| በምን መመዘኛ? |
|
|
| Wednesday, 30 July 2008 | |
|
ከአንድ ወር በፊት የፎቶግራፈር ቢኒያም መንገሻ የተለያዩ ፎቶግራፎች እንዳይታዩ መከልከላቸው አይዘነጋም... የከለከሉትም የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ናቸው፡፡ በሪፖርተር ጋዜጣ ሐምሌ 20 ቀን 2000 ዓ.ም እኔ የምለው ገጽ "ጥበብ ስትታነቅ" በሚል ርዕስ የቀረበው ጽሑፍ፣ ሚኒስትሩ የከለከሉት "ለመልካም ባህል ተቃራኒ ናቸው" በሚል ምክንያት ሳይሆን እንዳልቀረ ጠቁሟል፡፡ ሚኒስትሩ ለመልካም ባህሪ ተቃራኒ የሆኑ ፎቶግራፎችን ለሕዝብ እንዳይቀርቡ መከልከላቸው ጠንቃቃነታቸውን ያሳያል፡፡ ይህም ሊያስመሰግናቸው ይገባል፡፡
ወጣት ሴቶች የሱሪያቸውን መቆለፊያ ዝቅ አድርገው ዳሌያቸው በግልጽ እንዲታይ በሚያደርጉባት፣ ራቁት የሚደነስባቸው የምሽት ጭፈራ ቤቶች እንደ አሸን በበዙባት አገር የፎቶግራፈሩ ሥራዎች "ፀያፍ፣ ብልግናና ለመልካም ባህል ተቃራኒ" ብሎ መፈረጅ ያስቸግራል፡፡ ምክንያቱም ሥራዎቹ በይበልጥ ትኩረት ያደረጉት የፎቶግራፍ ጥበብና የዲጂታል ቴክኖሎጂ የደረሱበትን የእድገት ደረጃዎች ስለሆነ ነው፡፡ ሚኒስትሩም ለመልካም ባህሪ ተቃራኒ ብለው የፈረጁበትን ምክንያት በዝርዝር ብናውቀው መልካም ነው፡፡ ስለሆነም በዚህ የሙያ መስክ የተሰማሩ ወጣት የፎቶግራፈር ባለሙያዎችን ለማበረታታት፣ ለጥበቡም እድገትና መስፋፋት ሲባል ለአውደ ርዕይ እንዲቀርቡ ቢደረግ መልካም ነው፡፡ ውበትንና የአካል ቅርጽን ከማሳየት ያለፈ ነገር አይታይም፡፡ በዚህ ርዕሰስ ያገደው አካልም አስተያየቱን ቢሰነዝር ሚዛናዊ ይሆናል፡፡ (ከበደ አሰፋ፣ ከመርካቶ) |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |