) የኤፍ.ኤም ማሰራጫ ጣቢያው በእሳት ተቃጠለ የድሬዳዋ መገናኛ ብዙሀን ንብረት የሆነው ኤፍ ኤም ሬዲዮ ማሰራጫ የእሳት ቃጠሎ ደርሶበት ከአንድ ነጥብ ሦስት ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ንብረት መውደሙን የአስተዳደሩ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ የተለያዩ ኘሮግራሞችን በማስተላለፍ ላይ የነበረው ጣቢያው ሐምሌ 6 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. ከቀኑ 9 ሰዓት ከ5ዐ ደቂቃ ላይ ቃጠሎው እንደደረሰበት፣ በሥራ ላይ የነበሩት ጋዜጠኞችም ጉዳት ሳይደርስባቸው መትረፋቸውንና አንድ የአራት ዓመት ሕፃን ከህንፃው ላይ ለማዳን መቻሉን ፖሊስ አስታውቋል፡፡ (ዋኢማ) ደረጃቸውን ያልጠበቁ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች ችግር እያስከተሉ ነው ወደ አገር ውስጥ የሚገቡ ደረጃቸውን ያልጠበቁ የኤሌክትሪክ እቃዎች በሀገሪቱ ምጣኔ ሀብት ላይ አሉታዊ ተፅእኖ እያደረሱ መሆናቸውን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ መሐንዲሶች ማህበር ገለፀ፡፡ ጥራትና ደረጃዎች ባለሥልጣንም አገልግሎቱን ለመጠቀም የሚፈልጉ ድርጅቶች እንደሌሉ አስታውቋል፡፡ ማህበሩ ወደ አገር ውስጥ የሚገቡ ደረጃቸውን ያልጠበቁ የኤሌክትሪክ እቃዎች የሚያደርሱትን ችግር ለመከላከል በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር አዲስ አበባ ውስጥ ባካሄደው የፓናል ውይይት በየህንፃዎቹና መኖሪያ ቤቶች ላይ የሚቀበሩ ኬብሎች ደረጃቸው ዝቅ ያለ መሆኑን አስታውቋል፡፡ (ኢዜአ) በመሬት ናዳ ስምንት ሰዎች ሞቱ በወላይታ ዞን በኪንዶ ዲዳዬ ወረዳ ሰሞኑን የጣለውን ከባድ ዝናብ ተከትሎ በደረሰው የመሬት ናዳ ስምንት ሰዎች ህይወት ማለፉን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ ገለፀ፡፡ በደረሰው የናዳ አደጋ ሁለት የቤተሰብ አባላት የሆኑት አራት ወንዶችና አራት ሴቶች ህይወታቸው ማለፉን፣ በዝናቡ 21 የቤት እንስሳት መሞታቸውንና 1ዐ2 መኖሪያ ቤቶችን ጨምሮ የጓሮ አትክልት መውደሙን አስታውቋል፡፡ (አዲስ ዘመን ሐምሌ 7 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም". ባንኩ ለወላጅ አልባ ህፃናት እርዳታ ሰጠ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በለገዳዲ አካባቢ ለሚገኘው ለፅጌ ታደሰ ወላጅ አልባ ህፃናት ማሳደጊያ የተለያዩ ቁሳቁስና ለአንድ ወር ቀለብ የሚሆን የገንዘብ ድጋፍ ሰጠ፡፡ ባንኩ እርዳታውን ሊያደርግ የቻለው በመገናኛ ብዙሀን የድርጅቱን ታሪክና ያለበትን ችግር በመስማቱ ሲሆን፣ ስኘሪንግ ፍራሾች፣ አልጋ ልብሶች፣ ብርድ ልብሶች፣ ትራስ፣ ጥንድ አንሶላዎች፣ ደብተሮችና የተለያዩ ነገሮች እንደሚገኙበት አስታውቋል፡፡ (ኢዜአ) |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |