Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Friday
Aug 29th
Home arrow Sections arrow "ጃንጥላና ሹራብ ሰሪ ክረምት ይወዳል"
"ጃንጥላና ሹራብ ሰሪ ክረምት ይወዳል" Print E-mail
Wednesday, 16 July 2008

Image
አቶ አራርሳ ሔርጶ
በምህረት አስቻለው

መርካቶ ራጉኤል ቤተክርስቲያን አቅራቢያ ከሚገኝ አንድ የልብስ ሱቅ ደጃፍ ላይ የተበላሹ ጃንጥላዎችን ሲጠግኑ አገኘኋቸው፡፡ አቶ አራርሳ ሔርጶ ለሃያ ዓመታት በእሳት አደጋ መከላከያ ብርጌድ ውስጥ በጥበቃነት፣ በአደጋ ተከላካይነት እንደሰሩ ይናገራሉ፡፡  አሁንም በሰራተኛ ልሸፍት ኃላፊነት እዚያው እሳት አደጋ ውስጥ በመስራት ላይ ናቸው፡፡

ባለትዳርና የሦስት ልጆች አባት የሆኑት አቶ አራርሳ የተሰበሩ ጃንጥላዎችን መጠገን የጀመሩት ከአሥራ ሁለት ዓመታት በፊት ነው፡፡ "ምን አለሽ ተራ" የተበላሹ ጃንጥላዎችን የሚጠግኑ የቅርብ ዘመዳቸው ጋር በእረፍት ጊዜአቸው ብቅ ይሉ ነበር፡፡ አንድ ቀን ጃንጥላ ጠጋኙ ዘመዳቸው ቅርብ ቦታ ደርሰው እስኪመለሱ የተሠሩ ጥላዎችን ለደንበኞቻቸው እየሰጡ እንዲጠብቋቸው አቶ አራርሳን ጠየቋቸው፡፡ ተስማሙ፡፡ ወዲያው አንዲት ሴት የተሰበረ ጥላ ለማሠራት በመምጣቷ ተቀብለው ከዘመዳቸው ባዩት መሠረት ሠርተው በማስረከብ አምስት ብር መቀበላቸውን ያስታውሳሉ፡፡

"ሥራ የምሰራው በፈረቃ ነው፡፡ የሌሊት ሽፍት በምሆንበት ወቅት ቀን ላይ ጊዜዬን ለሱስ በሚያጋልጡ ቦታዎች ከማሳልፍ በማለት ነበር ጃንጥላ ሰሪው ዘመዴ ጋ እሄድ የነበረው፡፡ ጃንጥላ ጠጋግኜ ይህ ነው የሚባል ትርፍ ባላገኝ እንኳ ጊዜዬን በሥራ በማሳለፌ የማጣው ነገር የለም፡፡ በርካታ የሥራ ባልደረቦቼ ከእንደዚህ ዓይነት ዝቅተኛ ሥራ ይልቅ ባለኝ ትርፍ ጊዜ የተሻለ ገቢ የሚያስገኝ ሥራ እንድሰራ በተደጋጋሚ ይወተውቱኛል" ብለዋል፡፡

አቶ አራርሳ እንደሚሉት፣ በርካታ ሰዎች በቋሚነት ከሚሠሩት ጐን ለጐን በማኅበራዊ ተመራጭነቱ ዝቅተኛ በሆነና ገቢውም አነስተኛ በሆነ ሥራ ላይ መሰማራትን አይደፍሩም፡፡ በከዚህ አመለካከት የተነሳም በተደጋጋሚ ከተለያዩ ሰዎች ተገቢ ያልሆኑ አስተያየት ተሰንዝሮባቸዋል፡፡ ነገር ግን ጃንጥላ በመጠገናቸው በኑሯቸው ላይ የተመለከቱትን ለውጥ ከእሳቸው የበለጠ ማንም ሊረዳው አይችልም፡፡ ከመደበኛ ሥራቸው  ውጭ የሚኖራቸው ጊዜ ሰፊ ስለሆነ ጃንጥላ መጠጋገን ባይጀምሩ ለጭንቀት፣ አስፈላጊ ላልሆነ ወጪና ለሱስ ይጋለጡ ነበር፡፡ መርካቶ ውስጥ በሥራ የሚያሳልፉት ጊዜ ያስደስታቸዋል፡፡ በማንኛውም መልኩ መደበኛ ሥራቸውን አያስተጓጉሉም፡፡

ከእሑድ በስተቀር ዘወትር ወደ መርካቶ በመሄድ በሥራ ገበታቸው ላይ ይገኛሉ፡፡ በቋሚነት ጃንጥላ የሚያሰሯቸው ሱቆችና ደንበኞችም አሏቸው፡፡ ለመጠገኛ የሚጠቀሙባቸውን የጃንጥላ ብረቶች ከቆርቆሮ ያለሽ ሲገዙ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ከደንበኞች ያገኛሉ፡፡ አንዳንድ ደንበኞች ላሰሩት ጃንጥላ እንደክፍያ በማሰብ ሌላ አሮጌ (በጣም የተሰባበረ) ጃንጥላ ይሰጣሉ፡፡ "ዣንጥላና ሹራብ ሠሪ ክረምት ይወዳል፡፡ ምንም እንኳ ጥላ ተሰብሮ እንዲመጣ ፀሎት ባናደርግም ቢሰበር ደስ ይሉናል" የሚለት አቶ አራርሳ በአሁኑ ወቅት ብዙ ነገሮች ሲወደዱ የጥላ ማሰሪያ ዋጋ ግን አለመጨመሩን ገልፀውልናል፡፡ ከፍተኛ የሚባለው የመጠገኛ ክፍያ አምስት ብር ነው፡፡ መጠናቸው ትልቅ ለሆነ የውጭ ጃንጥላዎች ጥገና ግን እስከ አሥር ብር ይጠይቃሉ፡፡

የሚኖሩት በግል ቤት ነው፡፡ ለቤት ኪራይ ደግሞ በወር አራት መቶ ብር ይከፍላሉ፡፡ ገበያ በሚኖርበት ወቅት ክረምት በቀን እስከ ሰላሳ ብር ያገኛሉ፡፡ ሳይሠሩ የሚውሉበት ጊዜም አለ፡፡ የሌሊት ተረኛ በሚሆኑባቸው ቀናት ቀጥታ ከሥራ ወደ መርካቶ (ጃንጥላ ጥገና) እንደሚመጡ ተናግረዋል፡፡ "እንደ አጋጣሚ ሆኖ ሌሊት አደጋ ተፈጥሮ ሳንተኛ ካላደርን በስተቀር ዘወትር በቀጥታ ወደ መርካቶ ነው የምመጣው፡፡ ምሳም እዚሁ እበላለሁ" በማለት ከአምስት ከማይበልጡ የጃንጥላ ጨርቆች ተደራርቦ የተሠራውን ሽርጣቸውን ጋዋናቸውን በማሳየት ልብሳቸውንም ወደ ቤት በመሄድ መቀየር እንደማያስፈልጋቸው አመልክተዋል፡፡

ለጃንጥላ ጥገና ክፍያ የሚጠየቀው እንደጃንጥላው የብልሽት መጠን ብቻ ሳይሆን እንደ ገበያና እንደ አሰሪው አቅም ጭምር ነው፡፡ የጃንጥላ ጥገና ሥራ ከገንዘብ ማግኛና ከኑሮን መደጐሚያነት ባሻገር ከአልባሌ ቦታ መራቂያቸውም ጭምር ነው፡፡

በአሁኑ ወቅት ተምረው የተሻለ ሥራ ወይም ባሉበት ሥራ እድገት ማግኘት የማይታሰብ እንደሆነ የሚናገሩት አቶ አራርሳ ባለቤታቸው በሆስፒታል ውስጥ እንደሚሰሩና ተጋግዘው ልጆቻቸውን ደህና ትምህርት ቤት ለማስተማርና ለጥሩ ደረጃ ለማብቃት እንደሚጥሩ አመልክተዋል፡፡

ጃንጥላ ለመጠገን የወሰደባቸው የሦስት ወይም የአራት ቀን ልምምድ እንደነበር በማስታወስ ማንኛውም ሰው በመሥራት ሕይወቱን ለመለወጥ ካሰበ በቀላሉ ሊሰራው የሚችለውን ሥራ ለመጀመር ልበ ሙሉና የውሳኔ ሰው መሆን እንዳለበት ይመክራሉ፡፡  ሹራብ ሰሪ ክረምት ይወዳል"

ጃንጥላ ለመጠገን የወሰደባቸው የሦስት ወይም የአራት ቀን ልምምድ እንደነበር በማስታወስ ማንኛውም ሰው በመሥራት ሕይወቱን ለመለወጥ ካሰበ በቀላሉ ሊሰራው የሚችለውን ሥራ ለመጀመር ልበ ሙሉና የውሳኔ ሰው መሆን እንዳለበት ይመክራሉ፡፡
 
< Prev   Next >