Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Thursday
Aug 28th
Home arrow Sections arrow የምግብና የነዳጅ ፍላጎት መጨመር...
የምግብና የነዳጅ ፍላጎት መጨመር... Print E-mail
Wednesday, 16 July 2008

Imageየምግብና የነዳጅ ፍላጎት መጨመር ደንን እያወደመ ነው

የምግብና የነዳጅ ሰብሎችን ማምረት እንዲሁም የእንጨት ፍላጎት መጨመር የደን መጥፋትን ያስከትላል ሲል የ"ዘ ራይትስ ኤንድ ሪሶርስስ ኢንሽየቲቭ" ሪፖርት አስጠንቅቋል፡፡

 

ቢቢሲ እንዳተተው እ.ኤ.አ በ2030 የምግብና የነዳጅ ሰብሎችን ለማምረት ከሚያስፈልገው ነፃ ተጨማሪ መሬት ግማሹን ብቻ ለማግኘት ይቻላል፡፡ ይህ በምድር ወገብ አካባቢ የሚገኙ ጥቅጥቅ ደኖችን ሳይጨምር ነው፡፡

ሪፖርቱ እንዳመለከተው በማደግ ላይ በሚገኙ አገራት ያለው ኋላ ቀር የመሬት ባለቤትነት ማሻሻያ ፕሮግራምና የመልካም አስተዳደር እጦት ለችግሩ እንደ ምክንያት ይጠቀሳሉ፡፡

"በደን መጨፍጨፍ ምክንያት ከዚህ የባሰ የደን መውደም፣ ግጭት፣ የካርቦን ትነት፣ የአየር ንብረት ለውጥ እንዲሁም ድህነት እየተንሰራፋ ይሄዳል" በማለት የሪፖርቱ ፀሐፊ አንዲ ዋይት ተናግረዋል፡፡

በምግብ ፍላጎት መጨመር፣ በባዮፊዩል ሰብል እንዲሁም ለወረቀት፣ ለኢንዱስትሪና ለግንባታ በሚያስፈልጉ እንጨቶች ምክንያት በ2030 ተጨማሪ ሰብሎችን ለማምረትና ዛፎችን ለመትከል 515 ሚሊዮን ሄክታር ተጨማሪ መሬት ያስፈልጋል፡፡

በተባበሩት መንግስታት ሪፖርት መሠረት፣ በዓለማችን በአሁኑ ሰዓት 1.4 ቢሊዮን ሔክታር መሬት የእርሻ ሲሆን 3.4 ቢሊዮን ሄክታር ደግሞ ለግጦሽ ውሏል፡፡

በአንዳንድ አካባቢዎች የዘር ምርት የመስጠት አቅም እየወደቀ ሲሆን፣ ለዚህም የአየር ንብረት ለውጥ እንደ ምክንያት ይጠቀሳል፡፡ በሌላ በኩል ተጨማሪ መሬት ለማግኘት ተብሎ በምድር ወገብ አካባቢ ያሉ ደኖችን መጨፍጨፍ የአየር ንብረት ለውጡን እንደሚያባብሰው ሪፖርቱ አመልክቷል፡፡

ችግሩ ከመባባሱ በፊት የመሬት ባለቤትነት መብት ፖሊሲዎችን መከለስ አስፈላጊ ይሆናል፤ የአንድ አካባቢ ተወላጆችና ነዋሪዎች በየአካባቢያቸው የሚገኝ መሬትን ለማስተዳደርና ጠብቆ ለማቆየት ቅድሚያ መብት እንዲሰጣቸው ሁኔታዎችን ለማመቻቸት ጥናት እንደሚኖረውም ጠቅሷል፡፡

ደስታ የህይወት አሉታዊ ገጠመኝዎን ያክማል


በህይወት ዘመንዎ፣ የሚያጋጥምዎት እንደ ልጅ መውለድ፣ ትዳር መያዝና የመሳሰሉት ደስታን ይፈጥሩልዎታል፡፡ ደስታዎ ግን ጊዜያዊ ቢሆንም የሰውን ልጅ አሉታዊ ገጠመኝ ያክማል የሚለን ዘ ኢኮኖሚክ ጆርናል ሪፖርት ነው፡፡

የሰው ልጅ መሠረታዊ የደስታው መጠን በጎልማሳነት የእድሜ ዘመኑ በሙሉ ተመሳሳይ ነው፡፡

ከእንግሊዝ፣ አሜሪካና ፈረንሳይ የተውጣጡ ኢኮኖሚስቶች በእርካታና ደስታ ዙሪያ ለ20 ዓመታት የዘለቀውን ምርምራቸውን ያደረጉት በጀርመን የሚገኙ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን የጥናታቸው ተሳታፊ በማድረግ ነበር፡፡

"አዎንታዊም ሆነ አሉታዊ የሆነ ትልቅ ጉዳይ ለሰው ልጆች ሲያጋጥም የመንፈስ መወጣጠር ይኖራል፡፡ ሆኖም ወዲያው ቀድሞ ወደነበረበት ሁኔታ ይመለሳል፡፡ ከከፍተኛ ድንጋጤ በኋላም የተከሰተ ሀዘን ወደ ነበረበት ቦታ መልሶ የመምጣቱ ሁኔታ በጥናቱ ታይቷል፡፡

በጥናቱ ሰዎች ጥሩም ሆነ መጥፎ አጋጣሚን ካላቸው ሁኔታ ጋር አጣጥመው መሄድ የሚችሉበት አቅም እንዳላቸው ታይቷል፡፡

ከ18 እስከ 60 የእድሜ ክልል ውስጥ በሚገኙ ጀርመናውያን ላይ ላለፉት ሁለት አስርት ዓመታት የደስታቸውን መጠን አስመልክቶ በተደረገው ጥናት ስራ አጥነት ለረዥም ጊዜ ደስታን ይነጥቃል፡፡

በሌሎች አስደንጋጭ ሁኔታዎች ለምሳሌ ፍቺ ወይም ከባል ወይም ሚስት በሞት መለየት የሚያስከትሉት ሐዘን መልሶ የሚያገግም ነው፡፡


የሩሲያ የበረዶ ካምፕ እየቀለጠ ነው

የሩሲያ 20 ሳይንቲስቶች ለጥናት ከሚጠቀሙበት የበረዶ ካምፕ እንዲወጡ የተገደዱት የበረዶ ግግሩ እየቀለጠ በመምጣቱ ነው፡፡

ሳይንቲስቶቹ የጥናት ማዕከላቸውን የመሠረቱት ባለፈው መስከረም በሰሜናዊው ዋልታ 35 ዲግሪ ሴንቲግሬድ ሲሆን አላማቸውም እስከ ቀጣዩ መስከረም ጥናታቸውን እያካሄዱ ለመቆየት ነበር፡፡ ሆኖም ጊዜያዊ የጥናት ማዕከላቸው እየቀለጠ በመምጣቱ ለመውጣት ተገደዋል፡፡

የሩሲያን አርክቲክ ኤንድ አንታርቲክ ሪሰርች ኢንስቲትዩት ጠቅሶ ቢቢሲ እንደዘገበው ሳይንቲስቶቹ በደህና ሁኔታ የሚገኙ ሲሆን ጥናታቸውንም ጨርሰዋል፡፡
የሩሲያ ሳይንቲስቶች ጥናታቸውን ለማድረግ በረዷማ አካባቢዎችን ያዘወትራሉ፡፡ ባህሉን ያዳበሩትም ከ1930ዎቹ ጀምሮ ነው፡፡    


ከካሳቫ ተረፈ ምርት ኤሌክትሪክ ማመንጨት ተቻለ

ናይጄሪያዊው ሲቪል ኢንጂኒየር ዶ/ር ጆሴፍ አድሊን የናይጄሪያ መሠረታዊ ምግብ ከሆነው ካሳቫ ተረፈ ምርት ኤሌክትሪሲቲ ማምረት እንደሚቻል አሳውቋል፡፡

ዶ/ር አድሊን "ፓወር ቱ ዘ ፑር ኦፍ ግሪድ ላይቲንግ ፍሮም ካሳቫ ዌስት ኢን ናይጄሪያ" በሚለው ፕሮጀክታቸው ከአለም ባንክ የ250"000 ዶላር እርዳታ ያገኙ ሲሆን፣ ፕሮጀክቱ በአፍሪካ ምርጥ ፕሮጀክት የሚል ደረጃ አግኝቷል፡፡

ሲ ኤን ኤን እንዳመለከተው የዶ/ር አድሊን በፕሮጀክት በመጀመሪያው ዙር በቀን 200 ኪሎ ዋት የኤሌክትሪክ ፓወር በማምረት ከ2000 በላይ ለሚሆኑ ቤቶች መሠረታዊ ኤሌክትሪክ እንዲያገኙ ያስችላል፡፡

ተጠቃሚዎች መብራት ያገኛሉ፣ ቲቪ፣ ቴፕ እና ሬዲዮ መጠቀም ይችላሉ፡፡ ሆኖም ፍሪጅ ለመጠቀም የሚያስችል ሃይል አያገኙም፡፡

የፕሮጀክቱ ተጠቃሚ የሚሆኑት ከዚህ በፊት ኑሮዋቸውን በኪሮሲን (ነጭ ጋዝ) ላይ ያደረጉ ናቸው፡፡


በዓመት 13 ቢሊዮን ፌስታሎች
ዓለምን ይበክላሉ


በአለም በዓመት 13 ቢሊዮን ፌስታሎች ተጠቃሚዎች እጅ ይደርሳሉ፡፡ በአማካይም ለእያንዳንዱ ሰው በአመት 220 ፌስታል የሚደርሰው ሲሆን፣ አንድ ፌስታል አንድ ሰው ጋር የሚቆየውም ለ12 ደቂቃዎች ያህል ነው፡፡

በሲ ኤን ኤን ዘገባ መሠረት፣ ለጥቂት ደቂቃዎች ብቻ ጥቅም ላይ ውለው የሚጣሉት ፌስታሎች በአለማችን ከፍተኛ የአየር ብክለት አያስከተሉ ይገኛሉ፡፡ በሺህ ለሚቆጠሩ አመታትም አየርን ይበክላሉ፡፡

የ"ኢንቫይሮንመንት ካሊፎርኒያ" ጥናት እንደሚያሳየው በየዓመቱ የሚጣሉ ፕላስቲክ ፌስታሎች በዓመት እስከ አንድ ሚሊዮን የሚደርሱ የባህር እንስሳትን ይገድላሉ፡፡

በእያንዳንዱ ውቂያኖስ በአማካይ 46ሺህ ያህል የተጣሉ ፌስታሎች የሚገኙ ሲሆን የፌስታል ብክለትን ለመከላከልም አገራት የፌስታል ምርትን እስከማገድ የሚደርስ እርምጃ መውሰድ ጀምረዋል፡፡ 
 
< Prev   Next >