| በንብ ኢንሹራንስ ቦርድና በቀድሞ... |
|
|
| Wednesday, 16 January 2008 | |
|
በንብ ኢንሹራንስ ቦርድና በቀድሞ ሥራ አስኪያጅ ውዝግብ ጠቅላላ ጉባኤ ተጠራ ሥራ አስኪያጁ ቦርዱን በፍ/ቤት ከሰዋል በንብ ኢንሹራንስ ኩባንያ ከ20 በመቶ በላይ ድርሻ ያላቸው ባለአክስዮኖች በኦዲተራቸው በኩል እንዲጠራላቸው ባደረጉት ጠቅላላ ጉባኤ አዲስ የዳይሬክተሮች ቦርድ ምርጫ ሊያካሂዱ ነው፡፡ በቀድሞው ሥራ አስኪያጅና በቦርዱ መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት ጉባኤው ይመለከታል፡፡ በኩባንያው ኦዲተር በኩል የተጠራው ጠቅላላ ጉባኤ ጥር 17 ቀን 2000 እንደሚካሄድ የተገለፀ ሲሆን ጉባኤውን ለመጥራት ታስቦ የነበረው ግን ከ3 ወራት በፊት እንደነበር ካነጋገርናቸው ከባለ አክስዮኖች ያገኘነው መረጃ ያስረዳል፡፡ ምንጮች እንደገለፁት በኢንሹራንስ ኩባንያውና በቀድሞው ሥራ አስኪያጅ አቶ አመሃ ተፈሪ መካከል የተፈጠረው አለመግባባት ባለአክስዮኖች ፒቲሽን በማስፈረም በአገሪቱ ንግድ ህግ አንቀጽ 377 (2) በተደነገገው መሰረት ከዋናው ገንዘብ የመቶ ሃያ በላይ ያላቸው ባለአክስዮኖች ጠቅላላ ጉባኤ እንዲካሄድ በጠየቁት መሰረት ጉባኤው ሊጠራ መቻሉንና ጠቅላላ ጉባኤውም በቀረበለት አጀንዳ መሰረት ውሳኔ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በሌላ በኩልም ኦዲተሩ በጠራው ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳ ላይ ባይሰፍርም ፊርማውን ያሰባሰቡት አካላት አሁን ያለው ቦርድ የስልጣን ጊዜ አልፏል የሚል አመለካከት እንዳላቸውና በዚህም መሰረት ምርጫ መካሄዱ አግባብ እንደሆነ ይገልፃሉ፡፡ በቀድሞው የኩባንያው ሥራ አስኪያጅና በቦርዱ መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት ተከትሎም የቀድሞው ሥራ አስኪያጅ ቦርዱን በመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት መክሰሳቸውንና በአሁኑ ጊዜም ጉዳዩ በፍ/ቤት በመታየት ላይ ነው፡፡ የቀድሞውን ሥራ አስኪያጅ ቦርዱ ከሥራ ያሰናበተው ጥፋት የሚላቸውን በመዘርዘር ነው የሚሉት የቦርዱ አባላት በበኩላቸው "ቦርዱ የወሰነው ውሳኔ የማኔጅመንት ጉዳይ ነው፡፡ አንድ ማኔጅመንት የሚፈልገው ሥራ በአግባቡ አልተሰራልኝም ካለ ቀጥሮ የሚያሰራውን ሰው ሥራ እንዳይሰራ ሊያደርግ ይችላል" ብለዋል፡፡ ይህም ውሳኔ የሚወሰነው ሥራ እንዲያቆም የተደረገበትን ምክንያት በመዘርዘር እንደሆነ የጠቆሙት ያነጋገርናቸው የቦርድ አባላት በዚህ ጉዳይ ቦርዱ ተጠያቂ ሊሆን አይችልም ባይ ናቸው፡፡ በኦዲተሩ የጠቅላላ ጉባኤ ጥሪ አጀንዳ መሠረት በዋናነት የቀረበው በኢንሹራንሱ ቦርድና በቀድሞው የኩባንያው ሥራ አስኪያጅ መካከል በተፈጠረ ያለመግባባት ጉዳይ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ከኩባንያው የሥራ ኃላፊዎች አካባቢ ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው ደግሞ ሃያ በመቶ የአክስዮን ድርሻ አላቸው በተባሉ ባለአክስዮኖች የተፈረመው ፒቲሽን መሰረት ጠቅላላ ጉባኤውን ሊያስጠራ የሚችል ምክንያት ነው ወይም አይደለም የሚለውን ጉዳይ ጠቅላላ ጉባኤው የሚወስንበት እንደሆነና አሁን ባለው ደረጃ ግን ከዚህ የበለጠ አስተያየት ለመስጠት እንደማይችሉ ገልፀዋል፡፡ በሌላ በኩል ግን በቦርዱና በቀድሞው ሥራ አስኪያጅ መካከል በተፈጠረው አለመግባባት ሥራ አስኪያጁ አቶ አመሃ ተፈሪ የኩባንያውን ቦርድ በፍ/ቤት ከሰው ጉዳዩ በፍ/ቤት እየታየ እንደሆነ ታውቆ በጠቅላላ ጉባኤ ውሳኔ እንዲሰጥበት በአጀንዳነትም የተያዘው የፍ/ቤቱ ጉዳይ በመታየት ላይ ባለበት ጊዜ ነው፡፡ አሁን በኦዲተሩ በኩል እንዲደረግ የተጠራውን ጠቅላላ ጉባኤ እንዲጠራ ያስተባበሩት እርሳቸው ናቸው የሚል አስተያየት የተሰነዘረ ሲሆን በጠቅላላ ጉባኤው እንዲካሄድ በኦዲተራቸው በኩል ጥሪ ያስተላለፉት ባለ አክስዮኖች ሌላው ጉዳያቸው አሁን ያለው ቦርድ የሥራ ዘመን 21 ቀን አልፎታል የሚል እንደሆነም ያገኘነው መረጃ ያስረዳል፡፡ የኩባንያው የሥራ ኃላፊዎች እንደ ተገኘው መረጃ ደግሞ አቶ አመሃ በቦርዱ አማካኝነት ከሥራ እንዲታገዱ ተደርገው የነበሩት ግንቦት 1999 ዓ.ም ጀምሮ ነው፡፡ ያነጋገርናቸው የኩባንያው የቦርድ አባላት በበኩላቸው ኦዲተሩ ጠቅላላ ጉባኤ እንዲጠራ መወሰኑን እንደሚያውቁ ገልፀው ነገር ግን አጀንዳው ጠቅላላ ጉበኤ ያስጠራል የሚል እምነት እንደሌላቸው ገልፀዋል፡፡ በዳዊት ታዬ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |