Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
May 18th
Home arrow Sections arrow ሄክቶር የተባለ ትልቅ ኮምፒዩተር ተሰራ
ሄክቶር የተባለ ትልቅ ኮምፒዩተር ተሰራ Print E-mail
Wednesday, 16 January 2008

የሳይንሱን ዓለም ወደፊት ያራምዳል የተባለው ትልቁ ኮምፒዩተር ሄክቶር (ሃይ ኢንድ ኮምፒዩቲንግ ቴራስኬል ሪሶርስስ) የተሰኘ ሲሆን 63 ሚሊዮን ሂሳቦችን በሰኮንድ ያሰላል ተብሏል፡፡

እንደ ቢቢሲ ዘገባ ኮምፒዩተሩ ከሌሎች ኮምፒዩተሮች በአራት እጥፍ ፈጥኖ ነገሮችን ይከውናል፤ ከአስራ ሁለት ሺህ የዴስክ ቶፕ ሲስተሞች ጋር እኩል እንደሆነም ተነግሯል፡፡

የኤደንበርግ ዩኒቨርሲቲ ቃል አቀባይ እንደተናገሩት ኮምፒዩተሩ የተለያዩ ሳይንሳዊ ጥናቶችን ለማፋጠን እንዲያገለግል ታስቦ የተሰራ ሲሆን በህይወት አድን መድሃኒቶችና በሞዴል የአካባቢ ጥበቃና የብዝሃ ህይወት እንክብካቤ ጋር የተያያዘ ጥናት ለሚሰሩ ሳይንቲስቶች የ113 ሚሊዮን ፓውንድ የስድስት ዓመት በጀት ተመድቧል፡፡

ቃል አቀባዩ አክለው እንደገለፁት ሱፐር ኮምፒዩተሩ አጥኚዎችን ወደፊት እንዲራመዱ ከማገዙም በላይ በግኝትና ፈጠራ ላይም ሳይንስን ከአንድ እርከን ወደ ሌላኛው ያሸጋግራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የኤደንበርግ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪ የሆኑት ዶ/ር ዴቪድ ሄንቲ በበኩላቸው እስካሁን ድረስ ዘልማዳዊ የሳይንስ አሰራሮች በቲዮሪና ሙከራ/በኤክስፐርመንት እንደሚሰሩ ጠቁመው በእስክሪፕቶና ወረቀት የሚሰሩ ጥናቶች ከጥናትና ምርምር አኳያ ኋላ ቀር በመሆናቸው የዚህ ሱፐር ኮምፒዩተር መሰራት ፕሮግራሞችን ያቃልላል ብለዋል፡፡ እንደ ዶክተሩ አባባል በዚህ ኮምፒዩተር ከንዑስ የአቶሚክ ቅንጣት ያነሱ ነገሮችን በማግዘፍ ስለሚያሳይ ለመመልከት አይከብድም፡፡

የአውሮፓ ባዮፊውል መመሪያ እንዲሻሻል ተጠየቀ

የአውሮፓ አካባቢ ጥበቃ ሃላፊ ከሰሞኑ ለቢቢሲ እንደገለፁት የአውሮፓ ህብረት በመመሪያዎቹ ሳቢያ የሚመጡ ችግሮችን እንዲያጤን ጠይቀዋል፡፡

በቅርቡ የወጡ ሪፖርቶች እንደሚያመለክቱት የምግብ ዋጋ ንረትና የደን መጨፍጨፍ ምክንያት የባዮፊውል መጠናከር ነው ተብሏል፡፡ የአውሮፓ ህብረትም አዲስ ፖሊሲ በማውጣት የሚደርሰውን ጥፋት እከላከላለሁ ሲል ቃል መግባቱን ቢቢሲ አመልክቷል፡፡

የአውሮፓ ህብረት የአካባቢ ጥበቃ ኮሚሽነር ስታረቮስ ዲማስ እንደተናገሩት አካባቢያዊ ችግሮች በባዮፊውል ምክንያት እንደሚከሰቱና ይህም ለማህበራዊ ቀውስ መንስኤ መሆኑን ስለተረዳን በከፍተኛ ጥንቃቄ እያጤነው ነው ብለዋል፡፡

ኮሚሽነሩ እንደገለፁት ቀጣይነት ያለው ቅድመ ሁኔታ የነደፉ ሲሆን ይህም ማህበራዊና አካባቢያዊ ጉዳዮችን ያጠቃልላል፡፡ ይህም ከባዮፊዮል የተለያዩ ጠቀሜታዎችን ያስገኛል ሲሉ አብራተዋል፡፡

አዞና ዳይኖሰር የሚመስል ዝርያ ተገኘ

የእንግሊዝ አጥኝዎች ባወጡት ሪፖርት እንደገለፁት ያልተለመደ የዳይኖሰርና የአዞ ዓይነት ጭንቅላት ማግኘታቸውን አስረድተዋል፡፡

ቢቢሲ እንደገለፀው ዝርያው ባርዮኒክስ ዋልከሪ የሚባል ሲሆን ከወደ ጭንቅላቱ አሳ የሚበሉ አዞዎችን የሚመስል ሲሆን በቅርፁ ግን ዳይኖሰር ይመስላል፡፡

በጥንት የክሪታሼየስ ዘመን በሎሬይ እንደተገኘ የሚነገርለት ዳይኖሰር በሞቃትና ሃይቅ ዳር አካባቢዎች ይኖር እንደነበር ጥናቶች ያመለክታሉ፡፡

በአጥኝ ቡድኑ የታተመው ጆርናል እንደሚያስረዳው ባርዮኒክስና አሣ የሚበላው አዞ ተመሳሳይ ረጅም ስለታማ ጥርሶች አላቸው፡፡

የጥናት ቡድኑ መሪ ዶ/ር ኤሚሊ ሬይፊልድ እንደገለጹት ባሪዮኒክስ ጠባብና ሞላላ ጭንቅላት ሲኖረው አዞዎቹ ግን ጠፍጣፋ ወይም ቲዩብ መሰል ቅርፅ አላቸው ብለዋል፡፡

የተለያዩ ቴክኒኮችን በማቀናጀት የጥናት ቡድኑ እንዳረጋገጠው የሁለቱም ጭንቅላት ስሪት ግን ተመሳሳይ ሆኖ ተገኝቷል፡፡

የለንደን ተፈጥሮ ታሪክ ሙዚየም ተባባሪ ኃላፊ የሆኑት ዶ/ር አንጀላ ማይልነር በበኩላቸው ምንም እንኳን የባሪዮኒክስና አሣ ተመጋቢው አዞ አመጋገባቸው ራሱን የቻለ ተመሠሣይነት ቢኖረውም የጭንቅላታቸው አሠራር ግን በዝግመተ ለውጥ ምክንያት በተለያዩ መንገዶች ተመሳሳይ ሊሆን ችሏል ብለዋል፡፡

ወደ ሜሪኩሪ መንኮራኩር ሊመጥቅ ነው

  ከ30 ዓመት በላይ በፕላኔቷ ዙሪያ በ200 ኪሎ ሜትር ርቀት ትዞራለች ተብላ የምትጠበቀው መንኮራኩር ሜሪኩሪን በቅርበት የምትጎበኘው ለመጀመሪያ ጊዜ ነው ተብሏል፡፡

እንደ ቢቢሲ ዘገባ በሚቀጥሉት ዓመታት በዛቢያው ዙሪያ የምትቀላቀል ሲሆን የሜሪኩሪን ትንሽ ዓለም በ2011 እንድትቀላቀል እቅድ ተይዞላታል፡፡

በዚህ እቅድ መሰረት የአሜሪካዋ መንኮራኩር ከ1ሺህ ሶስት መቶ በላይ ፎቶ ግራፎችን እንደምታነሳ የሚጠበቅ ሲሆን የተለያዩ ቅኝቶችን ታደርጋለች፡፡

በመጋቢት 1968 ዓ.ም ከተካሄደው የማሪነር 10 ቅኝት ውጭ ወደሜሪኩሪ የተደረጉ ሶስት መጠቃዎች ተጠግቶ በመጎብኘት የተሳካላቸው አልነበሩም፡፡

የናሳ ሳይንቲስት የሆኑት ማርሊን ሊንደስትሮም እንደገለፁት ሁሉም ነገር በተጠንቀቅ ይገኛል፡፡ ሜሪኩሪ በሜሴንጀር ትቃኛለች ብለዋል፡፡

ሳይንቲስቱ የሜሴንጀርን ተልዕኮ ሲያስረዱም የሜሪኩሪን ቅርፅ፣ ውስጣዊ ይዘት አካባቢያዊ ሁኔታ የምትቃኝና ሪፖርት የምታቀርብ ሲሆን ከመሬት ጋር ያላት ተመሳሳይነትና ፕላኔቷ የተሰራችበትን ቁስ ምንነትም ለመረዳት የሚያስችል መረጃ ታቀርባለች ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ሜሴንጀር በፀሐይ ዙሪያ የሰባት ዓመት ሽክርክሪት የምታደርግ ሲሆን የ53 ሚሊዮን ኪሎ ሜትር ርቀቱን 8ሺህ ኪሎ ሜትር በሰዓት ፍጥነት ትጓዛለች፡፡

ሜርኩሪ ለፀሐይ ቅርቧ ፕላኔት ስትሆን 4800 ኪሎ ሜትር ዲያሜትርና 88 ቀናት ያላት ናት፡፡  

አሜሪካውያን በኢንተርኔት የሚተላለፍ ቪዲዮ ወደ መመልከት ተመልሰዋል

አሜሪካውያን በኢንተርኔት የሚተላለፉ ቪዲዮዎችን ወደመመልከት እየተመለሱ መሆኑን ቢቢሲ ዘገበ፡፡ በኢንተርኔት ቪዲዮ የሚያስተላለፍ እንደ ዩቱብ ያሉ ድረገፆችም የተጠቃሚዎቻቸው ቁጥር በእጥፍ እንደሚጨምር ታውቋል፡፡

አሜሪካውያኑ ወደኢንተርኔት ቪዲዮ የተመለሱት ካለፈው ጥቅምት ወር ጀምሮ ሲሆን ለዚህም ምክንያቱ አሜሪካውያን ፀሐፊዎች አምፀው የሚያሳትሟቸው ፅሁፎች ስለቆሙ መሆኑን ዘገባው ያመለክታል፡፡

የፀሐፊዎቹ አመፅ እንደቀጠለ ሲሆን ይህም በሃገሪቱ ታዋቂነትን ያተረፉ ፕሮግራሞች ለሕዝብ መቅረባቸውን እንዲያቆሙ አስገድጓል፡፡ የሚያነበው ፅሁፍና የሚከተታተለው የሚስብ ፕሮግራም ያጣው ህብረተሰብም ቪዲዮዎችን ወዶ መከታተሉን እንደቀጠለ ነው፡፡

 
< Prev   Next >